Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

"ሚሚ እና የኦሮሞ እንባ" Mimi Sibhatu


( በኢብሳ
ዱጋሳ ከአድአ በርጋ)
---------------------------------
የዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ሬዲዮ ባለቤት የሆነችዉ ሚሚ ስብሃቱ የሁል ጊዜ አጀንዳዋ የኦሮሞን ህዝብ እና የኦሮሚያን መንግስት ማጣጣልና መዝለፍ እንደሆነ ሀገር ያወቀዉ ፀሐይ የሞቀዉ እዉነት ነዉ፡፡ ይህ አስተሳስብ መነሻዉ ምንድን ነዉ? ሚሚ በኦሮሞ ህዝብ እንባ እንዴት እንዳደገች እና በኦሮሞ እንባ እንዴት እየኖረች እንደሆነ አስቃኛችኋለዉ፡፡


1. ፊዉዳላዊ
ትምክህት
ሴትዮዋ፣ ገና ከመነሻዋ ከህጻንነቷ ጀምሮ የኦሮሞ አርሶ አደር እምባ በጡጦ እየጠባች ያደገች ናት፡፡ አባቷ አቶ ስብሃቱ የፊንፊኔ የኦሮሞ አርሶ አደሮችን በማፈናቀል፣ በማስለቀስ ሀብት ያፈራ ፊዉዳል ነዉ፡፡ ለአብነትም አምባሳደር መናፈሻ፣ ብሄረ ጽጌ መናፈሻ እና ሌሎችም ሰፋፊ ንብረቶች የኦሮሞ አርሶ አደርን በማፈናቀል የተገኘ የነሚሚ ወላጆች ሀብት ነዉ፡፡ ያኔ የተፈናቀለዉ ሚስኪን የኦሮሞ አርሶ አደር የሚከተለዉን የጭቆና እንጉርጉሮ ለሚሚ አባት እና ለመሰሎቹ እያንጎራጎረ እግር ወደመራዉ ቦታ በስደት ተበትኗል፡፡
sii bahee biyyaa siibahee (ሄድኩልህ
ሀገር ጥዬ ተሰደድኩልህ)
Yoo muujjaan ollaa siita'ee (እንግዲህ
ሙጃ ጎሮቤት ይሁንህ)
sii bahee biyyaa siibahee (ሄድኩልህ
ሀገር ጥዬ ተሰደድኩልህ)
yoo jaldeessi daboo siibahee (እንግዲህ
ዝንጀሮ ወንፈል ይዉጣልህ) ....
ሄድኩልህ ሀገር ጥዬ ተሰደድኩልህ... እያለ እያንጎራገረ እግር ወደ መራዉ ተሰዷል፡፡ የአራዊት እራት ሆኗል፡፡ ቀየዉን ለቆ በመሰደድ የድህነትና የኋላቀርነት አረንቋ ዉስጥ ወድቋል፡፡ ለብሄር እና ለማንነት ጭቆና ተዳርጓል፡፡ ለዘመናት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የተሸጋገረ ባርነት ዉስጥ በዉርደት ኖሯል፡፡
በአንጻሩ ሚሚ ያደገችበትን ሁኔታ ስናይ ከሚስኪኑ የኦሮሞ አርሶ አደር በተዘረፈ መሬት በተገኘ ሀብት ተቀማጥላ፣ ያሰኛትን በልታ የሻት ለብሳ፣ ምርጥ በተባለ /ቤት ገብታ እየተማረች ነበር ያደገችዉ፡፡ በእንዲህ መልኩ ከኦሮሞ በተዘረፈ ሀብት ከማደጓ በተጨማሪ የኦሮሞ የሚባል ፍጡር አይደለም የሰዉ ልጅ የእንስሳ ክብር እንኳ እንደማይገባዉ፣ ደንቆሮና ኋላቀር እንደሆነ እየተነገራት ነዉ ያደገችዉ፡፡ በአንጻሩ የተፈናቀሉት የኦሮሞ አርሶ አደር ልጆች በአዕምሮ ደሀ ባይሆኑም፣ በአይኪዉ ከሚሚ ባያንሱም፤ በነሚሚ አባት እና በመሰሎቻቸዉ ከቀየያቸዉ በመፈናቀላቸዉ የጭሰኛ ልጅ ሆነዉ የዕዉቀትን ብርሃን ሳያዩ፣ ማንበብና መጻፍ ሳይችሉ በጨለማ ኖረዉ ወደ ሞት ጨለማ የተሸኙ ቁጥር ስፍር የላቸዉም፡፡
ይህን ሀሳብ ያነሳሁት ሴትዮዋ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያላት ንቀት፣ በሬዲዮኗ የምታደርገዉ ዘለፋ ምንጩ ፊዉዳላዊ ትምክህተኛ አስተዳደጓ እንደሆነ ለማስገንዘብ ያህል ነዉ፡፡


2. የዛሚ
ኤፍ ኤም 90.7 ሬዲዮ ዉልደት
የዛሚ ሬዲዮ የተገዛበት ገንዘብ ከዬት እንደመጣ ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ / ሚሚ በአበባ ኢንቨስትመንት ስም ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደተመለሰች በለምነቱ ከሚታወቀዉ የመናገሻ ደጋማ አካባቢ ከኦሮሞ አርሶ አደሮች ተነጥቆ የተሰጣት 40 ሄክታር የኢንቨስትመንት መሬት ወሰደች፡፡ መሬቱን የወሰደችዉ አበባ በማምረት ለአካባቢዉ ሰዎች የስራ እድል ፈጥሬ፣ የዉጭ ምንዛሬ አስገኝቼ ራሴንም ሀገሬንም እጠቅማለሁ የሚል አማላይ የኢንቨስትመንት ፕሮፖዛል አስገብታ ነዉ፡፡ የተረከበችዉን መሬት ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላ ምንም ኢንቨስትመንት ሳታካሂድበት በጣም አስገራሚ በሆነ ሁኔታ 29 ሚሊየን ብር ያዉም ለኦሮሞ ነጋዴዎች ሸጠችዉ፡፡ ከተራ ጋዜጠኝነት ወደሚሊየነርነት በአንዴ ተሸጋገረች፡፡ የአባቷን የኦሮሞ አርሶ አደር በማፈናቀል፣ በማስለቀስ ሀብት የማፍራትን ታሪክ ደገመች፡፡ ከዚያም በዚህ ሁኔታ የተገኘዉ ገንዘብ ዛሚ 90.7 ኤፍ ኤም ራዲዮንን አቋቋመችበት፡፡ የኦሮሞ አርሶ አደር መሬት የሚሚን የፕሮፓጋንዳ ማሽን ወለደ፡፡ የኦሮሞ አርሶ አደሮችን እንባ በጡጦ ጠብታ ያደገችዉ ሚሚ በጉልምስናዋ ዘመን የኦሮሞን አርሶ አደር ከሲታ ስጋ በላች፡፡ አጥንቱን ጋጠች፡፡ ደሙንም አጣጥማ ጠጣች፡፡ በጣም ጠገበች፡፡ መልኳም የጠገበ ጭራቅ መሰለ፡፡ የጥጋቧን ጥግ የሚያሳየዉ የኦሮሞን ሀብት በልታ አድጋ፣ በጉልምስና ዘመኗም ሚሊየነር ሆናበት ዝም አለማለቷ ነዉ፡፡ በዚህ ሁኔታ በመሰረተችዉ ሬዲዮ ነጋ ጠባ የኦሮሞን ህዝብ፣ የኦሮሚያን መንግስት፣ ኦህዴድን እየዘለፈች አለች፡፡ በዚህ ረገድ የኦሮሚያን መንግስት፣ ኦህዴድን እየዘለፈች እንድትኖር ከደህንነት መስሪያ ቤት ሁነኛ አጀንዳ አቀባይ ሹማምንት እንዳላትም ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ማን በሷ ጉዳይ ትንፍሽ ሊል ይችላል?


3. ዳንጎቴ
ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምን ተቃጠለ?
2008 . በኦሮሚያ ክልል በተቀጣጠለዉ አመጽ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸዉ ፋብሪካዎች ዉስጥ አንዱ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ነዉ፡፡ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምን ተቃጠለ? ምላሹ አጭር እና ግልጽ ነዉ፡፡ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የተቃጠለዉ በሚሚ ስብሃቱ ስራ ነዉ፡፡ ጉዳዩን ግልጽ ለማድረግ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኛን የሚያቀርበዉ ኤጂንሲ የሚሚ ስብሃቱ ነዉ፡፡ ሚሚ በኤጄንሲዉ አማካይነት ለፋብሪካዉ የሚቀጠሩ ሰራተኞችን እጅግ ባፈጠጠ አድሎአዊ አሰራር መፈጸሙን ተያያዘቸዉ፡፡ የአደአ በርጋ ወጣቶች ወደ ዳንጎቴ ሲሚንቶ በሾፌርነት፣ በጫኝ አዉራጅነት፣ በጥበቃ ስራ በላብ አደርነት ለመቀጠር ሲሄዱ ዋስ የሚሆናችሁ ሰዉ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ካርታ ማቅረብ አለበት የሚል ቅድመ ሁኔታ ተቀመጠ፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አርማ ያለበት የመንጃ ፈቃድ ተቀባይነት አጣ፡፡ የአድአ በርጋ፣ የበቡራዩ፣ የሆለታ የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታዎች አንድን ሰዉ በሲሚንቶ ፋብሪካ በላብአደርነት ለማስቀጠር አቅም አጡ፡፡ የአድአ በርጋ ወጣቶች ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ የስራ ዕድል ተገለሉ፡፡ በአንጻሩ የሚሚ ስብሃቱ ዘመድ አዝማዶች ከማኔጅመንት እስከ ጉልበት ስራ፣ ከጥበቃ እስከ ጽዳት፣ ከሾፌርነት እስከ ሲሚንቶ አከፋፋይነት የዳንጎቴ ኩባንያ ቤተሰብ ሆኑ፡፡ የአድአ በርጋ ወጣቶች ስራ በማጣታቸዉ ተከፉ፡፡ በአባታቸዉ ሀገር በመገለላቸዉ አለቀሱ፡፡ ሚሚም የወጣት ኦሮሞዎችን ትኩስ እንባ እንደምትወደዉ ቮድካ እና ጫት አጣጣመችዉ፡፡ የአድአ በርጋ ወጣቶች የቁጣ ትንፋሽ እንደምትወደዉ ሲጋራ እና ሺሻ ጭስ ማገችዉ፡፡ በዚህ ቁጣ ዉስጥ የነበሩ የአድአ በርጋ ወጣቶች 2008 . በኦሮሚያ ክልል በተቀጣጠለዉ አመጽ አድአ በርጋ ዉስጥ ያሉ እንደ ደርባ፣ ሙገር እና ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካዎች እንድም ጉዳት እንዳይደርስባቸዉ ጠብቀዉ ዳንጎቴ የሲሚንቶ ፋብሪካን አቃጠሉ፡፡ የዳንጎቴ ዘመናዊ የሲሚንቶ ማመላለሻ መኪኖች ወደ አመድነት ተቀየሩ፡፡ የተቃጠሉ የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ መኪኖች አሁንም ድረስ ከሞጆ ወደ ሀዋሳ በሚወስደዉ መንገድ ላይ እንደሚሚ ከንፈር በእሳት ተለብልበዉ ሚሚ ስብሃቱን መስለዉ ከስለዉ ቆመዋል፡፡
4. ማጠቃለያ
አሁን ባለዉ ተጨባጭ ሁኔታ በኦሮሞ ህዝብ ጠላትነት ከተሰለፉ ሰዎች ዉስጥ ሚሚ ስብሃቱ፣ በኦሮሞ ህዝብ ጠላትነት ከተሰለፉ የሚዲያ ተቋማት ዉስጥ የዛሚ ኤፍ.ኤም 90.7 መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነዉ፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ይህን ሚዲያ ቦይኮት ማድረግ አለበት፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በዚህ ሚዲያ ማስታወቂያ የሚያስነግሩ ኩባንያዎችን ምርትና አገልግሎት ባለመጠቀም የሚሚና የዛሚን የጥላቻ ሰንኮፍ መንቀል ይኖርበታል፡፡"

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved