Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

ቀን ሐምሌ 2009 ዓም
ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የፌዴረሽን ምክር ቤት
/


ጉዳዩ፡ በቤ/ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመተከል ዞን በወንበራ ወረዳ፣ድባጢ ወረዳ፣እና ቡለን ወረዳ ዉስጥ የምንገኝ የኦሮሞ ብሔር ራሳችንን በራሳችን እንድናስተዳድር ዘንድ ስለመጠየቅ ይሆናል፡፡
የኢ... ፌዴረሽን /ቤት 1987 / በጸደቀዉ የኢ... ህገ መንግስት አንቀጽ 53 እና 61 እንዲሁም የፌዴረሽን /ቤት ለማጠናከር በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 3 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የብሄሮች ብሄረሰቦች ህዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን በተመለከተ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎች ላይ በህገ-መንግስቱ መሰረት የመወሰን ስልጣን ስላለዉ እኛም በመተከል ዞን ዉስጥ የምንገኝ የኦሮሞ ብሄር ጥያቄያችንን ለዚህ ክቡር /ቤት አቅርበናል፡፡
እንደሚታወቀዉ የኦሮሞ ህዝብ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ከጥንት ጀምሮ ከሚኖሩት ህዝቦች መካከል አንዱና በህዝብ ብዛትም ቅድሚያ የሚይዝ የአገራችን ትልቁ ማህበረሰብ መሆኑ እዉን ነዉ፡፡ይህ ትልቅ ህዝብ በተለያዩ ታሪካዊ አጋጣሚዎች 16ኛዉ መቶ /ዘመን ጀምሮ በሀገራችን ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በመስፋፋት የራሱን ግዛትና የአስተዳደር ስርዓት ዘርግቶ ስኖር የቆየና እየኖረ የሚገኝ ህዝብ ነዉ፡፡

በዚህም መሰረት ብዙ የኦሮሞ አባቶች በምዕራብና በምስራቅ ወለጋ አባይን ተሻግረዉ እስከ ሱዳን ድንበር ድረስ 16ኛዉ መቶ /ዘመን ጀምሮ በአካባቢዉ ስኖሩ የነበሩ መሆናቸዉን ታርክ ከሚያረጋግጠዉ በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ መሬት ላይ ያለ የማይካድ/የማይሸፈን ሀቅ ነዉ፡፡ከዚህም የተነሳ በዛሬዋ መተከል ዞን ዉስጥ የኦሮሞ ህዝብ በወምበራ ወረዳ፣ድባጢ ወረዳ፣እና ቡለን ወረዳ ዉስጥ ከላይ በተጠቀሰዉ ጊዜ ጀምሮ የራሱ የሆነ ባህል፣ቋንቋ፣ታሪክና እሴቶችን ይዞ በተወሰነና በታወቀ መልከዓ-ምድር ላይ ሰፍሮ ሲኖር የነበረ እና እየኖረ ያለ ብሄር ነዉ፡፡ ምንም እንኳን የክልሉ ባለስልጣናት በተለይም የመተከል ዞን ባለስልጣናት በዞኑ የሚኖሩትን የኦሮሞ ህዝብ ብዛት እንዳይታወቅ በማሰብ የህዝቡን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ ትክክለኛዉን የህዝቡን ብዛት መግለጽ ቢክዱም በአሁኑ ጊዜ በዚህ በመተከል ዞን 150.000(ከመቶ ሀምሳ ሺህ) እስከ 200.000(ሁለት መቶ ሺህ) የሚገመቱ የኦሮሞ ህዝብ እንደምኖር ይገመታል፡፡

በዚህ ዞን ዉስጥ የሚንገኝ እኛ የኦሮ ብሄር ተወላጆች እንደማንኛዉም የኢትዮጵያ እና የክልሉ ህዝቦች በሀገር ግንባታ ዉስጥ የላቀ አስተዋጽኦ እያደረግን የቆየን እና እያደረግን ያለን ህዝብ ነን፡፡በዚህ ክልል ይኖሩ የነበሩ ቅድመ-አያቶቻችንና አያቶቻችን እንደማንኛዉም የሀገሪቱ ህዝቦች የኢትዮጵያን ድንበር እና ህልዉና ከሚፈታተኑ የሀገር ዉስጥ እና ሀገር ዉጭ ወራሪዎች ጠብቆ የዛሬዋን ኢትዮጵያ ለማቆየት ጉልህ አስተዋጽኦ የነበራችዉ ሲሆን እኛም ዛሬ በአሁንቷ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ መስኮች እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ
የበኩላችን አስተዋጽኦ እያበረከትን እንገኛለን፡፡
እንደምታወቀዉ አገራችን ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜያት በፀረ- ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ ስትማቅቅ የነበረች ሀገር ነች፡፡ዜጎች መብታቸዉንና ጥቅማቸዉን በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ማስጠበቅ የሚችሉበት እድል ተነፈጓቸዉ የነበሩባት ሀገር ነበረች፡፡የዜጎች የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተከበረባት፣ መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለማየት በመመኘት ብዙዎች ታግለዉ ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል የዛሬዋን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ችለዋል፡፡ በዚህ የትግል ዉጤት የዜጎች የጋራ ሰነድ የሆነዉ ህገ- መንግስታችን 1987 / በሀገራችን ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጸድቆ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የዜጎች ተጠቃሚነት እንድኖር ተደርጓል፡፡ይሁን እንጂ እኛ በመተከል ዞን በወንበራ ወረዳ፣ድባጢ ወረዳና ቡለን ወረዳ የምንኖር የኦሮሞ ብሄር በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ህገ መንግስት የተከበሩልንን መሰረታዊ መብቶችን በክልሉ መንግስት ተነፍገን እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረን እየኖርን ነዉ፡፡በተለይም በሀገሪቱ ህገ መንግስት እና ሀገራችን ያጸደቀቻቸዉን የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ማለትም -የስቭልና ፖለቲካ መብቶች፣የማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ መብቶች እንድሁም የማደግ መብቶችን ህገ-መንግስቱን በጣሰ መልኩ በግልጽ ተነፍገናል፡፡
እኛ በመተከል ዞን ከላይ በተጠቀሱ ወረዳዎች የምንገኝ የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች በሀገርቱ ህገ መንግስት እና በተለያዩ የአለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶች የተደነገጉ እና ሀገራችንም አባል የሆነችበትን ሰነዶች በአግባቡ በክልሉ መንግስት በተለይም በመተከል ዞን መስተዳደር ስራ ላይ ባለመዋላቸዉ የደረሰብን ግፍና በደል ዘርፈ-ብዙ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹ እና ይሄንን የራስን እድል በራስ የመወሰን ህገ መንግስታዊ መብታችን እንድከበርልን ለመጠየቅ እንድንገደድ ካደረጉን ጉዳዮች መካከል ጥቂቶቹን እንደሚከተለዉ እናቀርባለን፡፡
ጥያቄ 1- ራስን በራስ የማስተዳደር ህገ መንግስታዊ መብትን ተነፍገናል፡፡

የኢ... ህገ መንግስት ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባለፉት ስርዓት የተነፈጉትን ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን አማራጭ የለለዉ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 39 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡የሀገራችን ህገ መንግስት የብሄር ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን እንደ አንድ መሰረታዊ መርሆ ያስቀመጠ መሆኑን ከዚሁ አንቀጽ 39 መገንዘብ ይቻላል፡፡በተጨማሪም ሀገራችን ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸዉ የተለያዩ የአለማቀፋዊና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ሰነዶችም ይህንኑ መብት እንደ መርህ በማስቀመጥ የሀገራችንን ህገ መንግስት ድንጋጌ ያጠናክራሉ፡፡ከነዚህ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነዶች ዉስጥ -
. የአለም አቀፍ የስቭልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት (ICCPR)
. የአለም አቀፍ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣እና ባህላዊ መብቶች ስምምነት(ICSECR)
. የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግጋት(UDHR) እና
. የሰብአዊ እና ህዝቦች መብት ዙርያ የተደረገ የአፍሪካ አህጉራዊ ስምምነት(ACHPR) እንደ አብይ ልጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ይህ የብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ዘረፈ ብዙ እና ሰፋ ያሉ መብቶችን በዉስጡ የያዘ መሆኑን ከኢ... ህገመንግስት አንቀጽ 39 እና ከላይ ከተጠቀሱ አለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡በተለይም የኢ... ህገመንግስት አንቀጽ 39/3 ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዘቦች እራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለዉ በማለት በግልጽ ይደነግጋል፡፡በዘህ አንቀጽ ስር ይህ መብት (እራስን የማስተዳደር መብት)ብሄር ብሄረሶቦችና ህዝቦች በሰፈሩበት መልክዓ ምድር ራሱን የሚያስተዳድርበት መንግስታዊ ተቋማት የማቋቋም እንድሁም በክልልና በፈደራል አስተዳደሮች ዉስጥ ሚዛናዊ ዉክልና የማግኘት መብትን እንደሚያጠቃልል በማያሻማ ቋንቋ አስቀምጧል፡፡ ይሁን እንጂ እኛ በመተከል ዞን ከላይ በተጠቀሱ ወረዳዎች ማለትም በወምበራ፣ድባጢ እና ቡለን ዉስጥ ያለን የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ራሳችንን በራሳችን እንኳን ማስተዳደር ቀርቶ በእኛ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍ እና ጭቆና ለመናገር መብቱንም ሆነ እድሉን ተነፍገን እንገኛለን፡፡ከላይ የተጠቀሱት የዞኑ ወረዳዎች የኦሮሞ ህዝብ በተያያዘ እና በተወሰነ መልክዓ ምድር ሰፍሮ የሚገኝ እና አብዛኛዉን የወረዳዎችን የህዝብ ቁጥር ሸፍኖ እያለ ከወረዳ አንስቶ እስከ ፌደራል መንግስት ደረጃ ድረስ ባሉት የመንግስት መዋቅሮች አንድም ተወካይ የለለን እና ኑሮንም የማይታወቅ ስለሆነ የራሳችንን እድል በራሳችን የመወሰን ህገ መንግስታዊ መብታችንን የተነፈግን መሆኑን በግልጽ የሚያመለክት ነዉ፡፡
ከላይ የተገለጸዉን የመብት ጥሰት በሚያባብስ ሁኔታ የክልሉ የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነዉ የተሻሻለዉ የቤ/ጉሙዝ ህገ መንግስት 16ኛዉ መቶ /ዘመን ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱ የዞኑ ወረዳዎች ስንኖር የቆየንን እኛን የኦሮሞ ህዝብ በክልሉ ዉስጥ ምንም አይነት ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንደለለን በግልጽሌሎችየሚል መጥርያ ሰጥቶን ከክልሉ የፖለቲካ ምህዳር ዉጭ አድርጎናል፡፡ይህ 1995/ ተሻሽሎ የወጣዉ የቤ/ጉሙዝ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ህገ መንግሰት በአንቀጽ 2 መሰረት የክልሉባለቤቶችብሄር ብሄረሰቦች በርታ፣ጉሙዝ፣ሽናሻ ማኦ እና ኮሞ ብቻ መሆናቸዉን ያስቀመጣል፡፡

በተጨማሪም ይህ የክልሉ ህገ መንግሰት አንቀጽ 39 የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 2 ስር የክልሉ ባለቤት ተብሎ ለተሰየሙ 5(አምስት)ብሄሮች ብቻ መስጠቱ የእኛን የዞኑን የኦሮሞ ብሄር የራስን እድል በራስ የመወሰን መብትን የነፈገ ከመሆኑም አልፎ የኢ... ህገ መንግስት አንቀጽ 39 ንም በግልጽ የምቃረን ነዉ፡፡ በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 39 ስር የተፈቀደዉ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለአምስቱ(5)የክልል ባለቤት ለተባሉ ብሄሮች ብቻ የሚያገለግል መሆኑን ከዚህ አንቀጽ 39 -በርእሱ ላይ በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ይሄዉም የአንቀጹ ርእስ (የቤኒሻነጉል ጉሙዝ ክልል ባለቤት ብሄር ብሄረሰቦች መብቶች…)የሚል ስሆን ይህ ደግሞ በክልሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 2 ስር ለተዘረዘሩ ለአምስቱ ብሄረሰቦች መብት ብቻ የሚፈቅድና የእኛን የራስ እድል በራስ የመወሰን መብትን በግልጽ የነፈገ ነዉ፡፡

ይህ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንኳ ሊገደብ የማይችል መብት መሆኑን የኢ... ህገ መንግስት አንቀጽ 93(4)() ደንግጎ እያለ የክልሉ ህገ መንግስት ግን በተቃራንዉ ፈጽሞ እኛን መከልከሉ የሀገሪቱን ህገ መንግስት በግልጽ የሚቃረን መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ በመሆኑም የክልሉ ህገ መንግስት ... ህገ መንግስት አንቀጽ 9 ስር የተገለፀዉን የፈደራል ህገ መንግስት የበላይነት መርህን የምቃረን ነዉ፡፡ ከዚህም ባለፈ የክልሉ ህገ መንግስት በክልሉ ላሉት ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እኩል የቆመ ነዉ ለማለት አያስችልም፡፡ ስለዚህ የክልሉ መንግስት አሰራርም ሆነ ህገ መንግስቱ የእኛን በመተከል ዞን የምንገኝ የኦሮሞ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ስላልመለሰልን ይህ የተከበረዉ ምክር ቤት የደረሰብንን በደል በማገናዘብ ራሳችንን በራሳችን እንድናስተዳድር እንድፈቅድልን እንጠይቃለን፡፡


ጥያቄ 2-በራሳችን ቋንቋ የመማር፣የራሳችን ቋንቋ እና ባህል የመግለፅ እና የማሳደግ እንድሁም የራሳችን ሀይማኖት የመግለጽ መብቶችን ተነፍገናል፡፡ እንደሚታወቀዉ የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ባደረጉት የጋራ ትግል የአህዳዊ የመንግስት ስርኣትን ገርስሰዉ ፈደራላዊና ድሞክራስያዊ መንግስት ለመገንባት ያነሳሳቸዉ አንዱና ትልቁ ምክንያት ባለፉት ስርአት ህዝቦች በራሳቸዉ ቋንቋ የመማር የመናገርና የማሳደግ የራሳቸዉን ባህል የማዳበርና የፈለጉትን ሀይማኖት የማንጸባረቅ መብቶችን በመነፈጋቸዉ ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት የብሄር በሄረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ ትግል ዉጤት የሆነዉ የኢ... ህገ መንግስት አንቀጽ 39(2)
ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰብ፣ህዝብ በቋንቋዉ የመናገር፣የመጻፍ፡ቋንቋዉን የማሳደግና ባህሉን
የመግለጽ፣የማዳበር እና የማስፋፋት እንድሁም ታሪኩን የማንከባበከብ መብት እንዳለዉ በመግለጽ ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ያጸደቀቻቸዉ አለማቀፋዊ እና አህጉራዊ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ይህንኑ የሚያጠናክሩ ናቸዉ፡፡ ለአንድ ማህበረሰብ በአፍ መፍቻ ቋንቋ መማር ከላይ የተጠቀሱ መብቶችን ለመተግበር ዋነኛዉ እና ቁልፍ ሚና የሚጫወት መሳርያ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የአንድ ብሄር፣ ቋንቋ ፣ባህል እና ሀይማኖትን አስወግደዉ ሁሉም በራሱ ቋንቋ እና በፈለገዉ ቋንቋ የመማር፣የማሳደግ፣የፈለገዉን ሀይማኖት የማንጸባረቅ እና የራሱን ባህል የማዳበር መብት ከተጎናጸፈ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ቢሆንም እኛ በመተከል ዞን ዉስጥ የምንገኝ የኦሮሞ ህዝቦች በክልሉ መንግስት በተለይም በዞኑ ባለስልጣናት እነኝህን ከላይ የተዘረዘሩትን መብቶች ተነፍገን እንገኛለን፡፡
ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ እንዲማሩ ማድረግ የበለጠ ዉጤታማ እንደሚያደርጋቸዉ በህጻናት ትምህርት ዙርያ የተሰሩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡በተጨማሪም በህጻናት መብት ዙርያ የተደነገጉ አለማቀፋዊ እና አህጉራዊ ስምምነቶች ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ የመማር መብት እንዳላቸዉ ያስቀምጣሉ፡፡ ይሁን እንጂ የእኛ የመተከል ኦሮሞ ህጻናት ይህንን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር መብት ማጣታቸዉ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ ከሚማሩ ህጻናት ጋር ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ ከማድረግም አልፎ ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸዉ የመማር መብት አላቸዉ የሚለዉን ህግ የሚጻረር ነዉ፡፡ የክልሉ መንግስትም ይህን የህጻናት መብት የመተግበር ግዴታ ያለዉ ሆኖ ሳለ ይህንን ግዴታዉን ወደ ጎን በመተዉ በመተክል ዉስጥ የሚገኙ የኦሮሞ ብዙ ሺህ ህጻናት ተገደዉ በማያዉቁትና በማይፈልጉት ሁለት (2)እና ከዚያ በላይ የራሳቸዉ ባልሆነ ቋንቋ እንዲማሩ ማስገደድ -ህገ መንግስታዊ ድርጊት ነዉ፡፡

እኛም በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ለመማር በተለያዩ ጊዜያት የክልሉን መንግስት ላለፉት 25(ሃያ አምስት) ዓመታት በሙሉ ብንጠይቅም ይህንን ጥያቄ በሚያቀርቡ ግለሰቦች ላይ የድብደባ እና የእስራት እርምጃ ከመዉሰድ ባለፈ መፈትሄ ሊሰጡን አልፈለጉም፡፡ በተጨማሪም በዚህ ዞን የተወለዱ የኦሮሞ ልጆች በክልሉ አድሎአዊ አሰራር ምክንያት ስራ የማግኘት ዕድላቸዉ በጣም አነስተኛ በመሆኑ ወደ ኦሮሚያ ክልል ሄደዉ ስራ ለማገኘት እንኳን የራሳቸዉ የሆነዉን የክልሉን የአፋን ኦሮሞን ቋንቋ መጻፍና ማንበብ ባለመቻላቸዉ ብዙዎች በቤ/ጉሙዝ ክልል ዉስጥ ስራ አጥ ሆነዉ በየቦታዉ እየተንከራተቱ ይገኛሉ፡፡
አንድ ማህበረሰብ የራሱን ባህል ለማሳደግ በመጀመርያ ደረጃ የባህል እሴቶቹን በራሱ ቋንቋ በመጻፍ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ በማስተላለፍ መጠቀም እና መንከባከብ መቻል አለበት፡፡ ስለዚህ ለአንድ ማህበረሰብ የባህል ዕድገት የቋንቋዉ ዕድገት መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ እና ቋንቋ ደግሞ ማደግ የምችለዉ ዜጎች በቋንቋቸዉ የመማር መብት ስጎናፀፉ እና ይህም መብት ስተገበርላቸዉ ስለሆነ መንግስት ትኩረት ልያደርግበት የምገባ ጉዳይ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ እኛ በመተከል ዞን የምንገኝ የኦሮሞ ህዝቦች በራሳችን ቋንቋ የመማር መብታችንን ስለተነፈግን የራሳችን ባህል ማሳደግም ሆነ ማስተዋወቅ አልቻልንም፡፡ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከዛሬ 25 አመት አካባቢ የተመለሰላቸዉ የመብት ጥያቄ እስካሁን ድረስ በክልሉ መንግስት ጭቆና ምክንያት ያልተመለሰልን መብት መሆኑን ያመላክታል፡፡
በታርክም ሆነ በአሁኑ ጊዜ በተጨባጭ እንደሚታየዉ የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ በገዳ ስርአት የሚተዳደር ሰፊ ህዝብ መሆኑ ይታወቃል፡፡እኛ በመተከል ዞን የሚንገኝ የኦሮሞ ህዝቦችም ከጥንት ከአባቶቻችን የወረስነዉን የገዳ ስርዓት እና የዋቄፋና እምነት ስንከተል ብንቆይም 25(ሃያ አምስት )አመት ወድህ ይህ የገዳ ስርኣትም ሆነ የዋቄፋና እምነት በዞኑ እንዳይቀጥል በክልሉ እና በዞኑ መንግስት ታግዷል፡፡ በጣም የሚያሳዘነዉና የሚገርመዉ ደግሞ በክልሉ መንግስት የተቋረጠዉ የገዳ ስርአት እና የዋቄፋና እምነት የዛሬ 7(ስባት) አመት ገደማ በፌደራል መንግስት ተፈቅዶልን በለመድነዉ ስርአት መተዳደር እና እምነታችንን ማስተዋወቅ ስንጀምር አሁንም የክልሉ መንግስት የተጀመረዉን የገዳ ስርአት እና የዋቄፋና እምነት እንድቆም ከማደረጉም ባሻገር የድርጅቱን ንብረት ሙሉ በሙሉ በመዉረስ የስርኣቱን አባ ገዳ መሪዎች ለእስር ዳረጓቸዋል፡፡ይህ አይነቱ ድርጊት ደግሞ ሆን ተብሎ በክልሉ መንግስት የእኛን ባህል እና ቋንቋ ከዞኑ ለማዳከም እና ማንነታችንን ለማጥፋት የሚሰራ ሴራ መሆኑን ያሳያል፡፡ ስለዚህ ይህ መብት በሀገሪቱ ህገመንግስት በግልጽ ተደንግጎ እያለ በክልሉ መንግስት መነፈጋችን አግባብነት የለሌዉ እና የክልሉ መንግስት ይህ መብት እንዲከበርልን ፈላጎት የለሌዉ ስለሆነ ይህ የተከበረዉ ምክር ቤት ይህንን እና ከላይ የገለጽናቸዉን ችግሮች ከሀገሪቱ ህገ መንግስት ጋር በማገናዘብ ራሳችን በራሳችን እንድናስተዳድር እንዲፈቅድልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡


ጥያቄ 3-የእኩልነት እና የእኩል ተጠቃሚነት መብቶችንተነፍገናል።
የኢ.... ህገ መንግስት አንቀጽ 25 ሁሉም ሰዎች በዘር፣በብሄር፣በብሄረሰብ፣በቋንቋ፣በቀለም፣ በጾታ እና በሀይማኖት እንዲሁም በትዉልድ ወይም በሌላ አቋም ምክንያት ልዩነት ሳያደርግ ሰዎች ሁሉ እኩል እና ተጨባጭ የህግ ዋስትና የማግኘት መብት እንዳላቸዉ ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ የክልሉ መንግስት ይህንን የእኩልነት መርህ በመጣስ የተማሪዎች ከክፍል ወደ ክፍል የማለፈያ ዉጤት ጀምሮ እስከ የስራ እድል ማግኘት ድረስ የክልሉ ባለቤት በሚባሉ ብሄሮች እና የኦሮሞ ብሄር መካከል ፍታዊ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ልዩነት ስያደርግ ይታያል፡፡ በትምህርት አለም ዉስጥ ከክፍል ወደክፍል የመዘዋወርያ ዉጤት በተመለከተ 8(ሰምንተኛ)ክፍል የሚኒስትሪ ማለፈያ ዉጤት፣የ10(አስረኛ )ክፍል ማለፍያ ዉጤት፡የዩኒቨርሲት መግብያ ዉጤት እና በክልሉ ዉስጥ ተወዳድሮ የትምህርት *እድል እና የስራ እድል ለማግኘት የሚያስፈልገዉ ዉጤት በእኛ በኦሮሞ ብሄር እና የክልል ባለቤት በተባሉ አመስቱ(5) ብሄለሰቦች መካከል እኩል አለመሆኑ ከላይ የተጠቀሰዉን የእኩልነት መርህ የሚጥስ ስለሆነ -ህገ መንግስታዊ ነዉ፡፡ በተለይም የሁሉም የዞኑ ብሄር ብሄረሰብ ተማሪዎች በአንድ / ቤት፣በአንድ አይነት መምህር፣ እና በተመሳሳይ ሁኔታ ተምረዉ አንድ አይነት ፈተና ከወሰዱ በኃላ የኦሮሞ ተማሪዎች ኦሮሞ በመሆናቸዉ ብቻ የማለፍያ ዉጤት ከሌሎች የክልሉ ባለቤት ከሚባሉት ብሄረሰቦች ተለይቶ መታየቱ የሀገሪቱን ህገ መንግስት በግልጽ የሚፃረር ድሪጊት ነዉ፡፡

ይህ የክልሉ -ፍትሃዊ ድርጊት ሳያንስ ሆን ተብሎ የኦሮሞ ልጆች ብሄራቸዉን ወደ አምስቱ(5) የክልሉ ባለቤት ወደተባሉ ብሄረሰቦች በተለይም ወደ ሺናሻ ብሄረሰብ ቢቀይሩ የት/ ማለፍያ ዉጤት በእነዚህ ብሄረሰብ ሁኔታ የሚታይለት እና የስራ እድል ያገኛል በሚል ማንነታችንን ለማጥፋት ታስቦ የሚሰር ሴራ መሆኑ ታዉቆ የራሳችን እድል በራሳችን የመወሰን መብት ተጠብቆልን ከዚህ ማንነታችን ለማጥፋት ከሚሰራ ሴራ በአስቸኳይ እንድትታደጉን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
በክልሉ ዉስጥ የስራ እድል ለማግኘት እና ለመቀጠር በመተከል ዞን የኦሮሞ ልጆች እና በአምስቱ ብሄረሰብ መካከል -ፍታዊ የሆነ ክፍፍል ስላለ ብዙ የኦሮሞ ብሀር ተወላጆች ህንን የስራ እድል ለማግኘት ማንነታቸዉን ወደ ሌላ ብሄር እንዲቀይሩ እተደረጉ ስለሆነ ይህ የራሳችን እድል በራሳችን የመወሰን መብት ጥያቄያችን እልባት ካላገኘ ለወደፊቱ በዞኑ ዉስጥ የእኛ ህዝብ መኖር ጥያቄ ዉስጥ ይገባል፡፡
ዜጎች በሀገሪቱ ዉስጥ ሰርተዉ ከሚያገኙት ገቢ ለመንግስት ግብር የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸዉ ሁሉ መንግስት ደግሞ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ለዜጎች የመሰረተ ልማት አዉታሮችን ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡በዚህም መሰረት መተከል ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች በቡና፣ሰሊጥ፣ማር፣ቅቤ፣የጋማ ከብቶች እና በተለይም በማእድን ምርቶች የታወቁ ከመሆናቸዉ የተነሳ ለክልሉም ሆነ ለዞኑ ትልቅ የገቢ ምንጭ በማስገኘት ቀዳሚዉን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በአካባቢዉ አብዛኛዉ ነዋሪ የኦሮሞ ብሄር በመሆኑ ብቻ እነዚህን የመሰረተ ልማት አዉታሮችን ተነፍገናል፡፡በተለይም በዞኑ ከምገኙ ከተሞች በወምበራ፣በጋሌሳ እና በርበር ከተሞች መብራት እናስገባለን በማለት የመብራት ፖል ብቻ አቆመዉ ምንም አይነት አገልግሎት ሣይሰጥ አስር አመታትን እያስቆጠረ ይገኛል፡፡በጣም የሚያሳዝነዉ እና ግልጽ የሆነ አድሎ የሚታየዉ ደግሞ በዞኑ ካሉት ወረዳዎች የወምበራ ወረዳ እሰካሁን የመብራት እና የዉሃ አገልግሎት እንድያገኝ አልተደረገም፡፡ይህ ደግሞ በወረዳዉ 85% በላይ የሚሆነዉ ነዋሪ የእኛ የኦሮሞ ብሄር መሆናቸዉ እንጂ ምንም ሌላ ምክንያት የለዉም፡፡


በተመሳሳይ ሁኔታ የተለያዩ የመሰረተ ልማት አዉታሮች እንደ መንገድ፣ንጹህ የመጠጥ ዉሃ አቅርቦት፡የጤና አገልግሎት፣የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት እና ሌሎችም በዞኑ የኦሮሞ ህዝቦች በብዛት ባሉበት ቦታ ተለይቶ ያልተሟሉ መሆናቸዉ በተጨባጭ የሚታይ እዉነታ እና ግልጽ የሆነ የክልሉ አድሎአዊ አሰራር የሚያሳይ ነዉ፡፡ ይብስ ብሎ ደግሞ በነዚህ አከባቢ የምገኙ እንደ ዜጋ የልማት ጥያቄ የምያቀርቡ የአከባቢዉ ኦሮሞ ተወላጆች በዞኑና በክልሉ ባለስልጣናት እንደ ጠላት የምታዩት ሲሆን ጥያቄዉን የምያቀርበዉ በክልሉ የመንግስት መስሪያቤት ሰራተኛ ከሆኑ ደግሞ ያለቅድሜ ሁኔታ ከስራ ይባረራል ለብዙ መከራ እንግልት ይዳረጋል፡፡ በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች ዉስጥ የምሰሩ የክልሉ በተለይ ደግሞ የመተከል ዞን የኦሮሞ ብሄር ተወላጆች ኦሮሞ በመሆናቸዉ ብቻ ማህበረሰቡን ለማገልገል ቁርጠኝነት እያላቸዉ ከስራቸዉ ተባርረዋል፡፡
በአጠቃላይ በክልሉ መንግስት ስደርስብን የቆየ እና እየደረሰብን ያለ ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ የመብቶች ጥሰት እንድሁም -ህገ መንግስታዊ እና -ፍትሃዊ አሰራሮች በጥቂቱ ከላይ የተገለጹት ሲሆኑ ይህ ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣ የማንነት ማጥፋት ዘመቻ እና ህልዉናችን አደጋ ዉስጥ እየከተተ የሚገኝ አደገኛ ተግባር ነዉ፡፡ ስለዚህ ይህ የተከበረዉ ምክር ቤት በክልሉ መንግስት እየደረሰብን የነበረ እና እየደረሰብን ያለዉን ግፍና በደል በማገናዘብ ለዚህም መፍትኤ ልሆን የምችለዉ ብቸኛዉ ዘዴ ራሳችንን በራሳች ማስተዳደር መሆኑን ተረድቶልን የራሳችንን እድል በራሳችን እንድንወስን እንድፈቅድልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
አመልካቾች እኛ በቤ//// በመተከል ዞን በወምበራ ወረዳ፣በድባጢ ወረዳ እና በቡለን ወረዳ የምንኖር የኦሮሞ ህዝቦች ነን::
ግልባጭ
ለኢ... ጠቅላይ ሚኒስቴር /ቤት
.... ማዕከላዊ ኮሚቴ /ቤት
ለኢ... / ሚኒስቴር
ለኢ... ሴቶች እና ህጻናት ሚኒስቴር
ለኢ... ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
አዲስ አበባ
ኦሮሚያ /// ፕሬዚዳንት /ቤት
ለኦ... መዕከላዊ ኮሚቴ /ቤት
ለኦሮሚያ / ቢሮ
ለኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
ለኦሮሚያ ሴቶች እና ህጻናት ቢሮ
ለኦሮሞ ባህል ማዕከል
ፊንፊኔ
ለቤ//// ፕሬዚዳንት /ቤት
አሶሳ
ለቤ///// መተከል ዞን አስተዳደር /ቤት
ግልገል በለስ

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved