Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

Mootii Biyyaa Isaa jira?  ሞቲ ብያን አፋልጉን-

  ኦሮሚያን በፈረቃ  ሞቲ ብያ

Degebassa Feyissa

ሞቲ ብያ አሁንም መኖራቸውንና ለምን ብእራቸውን እነዳስቀመጡ እስከሚነግሩን ድረስ መጽኃፋቻን በመንተራስ ህዝባችን ማስተማር በጀመርነው መሰረት፤ ይህ የሳምነታዊው የሞቲ ብን አፋልጉን ጽኁፍ ለዛሬ የኦሮሞ ጉዳዮችና የገዢዎቻችን/በተቃራኒዎቻቸው አመለካከት በሚል የቀረበ ሲሆን እነደተለመደው /…./ ውስጥ የተካተቱት የጊዜውን ሁኔታና የኔን አመለካከት ያካተተተ ጨማሪ ነው፡፡/ በዚህ ጽኁፍ ሞቲ ብያ ያጣቀሳቸውን የኦሮሞ ምሁራን በአሁን ወቅት በትግል ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎና ይህ ጽኁፍ ሲጻፍ ነበራቸው አመለካከትና የኦሮሞ ፖለቲከኛነት ምን ያህል እነዳደገና እነደ ተቀየረ በመረዳት በቀጥታ አልጠቀስኳቸውም፡፡

የኦሮሞ ጉዳዮችና የገዢዎቻችን/ተቃራኒዎቻችን አመለካከቶች፡፡ ኦሮሚያን በፈረቃ የተቀነጨበ

የኦሮሞ ህዝብ ታላቅ ታሪካዊ ህዝብ ነው፡፡ ዛሬ ‹‹ኢትዮጲያ>> በምትባለው ክልል ለብዙ ሺህ አመታት የኖረ ህዝብ ነው በአፍሪካ ኩሽ ቋንቋ የሚናገር፤ እጅግ ሰፊ በሆነ ክልል ላይ ተንጣሎ የሚገኝ ታላቅ ብሄር ነው፡፡ ጥናቶች እነደሚያሳዩት በአለም ላይ የኩሽ ቋንቋ ከሚናገሩት ውስጥ ከግማሽ በላይ አፋን ኦሮሞ (ኦሮምኛ) ተናጋሪ ናቸው፡፡ ከዚህም ሌላ አፋን ኦሮሞ ከአረቢኛና ከሃውሳ ቀጥሎ ከአለም ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የአፍሮ ኤሺያቲክ ቋንቋ ነው፡፡ እነደዚህ ሆኖ እስከ 1972 . ድረስ በኢትዮጲያ ውስጥ በዚህ ታላቅ ቋንቋ መጻፍ፤ ማሳተም፤ በሬዲዮ መናገር ወይም መስበክ/ወንጌልን ማስተማር/ የተከለከለ ሆኖ ቆይቷል፡፡/ በዛሬይቱ ኢትዮጲያ ሰልጥነን አለም አውቆናል የሚሉትም በአሜሪካን ምድር በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የአማርኛ ቋንቋ የስራ ቋንቋ እንዲሆን አስፈቀድን ብለው በለፈለፉበት አፋቸው፤ የኦሮሞ ህዝብ በገዛ ሃገሩ ቋንቋዬ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን ብሎ መጠየቁን እነደ ወንጀል አድርገው ይመለከቱታል፡፡ 21ኛው ክፍለዘመን እነዲህ ያለው አስተሳሰብ ፍጹም የማይጠበቅና አሳፋሪም ነው፡፡/

የኦሮምኛን ቋንቋ ከኦፊሳሊያዊና አጠቃቀም/ከፌዴራል መንግስት መጠቀምያነት / እንደሁም ከስነጽሁፍና ከማንኛውም የስነ-ጥበብ መስኮች ሆን ብሎ ከማገዱ ጎን የኦሮሞን ህዝብ በአጠቃላይ ‹‹ የአማራ ጠላት›› አድርጎ ማቅረቡም የተለመደ ነው፡፡ /ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እነደሚባለው ሆነና ተበዳዩ ኦሮሞው የሚታማውም ኦሮሞው ሆኖ አረፈው፡፡/ የአሁኑ ጊዜ የአማራ ህዝብ እነደነ አባ በህሬ (1593) እና፤ የክፍለ ዘመኑ አባ ባህሬኖች የሚያሳርፉበት ጫና ብዙ ቢሆንም የኦሮሞን ህዝብ ለመብቱ ስለታገለ እንደ ጠላት መፈረጁን ማቆም እነዳለበት መገንዘብ ይኖርበታል፡፡ በየዘመናቱ በተጨባጭ እነደሚታየው ሃበሾችና ተከታዮቻቸው ኦሮሞን እንደ ችግር ሲመለከቱት ኖረዋል፡፡ ዛሬም ቢሆን ከዚህ አድራጎታቸው አልታቀቡም ለእነሱ ኦሮሞ ችግር ያለበት አይደለም፡፡ በራሱ ችግር ነው፡፡ የህዝብ ጥያቄ የድንበር ጥያቄ ስለሚያስነሳ አስፈላጊ አይደለም፡ ማለት የሚቃጣቸው እነዚህ ወገኖች በአለም ላይ የድንበር ጥያቄን ፈርተው ነጻነታቸውን እነዲቀር ያደረጉ ሀገሮችን ለአብነት ሊጠቅሱልን በተገባቸው ነበር፡፡

በአንዳንድ የኦሮሞ ምሁራን ነን ባዮች ትንተና መሰረት የኦሮሞ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብት ተግባራዊ ማድረግ የማይኖርበት ዋናው ምክንያት ከሁሉም ጋር ስለሚዋሰን ነው፡፡ ጎረቤቶቹ በወሰን ምክንያት ቅር ስለሚሰኙ የኦሮሞ ነጻነትና ነጻ መንግስት ጥያቄ ባይነሳ ይሻላል ማለታቸው ነው፡፡ በተራ የጉርብትና ንሮ ውስጥ በድንበር ምክንያት ከጎረቤት ጋር እጋጫለሁ ብሎ በመፍራት ለግቢው አጥር የማያጥር ማነው፡፡ ሃበሾችና አንዳንድ ኦሮሞ የሃበሻ ወገኖች ኦሮምያን ለመግዛት በኦሮምያ ምድር መሃል መጥተው በቆረቆሩዋቸው ከተሞች ሳቢያ የኦሮሚያ ተፈጥሮአዊ ነጻነት የማያስፈልግ ሆኖ ይቀርባል፡፡ ‹‹በአዲስ አበባ፤ በናዝሬት፤ በድሬደዋ›› በመሳሰሉት ቦታዎች በመጤነታቸው በዝተው በመገኘታቸውና በመዋለዳቸው የኦሮሚያ ነጻነት የማያስፈልግ አድርገው ያቀርቡታል፡፡/ በእነዚህ መርሆአዊ/Principle/ ባልሆኑ በስምምነት ሊቃለሉ በሚችሉ ጥቃቅን ጉዳዮች ምክንያት የህዝብ መብት የሚጻረሩ ኦሮሞ የሆኑ ሃበሻ ወገኞች ‹‹እኔም ኦሮሞ ነኝ›› አስቂኝ ነገር ነው፡፡ አሁን ነው በደንብ የበራልኝ አለ ይባላል እብድ የራሱን ቤት በእሳት አጋይቶ፡፡/እነዚህ ኦሮሞ ነኝ በዮችና የኦሮሞን ህዝብ ተፈጥታዊ የነጻነት ጥያቄ ለመበረዝ ወይም ለማኮለሸት የሚያደርጉት እንቅስቃሤ ከእብዱ ያልተሸለ ስራን እየሰሩ መሆናቸውን ማወቅ ይገባቸዋል፡፡/

ዛሮም እነደ አንድ ወቅት የሃበሻና ኦሮሞ የሆኑ ጸሃፍት በተደጋጋሚ የሚያነሱት ‹‹ ከምንሊክ አስከሬንና ሃውልት ጋር በሃሳብ መታገል ወይም የጎበናን የሙት መንፈስ በማሳደድ የዛሬ ኦሮሞዎች የሚያገኙት አንዳች ጥቅም የለም›› እያሉ ሊሰብኩን ያስባሉ፡፡ የኦሮሞን (በራሳቸው አባባል) ‹‹ነጻ ሪብሊካዊ መንግስት›› አስፈላጊነት በድንበሮች ጉዳይ ውድቅ ያደረጉት ምሁር ተብዬዎቻችን ቀጥለው የሚሉት ምን ሊሆን እነደሚችል የማያውቅ ቢኖርደደብ ብቻ ነው፡፡ እነሱ የሚሉት የምኒሊክ አስከሬን በሰላም ይረፍ፡፡ ሃውልታቸው ለዝነተ አለም የሚኖር የብረት ምሰሶ ይሁን፤ /የአኖሌ ሃውልት ፍረስ/፡፡ የጎበናም የሙት መንፈስ ከአሳዳጆቹ እጅ ያምልጥ፤ ይዳን፡፡/ በጣም ደም የሚያፈላው ግን በጣልያን የአምስት አመት ቆይታ ተጨፈጨፉ ለሚሉት ወገኞቻቸው በመሃል ፊንፊኔ ሃውልት አቁመው የሚሰግዱለት ሀበሾች፤ አንድ መቶ ሃያ አምስት አመታት ቅኝ የገዙት ህዝብ የጨፈጨፉበት በአርሲ ላይ ያቆመውን የአኖሌ የመታሰቢያ ሃውልት ይቃወሙታል፡፡ በመሃል ፊንፊኔ የተገተረው የሚኒሊክ ሃውልት ለኦሮሞው ህዝብ ምኑ ነው? የደጎል አደባባይ የአጼ ቴዎድሮስ መድፍ ሀውልት ምን ይሰራል? አጼው እራሳቸው ከሞት ቢነሱ ይህን ዲንጋይ ለማስመለስ የሚሟገቱ ይመስለኛል፡፡ የአጼ ቴዎድሮስ ኦሮምያን እነደ ኢትዮጵያ አስበዋት ስለማያውቁ፡፡ ለኦሮሞ ህዝብ የምንሊክ ሃውልት በመሃል አዲስ አበባ መመልከትና ምንም ቅር አለመሰኘት የአንድ እስራኤላዊን የናዚ ሃውልት በእየሩሳሌም ማስተከል ነው፡፡ ሁለቱም የጨፈጨፉት ህዝብ ነውና፡፡ ለተጨፈጨፉት የተተከለውን የአኖሌ መታሰቢያ በመቃወም ለጨፍጫፊዎች የተተከለውን የምኒሊክ ሃውልት ማሞገስ ምን የሚሉት በሽታ እነደሆነ መገመት ያስቸግራል፡፡ በተለይ ለኦሮሞ አድርባዮች/

ይህ ሁሉ አያጣላም፡፡ ኦሮሞ በመካከሉ በመንፈስ ሙተው በስጋ ብቻ የሚንቀሳቀሱ የተማሩ ‹‹ማይማኑን›› መታገሉን ትቶ የሙታን መንፈስ ወይም ሃውልት ዘንድ ምን ወሰደው? ኦሮሞን ከሞቱት ይበልጥ በሞቱት ስም የሚናገሩ፤ በሙታን የጥንት ስራ የሚያመልኩ፤ የጨቋኞች ታሪክ ጥብቅና የቆሞ አሳዛኝ ህያውን ናቸው በማስቸገር ላይ ያሉት፡፡ ህያውያን የሙታን ጠበቆች/ ኦፒደኦ በመባል ይታወቃሉ/፡፡ የዛሮዎቹ የሃበሻ ገዢ መደብ ርዝራዦች ያለፈውን የወረራ የጭቆና የዘረፋ ታሪክ ከአስከሬን ከሃውልትና ከሙት መንፈስና እያገናኙ እነዳናነሳው ያስፈራሩናል፡፡ ያስጠነቅቁናል፡፡ አትናገሩ ወይም አትጻፉ ይሉናል፡፡ ታሪክ ማስታወስ ለምን አይገባም? ታሪክ የሚነሳው ለትናንቱ ብቻ አይደለም፡፡ ታሪክ ካልተነሳ ሰው ከታሪክ የሚማረው እንዴት ነው? የዛሬዎቹ ምንሊክና ጎበናዎች/ወያኔና ኦፒዲኦ/ ትምህርት የሚያገኙት አንዴት ነው? ትናንት በህዝባችን ላይ የተፈጸመው በደል የዋዛና ቀልድ አልነበረም፡፡ ታሪክ አታንሱ የማለት ያህል ቀላል አልነበረም፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ደም የፈሰሰበት ሕይወት የጠፋበት፤ ነጻነት የታጣበት ባርነት የተጀመረበት ነበር፡፡ /ይህ ባርነትና እንግልት ከምንጊዜውም በበለጠ እቀጠለ ባለበት ሁኔታ ይገኛል/

በዛሬው ጊዜ አለምን እያናወጠት ያለው ለብዙ አመታት በመደብ ተዎሪ ስር ተቀብሮ እነዲቆ የተደረገው የህዝቦች ብሄራዊ ስሜት ነው፡፡ ሀበሾች/ወያኔዎች የኦሮሜያን ህዝብ ጥያቄ አፍነው ለማስቀረት ይፈልጋሉ፡፡ ጥያቄው የተመለሰለትና ያለቀለትም ጉዳይ አድርገው ያቀርባሉ፡፡/ይህን ለመለፈፍ የሚዳዳቸው የኦሮሞ ምሁራንና፤ ደንቆሮዎችም ብቅ ጥልቅ ይላሉ፡፡/ ሖኖም የህዝቡ ጥያቄ መፈታት ያለበት በራሱ በህዝቡና ህዝቡም በሚፈልገው መንገድ መሆን ይኖርበታል፡፡ የጥያቄው አፈታት ሌሎች በሚፈልጉት መንገድ ከሆነ ትግሉ መቀጠሉ አይቀርም፡፡/ ለዚህም ነው ወያኔ መብትህን እኔ በፈለግሁት በኩል አስመልሼለሃለው ብላ ልታታልለው ብትሞክር ሳይቀበል ቀርቶ ትግሉን እዚህ ደረጃ ደረሰው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ነጻነቱን ለማግኘት የትግል አማራጩን መምረጥ የራሱና የራሱ ብቻ ማድረግ አለበት፡፡ የሊበን ዋቆንም አማራጭ መክሮ ያዋጣል አያዋጣም ማለት ራሱና የራሱ ብቻ እንጂ ሌሎች ሊገመግሙለት አይገባም፡፡ የነሱን ምክርና የነጻ ማውጣት አጀንዳ የት እንደደረሰው ከኦፒዲኦ ተሞክሮ ተረድቶታልና፡፡/

እርግጥ ነው ማንም ህዝብ የራሱን እድል ሌላው ወገን ደስ ባለው ይወስንልኝ አይልም፡፡ ህጻን ልጅ፤ የጃጀች አሮጊት፤ እብድ ሰው ወይም የታወቀ ጅላጅል ማንም ይህንን ውሳኔ አይቀበልም፡፡ እነዲደርስበትም አይፈልግም/እነ አባ ደላ ካልመሩት በስተቀር/

በዛሬው የሞቲ ብያን አፋልጉን-ከመጽሃፋቸው-ከኦሮሚን በፈረቃ የተወሰደና ከጊዜው ሁኔታ ጋር በማጣታም ቀርቧል፡፡ በሚቀጥለው ሳምነት እንገናኝ

 

በፊንፊኔ ኦሮሞዎች ላይ እደረሰ ያለው በደል ከማንኛውም በኦሮምያ ውስጥ ካሉት ያልተናነሰ ቢሆንም፤ በአዲሳባ ነዋሪነቴ በወል ታቅዶ የደረሰብንን ስውር ሳይሆን የተቀነባበረ ደባ ከእለታት አንድ ቀን ወያኔንና ግብረአበሮቹን ለመፋረድ ያበቃናል ብዬ አስባለሁ፡፡

በፊንፊኔ ነዋሪ ኦሮሞዎች ላይ ነጣጠረ ደባ፡፡

በፊንፊኔ አደግና ነዋሪ የሆነ ኦሮሞ ወይም በገጠር ተወልዶና አድጎ አዲስ አበባ ንሮን የመሰረተ በተለይ ከሌላ ብሄረሰብ የተጋባ ኦሮሞ ላይ የተከናወነውን ደባ በጥቂቱ ለመተንነተን እሞክራለሁ፡፡ እኔም አንዱ ስለሆንኩና በደሉ በቀጥታ ስለሚመለከተኝ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው የታዘብኩትን ለመተንተን እሞክራለሁ፡፡

ጊዜው 1992 . ጀምሮ በአዲስ አበባ ውስጥ የኦሮሞነት ስሜት እየዳበረና እያበበ የመጣበት ወቅት ነበር፡፡ ኦነግ እንደ መንግስት መሪነት ነጻ ሆኖ ከመሰሪ ከከሃዲ ወያኖዎች ጋር የኔው ቶም ጄሪን አምኖ በጀርባው ተንጋሎ የተኛበት ወቅት ነው፡፡ የመሰባሰቢያ ቦታችንን ጉለሌ ገልማ ቱፋ አድርገን በየሳምነቱ እየተገናኘን የባህል ሙዚቃዎችን ሃገርኛ ወለሎዎችን የምነኮሞክምበት ወቅት ነበር፡፡ ሳምንቱ እስኪመጣ የናፈቅንበት፡ ልጆቻችን የአባቶቻቸውና የእናቶቻቸው ባህል ምን እንደሆነ ሊረዱ የሚችሉበት አጋጣሚ የተፈጠረ መስሎን የፈነደቅንበት ወቅት፡ ታወሰኝ! የአዲስ አበባ ኦሮሞ ነብስ ያላወቀ እምቦቃቅላ ልጁን ጉለሌ አመቺሳ የሚስደርግ ይመስል ፤በቤተሰብ ደረጃ አቅፈን ተንጋግተን ትኬት ለመግዛት የተሰለፍንበት፡፡ ኦሮሙማ እጅግ በመጠቀ ፍጥነት ወዳ ከፍተኛ ደረጃ ሊሸጋገር የተነሳበት እተንደረደረ፤ የአዲሳባው ኦሮሞ እምኖረው ፊንፊኔ ነው ብሎ መናገር የደፈረበት፤ ፊንፊኔ ከተራ የምግብ ቤት ስምነት ወጥታ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስም ልትሆን የታጨችበት ጊዜ ነበር፡፡ በዚን ወቅት ዘመናዊ ተብዬውን አለባበስ ለብሰን በማንኛውም ቦታ በኦሮምኛ መናገር ደፍረን ስነልቦናችን ላይ ያጠላው አይነጥላ የተገፈፈለት ያልመሰለው ኦሮሞ አልነበረም፡፡ ሰዉም ተቀብሎን ሱፍ ለብሶ ኦሮምኛ የሚናገርን ኦሮሞ ፈገግ በሎ ማየት ጀምሮ ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ልጃገረድ ጠበሳን በኦሮምኛ መሞከር የሚያስቀጣ መስል ኦሮሞ ለኦሮሞ የፍቅር ጨዋታ በተብታባው በአማርኛ መሆኑ ቀርቶ አፍ በፈታንበት ቋንቋ ሆኖ ነበር፡፡ ፍቅር ባፍ መፍቻ ቋንቋ መጣፈጡን የተረዳነው በዚን ጊዜ ነበር፡፡

ሙዚቃ ባህልን ተከትሎ ይሄዳል ወይስ ባህል ሙዚቃን? እንጃ! ብቻ በዚኑ ወቅት በጣም የሚጣፍጡ ኦሮሞነትን የሚያጎለብቱ ማንነትን የሚያዳብሩ ሙዚቃዎች እነደአሸን ፈሉ፡፡ በኦሮምኛ ቋንቋ የሚተላለፍ የኦሮምኛ ሬዲዮ የኦነግን ፕሮግራም ከማስተዋወቁም በላይ በኦሮሞ ታሪክና ባህል ዙሪያ ያስተላልፍ የነበረው መልእክት አሁን ላለንበት የእኔነት መሰረት ሁነዋል፡፡ የባህል እድገቱ መነሳሳት የባህል ልብስ ቤቶችና የሙዚቃ ቤቶችን መስፋፋት በማምጠቱ በፊንፊኔ የተለያ ቦታዎች የኦሮሞ ባህል ልብሶችን ሰቅለው የሚሸጡ ሱቆች ተበራከቱ፡፡ የሽሮ ሜዳ ሸማኔ እነኳን ፍላጎትን መከተል ጀመረ፡፡

በአዲስ አበባ ልጆቻቸውን ወልደው ያሳደጉና በመጤው ባህል ልጆቻቸው የተለከፋባቸው ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ለማስተማርና እነሱም ቁቤን ለመማር ያላቸውን ከፍተና ፍለጎት የሚሳኩበት ትምህርት ቤቶች በየቦታው በሚገኙ አንደኛና የከፍተኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ እነደ አሸን በመፍላታቸው አሮሞው ከስራ ሲወጣ ይህችን ማንነቱንና ቋንቋውን ወደሚማርበት ትምህርት ቤት መትመሙን ተያዘው፡ እኔም አንዱ ነበርኩ፡ አንድ ወንድሜን አስከትዬ ከረባቴን አውልቄ አበጨዳን ማጨዱን ተያያዝኩ፡፡ የነበረንን ስሜት ማስረዳት አልችልም፡፡ ጠእሙ ግን በተለይ ኦሮሞ ለሆነ ማስረዳት ይዳግታል፡፡ የኛም ቋንቋ ወረቀት ላይ አርፋ መናገርዋን ያላመኑትን አዛውንት አስታውሳቸዋለሁ፡፡

ከላይ የገለጽኩዋቸው ሁሉ ኦነግ በምክር ቤቱ ከወያኔ ጋር እሰጣ እገባውን እያከሄደ በህዝብ ውስጥ በተፈጠረው የመንፈስ ኩራትና የስነ ልቡና ነጻነት የመነጩ እናም እኩል ኢትዮፕያዊ ነን የሚል ኩራትን በአዲስ አቤው ኦሮሞ ላይ የፈጠሩ ወቅቶች ናቸው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ ወደ በተክርስቲን ሳይሆን በሰንበት ወደ ጉለሌ ለመሄድ ሽር ጉድ ያለበት ወቅት፡፡

ይህ ተሙቆ እነደተሞላልን በሰወነታችን ውስጥ ግለቱን እየጨመረ የመጣ ስሜት ግን እነደ ጀመረው አልቀጠለም፡፡ ወያኔ የኦሮሞውን ህዝብ ለኦነግ ያለውን ተአማኝነትና፤ ለወደፊትም የስልጣን ባላንጣነት አልጣማትም፡፡ ከበፊቱም አይጥና ድመት የነበሩት ኦነግና ወያኔ በሸፍጥ ተጠናቀቀ፡፡ የጋለው የአዲሳቤ ኦሮሞ የማንነት፤ ኦሮሞማ ስሜትን ለማርገብ ቀጥተኛ የሆነ የተግባር መርሃ ግብር ተነድፎ መተግበር ነበረበት፡፡ ወያኔ ይህን ለማድረግ በንጉሱ ዘመን አክሊሉ ሃብተወልድ እንደ ማእበል ይውጠናል ብለው የፈሩትን የኦሮሞ ህዝብ በተለይ በአዲስ አበባ ማስተማር አደገኛ መሆኑን ተረዳች፡፡ ስለዚህ ኦነግ ከምክር ቤቱ በወጣ በማግስቱ ኦሮምኛ ያስተምሩ የነበሩትን መምህራን በሙሉ ከኦነግ ጋር ያበሩ ናቸው ብላ አሰረች፡፡ ዋናው አላማ ግን በፊንፊኔ እየጎለበተ የመጣውን ጠንካራ የኦሮሞ ብሄርተኝነትን ከስሩ መንቅሎ መጣል ነበር፡፡ በጣም የማልረሳውና በወቅቱ በኦፒዲኦ አባላት ምንም ተቃውሞ አለመቅረቡ ሲሆን የኦሮሞን ቋንቋና ማንነትና ታሪክ የታሰሩትን መምህራን ተክቶ አለማስተማር በዚህ በአዲስ አበባ ነዋሪ ኦሮሞዎች ላይ በደረሰ በደል ግንባር ቀደም ተጠያቂ ደርጋቸዋል፡፡ እኔና ወንድሜም የጀመርነው በራሳችን ቋንቋ መማርና የባህላችንን የማወቅ ትግል በወያኔ ተጨናገፈ፡፡
ይቀጥላል

Dhaamsa Gulalaa:

Mooti Biyya deebiye akkan hoji bareesuti debiyuun barbada, akkan du’aa irra hafuuf fi mana hidhati ba’uu ilee namoon akka naf gargaran caaraaqan ture, kitaabi Mootii biyya akka deeye maxanfamu iyaachan jira hayuun afaan Oromoo akka Beekan Gulumma Irrana faa amoo utuu Afaan Oromooti jijiran Dhaalooti qube Kitaaba kana dubse nati tola.

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved