Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

የራያ-ራዩማ የማንነት ጥያቄ Rayya fi Gaafi Enyummaa

 #RayaTimes

 (Tazeze Fekadu Hawu Embeteye)

ጉራ ብቻ የተጠናወታቸው የከሰሩ ጀማሪ የተህሃት የፖለቲካ አጋፋሪዎች(የነገው የዋጃ ድርድር)
* * *
ራያዊ መነሻየ ኩሸቲካዊ ዶብሃዎች እንጂ ሴሜቲካዊ ትግረዋይነት አይደለም
* * *
የራያ-ራዩማ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ለማዳፈን ሌት ተቀን የሚዋትቱት ጉራ ብቻ የተጠናወታቸው የከሰሩ ጀማሪ የተህሃት የፖሊቲካ አጋፋሪዎች በቅርቡ በይፋ የተመሰረተውን የራያ ሕዝብ የማንነትና ራስ-ገዝ ግዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ላይ ጥላሸት መቀባት ከጀመሩ ዋል-አደር ብለዋል። የኮሚቴውም አባላት ከላሳታ፣ ዋግና ሰቆጣ የመጡ መጤዎች እንጂ በራያ ጉዳይ አንዳችም ነገር አይመለከታቸውም ይሉናል። ጨመር ሲያደርጉም ገረገራ ይሉናል፡፡ ላስታ፣ ሰቆታ፣ ገረጋራ ህዝቦች እነማን እንደሆኑ ስንጠይቃቸው ምላሽ የላቸውም ይልቁንስ በድጋሚ ላይከተሉን ይመስል ዘንዳ ያኮርፉናል፡፡ የላስታ፣ የየጁና የዋግ ህዝብ ለራያ ህዝብ እጅግ ቅርብ የሆኑና ትስስራቸውም የደምና የአጥንት ያክል መሆኑ ብዙ ግዜ ቆመን አስተምረናቸዋል፡፡ እነሱ ግን ሁሌም ይረሳሉ የነገርናቸውን በየቀኑ እየረሱ እውነትም ከጫካ የመጡ ገና በዘመነ-ድንጋይ አስተሳሰብ ያሉ በዘመናዊ የታሪክ ትምህርት ያላለፉ የባህሪም ሆነ የዘመናዊነት አስተሳሰብ ለውጥ ያላመጡ በቀቀኖች መሆናቸውን ፍንትው ብለው ይታያሉ፡፡ አጋፋሪዎቹ ከተህሃት ብብት በእንኩቤተር የተፈለፈሉ ተሰባሪ እንቁላሎች እንጂ እነሱ እንደሚሉት ደካማዎች እንጂ ጠንካራዎች አይደሉም፡፡ እስከሂወታችን ፍፃሜ እንታገላችሁኋለን የሚሉን ሸክላ-ስሪት ፈረሰኞች መሬት ላይ ቢወረወሩ በቀላሉ መሰበር የሚችሉ ዘረ-መል ፍጡራን ናቸው፡፡

በተደጋጋሚ የራያን ህዝብ የማንነት ጥያቄን ማንሳት ዘረኝነትና ጎጠኝነት የተጠናወታቸው የዘመኑ ነውጠኞችና ትምክህተኞች ይሉናል፡፡ ራያዊ ማንነት ማንሳት ዘረኝነትን ስለማቀጣጠል፣ ጎጠኝነትን ስለማስፋት፣ ትምክህተኝነት ስለመስበክ፣ ጦርነትን ስለማወጅና ኢትዮጲያዊነት ሰለማደብዘዝ ፈፅሞ የራቀ መሆኑን እነዚህ የተህሃት ምንዱባን ጥራዝ ነጠቅ ታሪክ-አልባ የተህነግ ፈረሰኞች ጠንቅቀው ይረዱታል፡፡ እነዚህ ጀማሪና የከሰሩ የፖለቲካ ቁማርተኞች ራያ ኩሩ ህዝብ ነው፣ የራሱ ባህል፣ ቋንቋ፣ እሴት ያለው ማህበረሰብ ነው ካሉን በኋላ የራያ ጥያቄ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንጂ የራያ ማንነቱ ትግራዋይነት መሆኑ ገልፀው ሁለት የተቃርኖ ሃሳቦች መሆናቸውን እየተረዱት እንኳን ዓይናቸውን በጨው አጥበው ውሎ ያደረ የሞኝ ለቅሶ መልሶ መልሶ ዓይነት የሞኝ ተረት በጀርባቸው ተሸክመው እንሆ 27 ዓመት ሙሉ ጉራቸውን እንደ ፊኛ ሲነፉ በቅዠታዊ ህልም ፈረስ ሲጋልቡ በዘመነ-ድንጋይ የተፈጠሩ እፉኞች የተህሃት አሽከርና የፖለቲካ አጋፋሪዎች መሆናቸው መላ የራያ ህዝብ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ 
እንደ እነ መንገሻ ሓጎስ ፀጋየና ጌታቸው ዳኛው ከበደ ዓይነት የተህሃት ታዳጊ ውርንጭላዎች በራያ ህዝብ ደም የጨቀዩ መሰረተ-ቢሶች የራያ የማንነት ጥያቄ ከስልጣን ምኞት ጋር ሊያያዙት ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ከተህሃት ጋር በመወገን በርካታ የራያ ወጣቶችን እያሳሰሩ፣ እያስገረፉ፣ ጥቆማ በመስጠት በርካታዎችን ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ እያደረጉ የሚገኙ የተህሃት ደም-ስሮች የራያ ህዝብ ነቀርሳዎች መሆናቸውን በመረዳት መላ የራያ ህዝብ እስከወድያኛው ሊመክታቸው ይገባል፡፡ አነዚህ የስዕል-ንድፍ ሰው-መሰል ጉንዳኖች ግማሽ አካላቸው የሰይጣን መንፈስ የተጠናወታቸው እንደ ፈረስ መጭ መጭ እያሉ በየቀኑ የሚጋልቧቸው የተህሃት ፈረሰኞች ናቸው፡፡
በተጨማሪም ጎይትኦም ብርሃኔ፣ ሰለሞን አያሌው(ነጋዴ ነው) እና መምህር ንጉስ አብርሃ(ከዚህ በፊት አፈ ጉባኤ የነበረ) 27 ዓመታት አሁንም ጨምሮ ከተህሃቶች ብር በመቀበል በርካታ የራያ ጀግኖችን ያስገደሉ፣ ያሳሰሩ፣ ያስገረፉና ደብዛቸው እንዲጠፋ ያደረጉ የራያ ህዝብ ጠላቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ድብቅ ዓላማን አንግበው ራያ ራያ ሳይሆን ትግራዋይ ነው እያሉ በየሰፈሩ እየዞሩ አባቶቻችነን እያሰቃዩ ብዙዎችን በስጋት እንዲኖሩ እያደረጉ የሚገኙ በቀቀኖች ከዚህ በላይ ክፋትና ሰቆቃ በህዘባችን ከማምጣታቻው በፊት ከወዲሁ ልንመክታቸው ይገባል፡፡ በተለይ በራያ የማንነት ጉዳይ በየቀኑ የሚያብጠለጥለው አብርሃ ረዳ ከትናንት በስትያ ዋጃ-ጥሙጋ በተገኘበት ወቅት በወንድሞቻችን ድብደባ ሊፈጸምበት የነበረ ሲሆን በሃገሬ ሽማግሌ ሂወቱን ሊያተርፍ ችሏል፡፡ እጅግ ከባድ የሆነ የመጨረሻ ማስጠንቀቅያም እንደተሰጠውም ሰምቻለሁ፡፡ የክፋት ውጤቱ ይህ ነው፡፡ ወንድሜ አብርሃ ረዳ ሆይ እጅግ የምንወድህና የምናከብርህ ወንድማችን ነህና ከዚህ በላይ በራያ ህዝብ ላይ ክፋትን ባታውጅ ጥሩ ይመሰለኛልና እባክህን ወደ ልቦናህ ተመለስ፡፡ የራያ ህዝብ አሁንም እጁን ዘርግቶ ይለምንሃል፡፡ ያስተማረህን ምስኪኑን የራያ ህዝብ ከዚህ በላይ ባታስከፋው ጥሩ ይመስለኛል ተመለስ አሁንም ተመለስ፡፡
ነገር ግን ራያዊ ሳይሆኑ አልያም ቅይጥ ማንነት ያላቸው በተለያየ ግዜ በፌስቡክ ገፃቸው እንዲሚለጥፉት ከሆነ ምንም ታሪክና መሰረት የሌለው በተህሃት አጋፋሪነት ራያ ትግራዋይ ነው ይሉናል፡፡ እንዴት ብለን ስንጠቃቸው ያኮርፉናል፣ ይሰድቡናል፣ ይዝቱብናል፡፡ እኛ ግን ሁሌም እንላቸዋለን በምንም አመክንዮ ራያ ትግራዋይ ሆኖ አያውቅም ሊሆንም አይችልም፡፡ የራያ መነሻ ኩሸቲካዊ ዶብሃ እንጂ ሴሜቲካዊ ትግራዋይነት ሊሆን አይችልም፡፡ እኔ የዶብሃ ደም ያለኝ የነ ኩቢ ሺኩሩ፤ የነ የኣርብሴ ነጋ የነ ሞገስ አራጌ፣ የነ ጌታሁን አርብሴ የዘር ሃረግ ያለኝ ፍፁም ራያዊ እንጂ 45 ዓመታት መነሻቸው ጫካ የሆነ የሰው አጥንት እየጋጡ፣ የሰው ደም እየመጠጡ በሰው ደም ስለጨቀዩት የአቢስንያ ቫምፓየሮች የነ ስብሃት ነጋ የዘር ሃረግ ከቶም አይኖረኝ፡፡ እኔ ኩሸቲካዊ እነሱ ትግራዋይነት ሴሜቲካዊ እንዴትስ ተደርጎ ነው ማንነታሁ ትግራዋይ ነው የምትሉን በምንስ መስፈርት፡፡

እውነት እናውጋ ከተባለ እኔ የጀግኖቹ የነ ሞገስ አባተ፣ የነ ኩቤ ኣባ ቦና፤ የነ ቢቾ ሌንጫ፣ የነ ሮብሶ ደንጎራ፣ የነ ሞገስ ካሳየ፣ የነ ባሮ ኣባሴሮ ፣የነ ባሮ ሓብጦ፣ የነ አበራ በላይ፣ የነ የይርጋ ኣበበ፣ የነ ንጉስ ቸኮለ የልጅ ልጅ የሆነኩኝ ራያዊ እንጂ እናንተ እንደምትሉኝ ትውልዴና ደሜ ከጫካ በመጡ የጫካ ዘላኖች ከቶም ሊሆን አይችልም፡፡ 
የተህሃት የፖሊቲካ አጋፋሪዎች ሆይ እናንተንና መሰሎቻችሁ በትግራይ ስር መተዳደር ማለት ትግራዋይነት ማለት አይደለም፡፡ ቢሆንማ ኖሮ ኩናማወችም ሆነ ኢሮቦች በትግራይ መካለላቸው ትግራዋይነት ያስብላቸው ይሆን፡፡ በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ ወፍላ/ኮረም በትግራይ ስር ሆኖ አያውቅም፡፡ በወንበዴዎቹ የስልጣን ዘመን ወፍላ ሆነ ራያ አላማጣ በትግራይ መካለሉ ትግራዋይነት ሊያስብለው አይችልም፡፡ አንድ አንድ ግዜ ህዝቡን ሊያወናብዱት ሲፈልጉ ቋንቋችሁ ትግሬኛ ነውና እናተ ራያዎች ትግራዋይ ናችሁ ይሉናል እኛም ቋንቋ የአንድን ማንነት መገለጫ ሊሆን አይችልም ስንላቸው ክንፉ በድንጋይ እንደተመታ አሞራ መሬት ላይ ወድቀው ይንገፈገፋሉ፣ ይንጨረጨራሉ፡፡ የማንነት መሰረቱ ቋንቋና ቋንቋ ቢሆንማ ኖሮ አምሃርኛ ተናጋሪው ሊማ ጋጋሪም አምሃራይ በሆነ ነበር፡፡ ዶር አብይም ትግራዋይ በሆነ ነበር፡፡ ቋንቋ በልምምድና በትምህርት ሊገኝ ይችላል ማንነት ግን አንጀት ውስጥ ገብቶ የሚሰረስር አንዳች መግነጢሳዊ ሃይለ-መለኮት ያለው የደምና የአጥንት አውድ ነው፡፡
ጉማየና አሰላዳርየ የኔና የኔው ብቻ ናቸው መነሻቸው ራያ እንጂ ወልዋሎ ዓዲግራት አይደለም፡፡ እነዚህ እጅግ የምኮራባቸው ራያዊ አኩሪ እሴቶቼና መገለጫዎቼ ናቸው፡፡ የማንም አይደሉም፡፡ ሽሬ ወይም ውቕሮ ሄዳችሁ አታገኗቸውም፡፡
ዛር፣ ወዳጃ፣ ቱፍታ፣ ዱባርቴም፣ ጅራፍ ግርፍያ(ትኩዕ) ትግል(ሕሽይ) ሶለል የኔው ናቸው፡፡ እነዚህ የምንኮራባቸው ታሪካዊ መገለጫዎቻችን ናቸው፡፡ የትህነግ ሰዎች አሁንም ሊነጥቁን ይፈልጋሉ፡፡ መቀሌ ብትሄዱ ፍፁም አታገኗቸውም ምክንያቱም የኛና የኛው ብቻ ናቸውና፡፡ እነዚህ የየራሳቸው የታሪክ መስተጋብር ያላቸው በአሁኑ ሰዓት በራያ-ራዩማ መሬት ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
ቃሪሳና ጋሜ የራያ የሴቶች ባህላዊ የፀጉር አሰራር እንጂ የትግራዮች ሊሆንም ከቶም አይችልም፡፡ የራያን ባህላዊ የሴቶች ሙሉ አለባበስ የምንላቸው ገርመዶ፣ መልጎም፣ ትፍትፍ፣ ዲባ፣ ሽራጦ፣ ጉፍታ፣ መቀነት፣ ከቆዳ የተሰራ የህፃናት ማዘል የራያ መዓዛ የተላበሱ አኩሪ መገለጫዎቻችን እንጂ የአታኽልቲ አምባየ መገለጫ ከቶም ሊሆኑ አይችለም፡፡ ጎንቢሶ፣ ገማሬ፣ ሽፋይ ጫማ፣ ዘንግ፣ ዝናር ካሪያ መሰል የራያ የወንዶች ባህላዊ የባህል አልባሳት መነሻቸውም መድረሻቸውም የራ የሆኑ መገለጫዎቻችን እንጂ ለራያ የተላለፉ ከተህሃት በዉርስ የተገኙ አይደሉም(ክፍል ሁለት ላይ ሁሉንም ይዠ ለመቅረብ እሞክራለሁ)
.
ይሄንና መሰል ታሪካዊ እሴቶችና ትውፊቶች የራያ ህዝብ ታደለ ሆኖ ሳለ እነዚህ ሰዎች ራያዊ እንጂ ትግራዋይ አይደለንም ስንላቸው ጉዳዩ ከጥላቻ የመነጨ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ የራያ ህዝብ 27 ዓመት ታሪክ ውስጥ ፍፁም ከትግራይ ህዝብ ጋር አንዳችም ቀን ጠብ ውስጥ ገብቶ አያውቅም ይልቁንስ ጠንካራ ማህበራዊ ትስስር ፈጥሮ የኖረ ኩሩ ህዝብ እንጂ እነሱ እንደሚሉት ውስጣችን የጠብ አጫሪነት ስሜት የተጠናወተን ትእምንቶችም አይደለን፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው ትግራዋይ ማንነቱ፣ ቋንቋውና ባህሉ እንደሚወድና እንደሚያከብር ሁሉ እኛም ማንነታችንና ቋንቋችን በሮ ተደምረን እንኑር እያልን እንጂ ማንነታች፣ ባህላችንና ቋንቋችን ተደፍጥጦ ተደመሩ ብንባል የኛ ምላሽ የሚሆነው እምቢየው ነው፡፡ የዚህን ዓይነት ከንቱ-ልፋት አራማጆች ውስጣቸው በምቀኝነት የተሞላ አላስተዋይነት የተላበሰ ይመስለኛል፡፡
እስኪ የሚፅፉትን አስተውሏቸወው ትናንት በዋጃ-ጥሙጋ ወንድሞቻን በአደባባይ ሲገደሉ ማንም ያወገዘ አልነበረም እኛመ መቃወም ስንጀምር ሰዉን አስገደላችሁት ይሉናል፡፡ ትናንት የራያ ህዝብ በተህሃት ሲገደል፣ ሲዘረፍ፣ ሲሰቃይ፣ ግፍና መከራ ሲፈፀምበትና ማንነቱና ባህሉ ሲደፈጠጥ ዝም ጭጭ ብለው ዛሬ ደርሰው ግን እንደዳበደ ውሻ መጮህ ሲጀምሩ .........ክፍል 2 ይቀጥላል
የክፍል አንድ ምርቃን
መንገሻ ሓጎስ ፀጋየ፣ ጌታቸው ዳኛው ከበደ፣ ጎይትኦም ብርሃኔ፣ ሰለሞን አያሌው(ነጋዴ ነው) እና መምህር ንጉስ አብርሃ(ከዚህ በፊት አፈ ጉባኤ የነበረ) በአሁኑ ሰዓት ከተህሃት ጎን በመወገን በራያ ህዝብ ላይ ሲወነዝፉት የነበረው የክፋት ዱላ እዚህ ይገታና ቢችሉ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው ተመልሰው ከራያ ህዝብ ጎን ተሰልፈው የራያ ህዝብ ከተህሃት ነፃ ለማውጣት እየተፍጨረጨረ ባለበት ሰዓት ከጎኑ እንዲሰለፍ እንመክራለን ካልሆነ ግን ከዚህ በላይ የምንታገስበት አንዳችም ምክንያት የለምና የጥፋት ዱላቸውን እየመከትን ልንወነዝፍ ይገባል፡ እላለሁ፡፡ 
መልካም ቀን

 

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved