Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

 

ለኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶች

ለኦሮሞ ወጣቶች (Kai Qeerroo)

ለኦሮሞ ሚዲያዎች በያሉበት ።

January 1 /2016 ዓም

ጉዳዩ ፡ ለወገን የቀረበ የኡኡታ ጥሪ !

- ይህ ብሶት የወለደው ፤ ሲቃ የተናነቀው ጩሀት ነው ፤

-ጥሪው የቀረበው ለኦሮሞ ነው ፤

-ለጥሪው አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት መብትና ሃላፊነቱ የኦሮሞ ህዝብ ነው !!

ዓላማው ፡

ከሩቅ እስከ ደጃችን ድረስ በጉልበቱ ዘልቆ መጥቶ በግፍ ወረራ ሀገር የወሰደብን ፤ ቄያችንን ነጥቆና የዜግነት መብታችንን ገፎ መሬትና ሀገር እየሸጠ ትውልድን በመፍጀት ላይ ያለውን ወሮበላ የትግሬ ሽፍታ ጥርቅም በጋራ ደምስሰን ሰላም ፤ነጻነት እና እኩልነት የሰፈነባትን ዲሞክራሲያዊት የሆነች የሁላችን ሀገር ለመፍጠር በአረመኔው የንጹሃን ደም አፍሳሽና ነፍሰ-ገዳይ ወሮበላ የትግሬ አገዛዝ ሥር ያሉትን ዜጎቻችንና ሀገራችንን እንታደግ የሚል ጥሪ ለማስተላለፍ ነው ።

በአሁኑ ሰዓት ሁላችንም የኦሮሞ ተወላጆች ከምንጊዜውም የበለጠ እጅግ ከባድ ፈተና የሆነ አጣብቂኝና አንገብጋቢ ችግር ውስጥ መሆናችን እሙን ነው ። በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ አረመኔና ክፉ እርጉም ባላንጣ ገጥሞናል ። ዘረኛውና ጠባብ ጎጠኛው የትግሬ ቅኝ ገዢ ወሮበላ መንግስት የዘር ማጥፋት (genocide ) ጦርነት ዘመቻ አውጆብናል ፤ ቄያችንን በጠመንጃ ሃይል ወስደውብናል ፤ መሬትና ሀገር አልባ አድርጎናል ፤ ለቀረበለት የመብትና ፍትሃዊ የሆነ ሰላማዊ ጥያቄ መልሱ ጥይትና ቦንብ ሆኖ ህዝባችንን በአደባባይ ፤በየቤታቸው ደጃፍ ፤ በየትምህርት ገበታቸውውና በየሥራ መስኩ እየረሽነ ነው ፤ ከዚም የከፋ እርምጃን ለመውሰድ ዘመቻው በሰፊው ቀጥሏል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሀገር ቤትም ሆነ በውጪው ዓለም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞም ሆነ የሌሎች ፖለቲካ ፓርቲዎች ( ድርጅቶች ) የቱንም ያህል ለህዝብ መብትና ነጻነት ፤ ለሀገር ሉዓላዊነት መጠበቅና ለዲሞክራሲ ሥርዓት መስፈን በየአቅጣጫው ደፋ ቀና እያሉ ቢሆንም አንድ የጋራ ጠላት እያላቸው ሃይላቸውን አቀናጅተው ህዝቡን ለዚያ ለታቀደ አንድ ወጥ ዓላማ አስተባብረው መርተውና ገርተው ውጤት ያለው ሥራ በመስራት የጋራ ጠላታቸውን ሊያስወግዱ ቀርቶ ጠላትን የሚያቆስል ( የሚያደማ )ተግባር ማከናወን ጨርሶ አልቻሉም ።

በመሆኑም አሁን ከተጋረጠብን ፈተና እና ከገጠመን መሰሪ የወንበዴዎች ሴራ አኳያ ባለፈ ነገር ፤ በከረመ ስህተት ፤ በድሮ ታሪክ እንደገና ወደ ኋላ ተመልሰን ማንንም ተወቃሽ ፤ ማንንም የሚከሰስ ወንጀለኛ ለማድረግ ጊዜ የለንም ፤ ሁኔታውም አይፈቅድልንም ፤ መወቃቀስና መወነጃጀል ብሎም አንዱ ሌላውን ለማማት ( ለማጥላላት ) ለጠላት ጊዜ ለመሸመትና ይበልጥ ትውልዳችን እርስ-በርሱ እንዲፈጅ ካልሆነ በስተቀር ለማናችንም አይበጀንም ። pg. 2

ስለዚህ ለጊዜው ልዩነቶቻችንን አቻችለን ፤ ተከበባብረንና በመደማማመጥ ተቻችለን እጅ ለእጅ በመያያዝ ተጋግዘን የገጠሙንን ችግሮች አስወግደን ይህንን እርኩስ አረመኔ ባላንጣ ( ጠላት ) በጋራ ተረባርበን በአጭር ጊዜ ውስጥ ካላስወገድነው ከዚህ ካሁኑ እጅግ የከፋ ውርደትና ባሪነት ብሎም ከፍተኛ እልቂት በትውልዳችን ፊት ተደቅነዋል ።

እስካሁን እንዳየነው ከሀገራችን እየተሰደድን ነው ፤ ከመሬታችን ፤ ከቄያችን በቅሌት እየተፈናቀልን ነው ፤ ከትምህርት ገበታና ከሥራ እየተባረርን ነው ፤ እሱም አልበቃ ብሎ ህዝብ እያለቀ ነው ፤ ንጹሃን ዜጎቻችን (ዘሮቻችን ) በየሜዳውና በየጥሻው እጃቸው ታስሮ ፤ ልብሳቸውን አስወልቀው እርቃናቸውን ዓይናቸው እንደ ታሰረ ማንነታቸውን ለይቶ አስከሬናቸውን መቅበር እንዳይቻል ብርቅዬ ወጣቶቻችንን ጭንቅላት በጥይት በታትነው ሌሎችን ደግሞ በጫካ ውስጥ በዛፍ ላይ አንጠልጥለው ከገደሏቸው ( ከፈጇቸው ) በኋላ በድናቸውን አውሬ እንዲበላ ደማቸውን ውሻ እንዲልሰው ተደርገዋል ። ይህ ኢሰበአዊነት የጎደለው የመጨረሻው ጭካኔና አረመኔነት ነው ።

ይህንኑ ዓይነት ቀጣይ ዘመቻ በስፋት ቀጥለው የኦሮሞ ማህበረሰብ በሚኖሩባቸው ክልል ፤ የገጠር ቀበሌና ከተማ ውስጥ ገብተው እያሰሱ ፤ በየትምህርት ቤትና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እየገቡ በእሳት ፤ በጥይትና በቦንብ ጭምር የነገ ሀገር ተስፋ ወጣቶችን በጅምላ እየፈጁ ሲሆን ብብዙ ሺዎች የሚቆጠሩትን ደግሞ የታሰሩበት እስር ቤት እንኳ ሳይታወቅ በያሉበት ታጉረው እንደ እባብ እየተቀጠቀጡ በአረመኔዎች ሲሰሰቃዩ ፤ ሌሎች ደግሞ ማንም እንዳያያቸው ተገለው በየጥሻውና በየጉራንጉሩ እንደ አይጥ እየተጣሉ ናቸው ።

የሚደንቀውና እጅግ በጣም የሚያሳዝነው “ የፈጣሪ አምላክን ፈቃድ ሃሳብና ዓላማ በትውልድ መካከል ለማስፈጸም በግዚአብሔር ተመርጠን የተላክን የጌታ መልክተኛ ፤ ህዝበ-እግዚአብሔርንና ሀገርን የሚናገለግል ፤ ቤተእምነትን የምንመራ መንፈሳዊ አባቶች ( አማኞች ) ነን “ ብለው ራሳቸውን የሚጠሩቱ የህዝብና የፈጣሪ አምላክ ካህናት የተባሉት መንፈሳዊ መሪዎች የሰዎች ሰብዓዊ ክብር ሲገፈፍ ፤ የንጹሃን ደም አለአግባብ በከንቱ ሲፈስ ፤ መብትና ነጻነታቸው ተረግጦ ፤ የዜግነት ህገመንግስታዊና ሰባአዊ መብቱ ተገፎ እንዲህ ዓይነቱ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሀገሪቷ ዜጎች ላይ በጅምላ ሲፈጸም እውነትን በመከተል ፤ ህገመንግስታዊ መብታቸውን በመንተራስ ፤ ቃለ-እግዚአብሔርን በመጥቀስ ለህዝብ ህይወትና ለሀገር ጸጥታ መታወክ ፤ለትውልድ መብት መደፈር እና መጨቆን ጣልቃ ገብተው እልቂቱን ለማስቆም አንዲት ቃል እንኳን አለመተንፈሳቸው ፤ ብቅ አለማለታቸው አሳፋሪና አሳዛኝ ትዝብት ነው ::

ይህ አልበቃ ብሎ አንዳንድ በ3 ቢላዋ የሚበሉ የወያኔ ባንዳና አሽከር የሆኑ የውስጥ አርበኛ የቤተ-እምነት መሪ እና አገልጋይ ቄስ (ፓስተር) ነን ባዮች ከሰሞኑ “ የእርቅ ፤ የፍትህና የሰላም ጉባኤ ጥሪ “ በሚል ሀገር አቀፍ መንፈሳዊ ክሩሴድ ጠርተው በእግዚአብሔር ስም ህዝቡን አደናግረውና አወናብደው ፤ በፈጣሪና በራሱ በህዝቡ እየነገዱ ፤ ኪሳቸውን ሊያደልቡና ለወያኔ ደግሞ ጊዜን በመሸመት ትውልድ ተባብሮ ስለ መብትና ነጻነቱ በግራ ታግሎ ነፍሰ-ገዳይ የጫካ ሽፍቶችን በማስወገድ እውነተኛ የሆነ ዘላቂ ሰላምና ነጻነት እንዳያገኝ ልጆቻችንን አዘናግተው ሊያሳርዱ 4ኛ ቢላዋ እየሳሉ ወዲያና ውዲህ ሽር ጉድ እያሉ ናቸው ።

በሌላ በኩል እንዲህ ዓይነቱ ጭካኔና ግድየለሽ ደንታቢስነት ለኛ ለኦሮሞዎች ግልጽ የሆነ መልክት ነው ። ይህ በትውልድ ላይ የተቃጣው አደጋ በኛና በኛ ብቻ ነው ሊገታ የሚችለው ። ኦሮሞ ከእግዚአብሔርና pg. 3

ከራሱ ከኦሮሞ ሌላ ወዳጅ የላውም ፤ ኖሮትም አያውቅም ፤ በሌላ ጊዜ “ከጎናችሁ ነን ፤ ተጋብተናል ፤ ተዋልደናል ፤ አብሬን አድገን አብሬን ሰርተን አብረን ኖረናል “ ይሉን የነበሩት እንኳ ቢኖሩ ካንገት በላይ የይስሙላ የሆነ ሌላ ተንኮልና ታኮ ከኋላ አዘጋጅተው በዓይነ ቁረኛ እየተመለከቱን የአዞ እንባ የሚያነቡ ስለመሆናቸው መዘንጋት አያሻም።

“ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው “ እንደሚባለው ተረት ስለ አኦሮሞ መብት መረገጥ ፤ነጻነት መገፈፍ ጉዳይ ተገንዝቦ ነጻ ስለመውጣቱ ፤ ግፍ ለዘመናት የተፈራረቀበት የጭቆናው ገፈት ቀማሽ ከሆነው ከራሱ ከኦሮሞ ህዝብ በስተቀር ማንም ክብደት ስለማይሰጥ “የአኦሮሞ ነጻ መውጣት ተገቢና ፍትሃዊ ነው “ብሎ የሚደግፍ ሌላ አካል አለመኖሩ ሊያስደንቀን አይገባም ። ምክንያቱም የኛ ጉዳይ በእኛው እጅና ትከሻ ላይ የወደቀ ስለሆነ ችግራችንን የሚንፈታው ፤ መብታችንን የሚናስከብረው ፤ ነጻነታችንን የሚናረጋግጠው እኛው ብቻ መሆናችን ይበልጥ ግልጽ ሆኖልናል ።

እኔ በበኩሌ “ ይህ ይደረግ ፤ እንዲህና እንዲያ ይሁን “ ወዘተ.. በማለት መመሪያ ለማመንጨት ወይም ለእያንዳንዱ ኦሮሞ ወገኔ ትእዛዝ ለማስተላለፍ ልዩ ችሎታና ብቃት (ሥልጣን ) የለኝም ።ቢሆንም ሀገሬ በጠላት ተወሮ ፤ የዘመዶቼና ዘርንማንዘሮቼ ርስት ተሽጦ ፤ ቄያቸው ስፈራርስ ( በባዕድ ሲወረስ )፤ ህዝቤ ክኖረበት መንደሩ በጠመንጃ አፈሙዝ ተገዶ እየተፈናቀለ የትም በየሜዳው ተበትኖ የሰው አሽከርና ገረድ ሲሆን ፤ ከፊሉ ጎዳና ተዳዳሪ ሲሆን ፤ ህጻናት ፤ ወጣቶች ፤እናቶች ፤አቅመ ደካማ አሮጊቶች ፤ አዛውንቶች ፤ ጎልማሶችና ምስኪን ገበሬዎች ባለቤትና ሰሚ ዳኛ አጥተው በጥይት አናታቸው ሲበሳሳ ፤ ደማቸው በከንቱ ሲፈስ ፤ የብዙዎች ህይወት እንደ ቅጠል በጥይት ስረግፍ ፤ ቆሜ እያየሁና እየሰማሁ ለአንዲት ደቂቃና ሰኮንድ በመታገስ ራሴን መቆጣጠር ስላቃተኝ የውስጤን ጭንቀትና ንዴት ተንፍሼ ፤ በውስጤ የሚመላለሰውን ሃሳብ እና ፊላጎት ገልጬ ሸክሜንና ጥያቄዬን ለናንተ ለኦሮሞ ተወላጆች ብገልጽ ከኔ የተሻለ ክብደት ሰጥተው ፤እውቀት ፤ ልምድና ችሎታቸውን ተጠቅመው ትውልድን እንደገና በየደረጃው ቀስቅሰውና አዋቅረው በማደራጀት ታክቲክና ስትራቴጂ ነድፈው ሁሉንም ኦሮሞ ተወላጅ አንድ ወጥ በሆነው ማዕከላዊ አመራር ስር በማስተባበር ትውልድን የሚመሩ ፤ የሚቆጣጠሩ ብቁ ሰዎች በኛም መካከል እንደሚኖሩ እርግጠኛ በመሆን ቅንነቴና የማየው ከልክ ያለፈ ግፍና በደል አንገብግቦኝ በተቆርቋሪነቴ ያመነጨሁት በጎ ሃሳብ እንደሆነ ተደርጎ እንዲወሰድልኝ በቅድሚያ ለማሳሰብ እውዳለሁ ።

ስለ ማንነቴ ( ምንነቴ ) ለማወቅ ምናልባት ጥያቄ የሚያነሱ ቢኖሩ እኔ ፖለቲከኛና የፖለቲካ ተንታኝ አይደለሁም ፤ የታሪክ ተመራማሪና ጸሐፊ ፤ ወይም የጦር መሪ ( የጦርነት መሃንዲስ ) አይደለሁም ።ዜና ዘጋቢና ጋዜጠኛ ሆኜም አላውቅም ፤ ነገር ግን ባጭሩ የኦሮሞነቴ ( ኦሮሞ ሆኜ በመፈጠሬ ) ወይም ሰው በመሆኔ የውስጤ ስሜት የፈጠረብኝ ፤ ንዴት ያንገበበኝ ቁጭት ማንነቴን የተፈታተነኝ ፤ የኦሮሞነቴ ታሪካዊ ሃላፊነትና ግዴታ የወደቀብኝ አንድ ተራ ግለሰብ እንጂ ከሌላው ሰው የተለየ አቅምና ችሎታ የለኝም ።

ኦሮሞ ማን ነው ?

ኦሮሞ እንደ ማንኛውም የዓለምና የአካባቢው ህብረተሰብ አካል ሆኖ እሱም በሀገሩ (በኦሮሚያ መሬት ) ፤ በመንደሩ ፤ በሰፈሩ ፡ በቄዬውና በርስቱ ላይ ባለቤት እንዲሆን በተፈጠሮ ያገኘውን ዕድል ተጠቅሞ በሰላምና በነጻነት እንዲኖር ከአምላኩ በተሰጠው መብት መሰረት በየለበት የሚኖር መልካም ፤ ቅንና ደግ የሆነ ሰፊ ባህልና ጥንታዊ ታሪክ ያለው ጀግና ህዝብ ነው። pg. 4

ከፈጣሪ አምላኩ በሆነለት ዕድልና ስጦታ ዘርንማንዘሩ ሁሉ ለዘመናት የተከተሉትን ባህል ፤ የነበራቸውን ታሪክ አስጥሎ ፤ሰርዞና በጠመንጃ አፈሙዝ የራሱን ባዕድ ኮተት በግድ ለማሸከም ሀገርን በማቅናት ሰበብ ፤ በአንድነት ስም ፤ በግዚአብሔር ስም ፤ በአምላክ ፈቃድ የተላኩ የግዚአብሄር መልክተኞች መስለው ቅጥፈትን እየሰበኩ የኦሮሞን ሀገርና ቄዬ በብልጣብልጥነት ቀጣፌዎች በአቋራጭ ተቆጣጠሩት ።

በመቀጠልም በቅንነቱ ተዘናግቶ ፤ በደግነቱ የበሉበትን ወጪት ሰባሪዎች ቅጥፈት ተጭበርብሮ ፤ በአረመኔዎች የመስፋፋት ፖሊሲ ኦሮሞ ባህሉ ፤ እምነቱ ቋንቋው አደጋ ላይ ወደቀ ፤ ታሪኩ ጥላሸት ለብሶ ፤ ቄዬው በወራሪዎች ተወሮ እትብቱ የተቀበረበት ርስቱን ብቻ ሳይሆን ብርቅዬ ጀግኖች ልጆቹ ውድ ህይወታቸውን አጡ፤ ቅርሱና ንብረቱን ሁሉ ተነጠቀ (ተወረሰ) ።

“ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ “ እንደተባለው አንዳንድ የታሪክ አተላዎችና መሰሪዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች የአኦሮሞን ህዝብ “ መጤ “ ነው ለማለት በተደጋጋሚ የቃጡ ቢሆንም ሌላውን ለጊዜው ትተን የአኦሮሞ ህዝብ ከክርስቶስ ልደት በፊት 300 ዓመታት አስቀድሞ የኦሮሞ ማህበረሰብ ይጠቀምበት በነበረው የድንጋይ ውቅር (ጽሑፍ ) መረጃ መሰረት ራሳቸው ኦሮሞዎች የፈጠሩትን የቀን መቁጠሪያን ጨምሮ የነሱ ብቻ የሆነ ታሪክ ፤ እምነት ፤ ባህል ፤ ልማድና መኖሪያ ስፍራ እንደ ነበራቸው የሚጠቁሙ መረጃዎች በተለያየ የምስራቅ አፍሪካ ቦታዎች ( በተለይም በኬኒያ ፤ በሐረርጌ እንዲሁም በልዩ ልዩ የዛሬ ኦሮሚያ ክልል ዋሻዎችና ጫካዎች ) ውስጥ የተገኙ መረጃዎች ማህበረሳባችን ለረጅም ዘመናት የራሱ መሬት ባለቤት ብቻ ሳይሆን ከጥንት አንስቶ የጥበብ ተጠቃሚ ሆኖ የኖረ ጥንታዊ ህዝብ እንደ ነበር የሚያመላክቱ ሃቆች አሉ ።

በእምነት በኩልም ቢሆን የኦሮሞ ህዝብ የማንነቱ መነሻና መገለጫ የሆነው አንድ አምላክ (ዋቃ ) ፤ አንድ ሃይማኖት ፤ (ዋቄፋና) ፤ አንድ ቋንቋ ( አፋን አኦሮሞ ወይም ኦሮሚፋ ) ፤ አንድ ዲሞክራሲያዊ የአኗኗር ስርዓት ( ጋዳ ) ፤ አንድ ታሪክ ፤ አንድ ባህል ፤ አንድ ትውፊት ሲጋራ የኖረ ጥንታዊ ህዝብ ነው ።

ለምሳሌ በሁሉም ኦሮሞዎች ዘንድ የቦታ ርቀትና መልካ ምድራዊ አቀማመት ሳይገድበው በየአካባቢው ሁሉ ኦሮሞን ኦሮሞ ፤ አሮሙማ ፤ ጋዳ ፤ አባጋዳ ፤ ዋቃ ፤ ዋቄፋና ፤ አባሙዳ ፤ ጫፌ ፤ ኦዳ ካላቻ ፤ ቦኩ ጫጩ፤ ቡና ቃላ ፤ ስቄ ፤ እሬቻ .. ወዘተ የሚባኡት የእምነትና የአስተዳደር ስሞች የኦሮሞን የዘር ግንድ ትስስርና የአንድ ጎሳ መነሻ ምክንያቶች ምንነቱን አመልካች ማስረጃዎች ናቸው ።

ከላይ እንደተገለጸው ከጥንት ጀምሮ የኦሮሞ እምነት “ዋቄፋና “ ነው። ትርጉሙም “ዋቃ “ፈጣሪ አምላክ (እግዚአብሔር ) ማለት ሲሆን ይህንን ፈጣሪ አምላክ የማመኑ (የመከተሉ) ህደት ፤ ማለትም የአምልኮና የምስጋና ስርዓት አፈጻጸም ደግሞ “ ዋቄፈና “ ይባላል ። ዋቄፋና ምስጋናን ለፈጣሪ አምላክ (ዋቃ) ማቅረብ (መጸለይ) ሲሆን የአምልኮው ሥነስርዓት ደግሞ “እሬቻ “ በመባል ይታወቃል ።

የሆነ ሆኖ እነዚያ ከጥንት እስካሁን ኦሮሞን ሰንገው የያዙት ታሪካዊ ጠላቶቻችን ከመንፈሳዊ አባትነት እስከ ዛሬው ምሁሮቻቸው ኦሮሞን “ መጤ “ ፤ እምነቱን ደግሞ የፈጣሪ ፈቃድና ዓላማ (ቃል ) ተቃራኒ (አጋንንታዊ የአምልኮ ስርዓት ) አስመስለው አሳንሰውና አጥላልተው እያንቋሸሹ በቅጥፈት ቢለፍፉም በአፍሪካ ታሪክ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ ከዋቄፋና የአምልኮ ስርዓት በስተቀር መጤ አይደለሁም ሊል የሚችል እምነት ( ሃይማኖት ) ከቶ የለም ። pg. 5

ይህ የኦሮሞዎች እምነት ግን ከጥንት ጀምሮ እዚያው ከኦሮሞዎች ዘንድ አብሮያቸው የኖረ ፤ አሁንም ያለና ወደፊትም ከቶ የማይጠፋ እምነት ነው ።የኦሮም ህዝብ አንድ የዘር ግንድ ትስሥርና የአንድ ጎሳ መነሻ ስም የሆነውን በርካታ ሁኔታዎችን ሲጠቀም የኖረ ፤ አሁንም የሚጠቀምበትን ክልልና የራሱ መሬት ባለቤት የነበረ የራሱ ቄዬ ፤ርስትና ሀገር ኖሮት ለብዙ ሺህ ዘመናት ጸንቶ የኖረ ትልቅ ህዝብ ነው ።

ቀደም ሲል የነበረውን እንኳ ለጊዜው ትተን የቅርቡን ታሪክ ለመጥቀስ ያህል የኦሮሞ ህዝብ ከ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ጀምሮ እስከ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ከሰሜን ወደ መኖሪያው ሸዋ ከፍታማ ቦታዎች ለመስፋፋት በሞከሩት ልዩ ልዩ የሰሜን ወራራሪዎች ጋር በየጊዜው በርካታ ጦርነቶችን በማድረግ በብዙ የሞት ሽረት ክልሉን ( የራሱን መሬት ) በአሸናፊነት ተከላክሎ ማስከበር የቻለ ብርቱና ጀግና ህዝብ ነው ።

በመካከል ( በኋላም ) በተናጠል ሲያቅታቸው በሃይማኖት ሰበብ ጭምር በተለያዩ አቅጣጫ ግንባር ፈጥረው የተለያዩ ቡድኖች ኦሮሞን ቢወጉትም የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጦርነት ቀደም ሲል ከ10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በሸዋ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ይኖሩ በነበሩ የኦሮሞ ጎሳዎችና ወደዚሁ አካባቢ ለመስፋፋት ይሞክሩ በነበሩ ወራሪዎች መካካል ሲደረግ የቆየው ጦርነት ቅጥያ ነበር ።

በዚህ መልክ በተደጋጋሚ የተቃጣበትን የተስፋፊዎችን ጦርነት በድል አሻንፎ የራሱን መሬት ባለቤት መሆን ከመቻሉም በላይ ዋና ተቀናቃኙ የነብረውን የሰሜን ወራሪ ጦር ኋይል መክቶና ሰብሮ ከመሬቱ በማባረር እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ በአባይ ወንዝ ማዶ በመገደብ ከጥንት ጀምሮ የራሱ በሆነው ዋቄፋና እና ከዚሁ በመነጨው የገዳ ሥርዓት እየተመራ የኦሮሞን ጥበብ ፤ ባህል ፤ ወግና ሥርዓት ( ልማድ ) ጠብቆ ለማቆየት የቻለ ሲሆን ነገር ግን ከ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ ጀምሮ በሃይማኖት ሽፋን ( በአኦርቶዶክስ ተወሃዶ ቤተክርስቲያንና ) በክርስቲያናዊው መንግስት የጋራ ህብረት ፤ እንዲሁም በውጪ ሃይሎች እየታገዙ 2ኛው ወራሪ ኋይሎች በብዙ መልኩ ኦሮሞን ለከፍተኛ ጭቆና፤ እልቂት ፤ የመሬት ንጥቂያ በአጠቃላይም ለከባዱ የገባር ሥርዓት ጭሰኝነትና ባርነት ዳርገውት ነበር ። ይህ የዘንድሮው ( የሰሞኑ የትግሬ ወረራ ) የዚያን ጊዜው ቅጥያና ሌላው የጭቆና ገጽታ ነው ።

ታሪክና ጊዜ ፡ታሪክ አፍ አለው ፤ ይናገራል ፤ አካልም ስላለው ቆሞ ሲራመድ ይታያል ።ታሪክ በተጸዕኖና ዘመን ብዛት ከቶ አያረጅም አይጠፋምም ፤ገድለው ብቀብሩትም ፤ ክደው ቢያጣጥሉትም ፤ ንቀው ቢያንቋሽሹትም በቁርጥ ቀን ጀግና ልጆቹ ያልተቋረጠ የዘመናት ትግልና በዘመናዊው የምርምር ዘዴ ጭምር እንደገና ህያው ሆኖ በመቆም ስለ ራሱ የሚናገር አሻራው ጨርሶ የማይጠፋ ማንም የማይረታው የራሱ ጠበቃናምስክርነው ። ታሪክ ምስክርና ዳኛ ሆኖም ሊፈርድብን የሚችል ብቃት አለው።

ጊዜም ቢሆን ስለራሱ ይናገራል ፤እማኝ ሆኖ ይመሰክርብናል። መቼም ቢሆን ማንም መካድ የማይችለው በኦሮሞ ህዝብ ላይ በተለያዩ ዘመናት የተፈጸመ በደም የቀለመውና ሺህዎችን (ሚሊዮኖችን) ህይወት የቀጠፈው ፤ ቋንቋውን ፤ ባህሉን ፤ እምነቱንና ታሪኩን አጥፍቶ የባዕድ ጭቆና ቀንበር የጫነበትን የትናንት ታሪኩ ዛሬም አፍ አውጥቶ ይናገራል ፤ ጣቱን ቀስሮ ይመሰክራል ።

መሰሪዎቹ የቅኝ ገዢ ጠላቶቻችን ቅጥያ መልኩንና ቅርጹን ቀይሮ ፤ ስሙን ለውጦ ፤በጊዜና ዘመናት ብዛት አድብቶና አረሳስቶ እንደገና በሌላ መልክ ከምድር ገጽ ላይ ሊያጠፋን ተጠራርቶ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ፤ አሁን ከሰሞኑም እንኳ ይሀው እየተናነቀን ይገኛል ። ለኔ ግን ይሀኛው እጅግ መራራ ከመሆኑ የተነሳ ከቶ አልዋጥልህ ብሎኝ “ እምቢ ፤ NO “ ከእንግዲህ እኔና ሌሎች የአኦሮሞ ልጆች pg. 6

በህይወት እያለን ፤ በሁለት እግሮቻችን ቆመን በዚህ በኛ ዘመን ያ የቀድሞው ግፍ እንደገና በኔ ህዝብና ትውልድ ላይ ፈጽሞ አይደገምም ፤ “ በቃ “ ልንለው ይገባል እያልኩ ነኝ ።

በከዚህ ቀደሞቹ ወራሪ ገዢዎች አንዳንዴ በሀገር ስም ፤ ሌላ ጊዜ ደግም በፈጣሪ ስም ፤ በሃይማኖት ሰበብ ፤ በባንዲራ እና አንድነት ...ወዘተ የተረት ተረት መሰሪ ምክንያቶች ርስታችንን ነቅለው ጭሰኛ አደረጉን ፤ መብትና ነጻነታችንን ተገፈን ፤ ባህል እምነትና ቋንቋችንም ተንቀው ተጥለው እንዲረሱ የማንቋሸሽ ዘመቻ ተፈጸመባቸው ።

ዛሬ ደግሞ በልማት (master plan ) ሰበብ ፤ በነዚያና በነዚህኞቹ ውለታ-ቢስ ዘመነኛ ባለጊዜዎች የኦሮሞ ህዝብ ታሪኩ የተፋቀ (የጠፋ) ፤ ባህልና እምነቱም በሌሎች የተጨፈለቀ ፤ ቋንቋውን ትቶ ወይም አዳክሞ የሌላውን ያስተናገደ ፤ ማንነቱን ችላ ብሎ ስሙን በሌላ የለወጠ ፤ ፍትህ የናፈቀው ፤ ድህነትና ጭቆና ያንገሸገሸው ፤ከራሱ ይልቅ ለሌላ የኖረ ፤ በሩህሩህነቱ በገራገርነቱ በደግነቱ ሁሉን ችሎ ፤ ወጪ ወራጁን እንግዳ ተቀብሎ ፤ ለተቸገረው ረድቶ ፤ያለውን ለሌለው አካፍሎ ፤ የተራበንና የተጠማን አብልቶ በማጠጣት ውለታ የተነፈገው ፤ ስለ ጀግንነቱ ገድል ያልተወራለት ፤ ልፋት፤ ድካምና ጥረቱን ያጣጣሉበት ፤ በገዛ ሀገሩ ባይታወር እና የበይ ተመልካች ሆኖ የኖረ ምስኪን ህዝብ ነው ኦሮሞ ።

በዚህም ምክንያት ይህ የኦሮሞ ህዝብ “ኢትዮጵያ “ በሚትባል ሀገር ከእንጀራ ልጅነት ባልተናነሰ ለዘመናት እየኖረ በአንጻሩ ደግሞ በሰሜን በምስራቅ ይቺኑ ሀገር ለመውጋት የውጪ ወራሪ ጠላት ሲመጣባት በራሱ ስንቅና ትጥቅ ከምዕራብ ፤ ከምስራቅ ፤ ከደቦብና መሃል ኦሮሚያ ተጥራርቶ “ ሆ “ ብሎ በመውጣት ውድ ህይወቱን ሰውቶ ፤ ተራ በተራ ልጆቹን ገብሮ ኢትዮጵያን እስከ ዛሬ ሳትደፈር ፤ ሳትቆረስ ጠብቆ ያኖረ የኢትዮጵያ አለንታ ፤ መከታ ጀግና ህዝብ ነው ።

ኢትዮጵያ ፡

ኢትዮጵያ የሚትባል ምድር ኦሮሞ ባይኖር ኖሮ በየዘመናቱና ጊዜያቱ በተለያዩ አቅጣጫዎች እስከ ዛሬ ድረስ የተነሱባት የውጪ ወራሪዎች ኢትዮጵያን ከዓለም ካርታ ፍቀው የራሳቸው በማድረግ ታሪክና ስሟን ገና ድሮ ያጠፏት ነበር ።

አዎን ! ማንም ባያምን ቢያምን ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ህልውና መኖር የኦሮሞ ጀግኖች ድርሻ ፤ የህይወትና የደም ዋጋ እጅግ የላቀ ሥፍራ በተገባው ነበር ። ዳሩ ግን ምን ያደርጋል ? “ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” እንደተባለው ይቺ የደም መሬት ኢትዮጵያ ብርቅዬ የቁርጥ ቀን የኦሮሞ ልጆችን አፈራርቃ እየበላች የማትጠረቃ ፤ ከነአካቴውም የከሳች ሀገር ፤ በታሪክ ዳግም ጨርሶ የማናገኛቸውን ውድ ጀግኖቿን እጃቸው በደም በተነከረ መናኛ ባንዳና ከሃዲ አምባገነን አረመኔዎች አናት አናታቸውን የሚትቀጠቅጥ ፤ የከበረውን ብርቅ በመናኛ የሚትለውጥ ሀገር ኢትዮጵያ ።

ይቺ የደም መሬት ሁሌም ደም የሚንቆረቆርባት (የሚፈስባት) ፤ እሷ ራሷ ደም ፤ ታሪኳ ደም ፤ ስሟም ደም ፤ ኢትዮጵያ የደም ምድር የደም አምባ ፤ ፍትህ የሌለብሽ ፤ ህጋዊ መንግስት ጨርሶ ያልነገሰብሽ ፤አንቺ የደም መሬት መቼ ይሆን የሁሉ ሆነሽ የሚናይሽ ?

ኦሮሚያ ፡ pg. 7

ኦሮሚያ ግን ሁሉ እያላት ፤ ሁሉ ሞልቷት መብትና ነጻነት የተነፈጋት ፤ ችግር ፈተና የከበባት ፤ ሁሉም የሚግጣት ፤ ግፍና ስደት ያንገላታት ፤ ጠኔ ጎጆ የሰራባት ፤ ብርቱ የጭቆና ቀንበር የተጫናት ፤ያልታደለች ወልዳ አሳድጋ ፤ ለፍታ ገንብታ ፤ ዘርታ አልምታ ፤ ያለ ፍሬ የቀረች ፤ አስታዋሽ ያጣች ፤ አመድ አፋሽ የሆነች ፤ ለምና ገራገር ፤ ድንግል አፈር የነኛ የጀግኖች ሰፈር ኦሮሚያ ።

ኦሮሚያ ራሷ ዘርታ እውስጧ እየበቀለ እውስጧ እየፈላ ፤ እየተንተከተከ ፤ እየቦካ ፤ እየተጋገረ ተመልሶ መርዝ የምረጭባት ምድር ፤ ነፍሷንም ሥጋዋንም ተበልታ ፤ ልጆቿን ተነጥቃ ፤ ጀግኖቿን ገብራ አዛውንቶቿን አዋርዳ ታሪኳን ቀብራ ፤ የሁሉ ባለቤት ሆና ሳለ የሀገር አውራ ፤ እጅ እግሯ ተጠፍራ ታስራ ፤ ቄዬዋን ተወራ ፤እየቀጨጨች የሚታንስ ቁልቁል የሚታድግ እያደር ፤ ኮስምና ቀስ በቀስ እርር ድብን ብላ የሚታር፤ የሚትከስል ምድር ፤ ልጆቿን በማባረር ከሀገር ወደ መንደር እያደር ጠባብ መንደር ብሎም ትንሽ ሰፈር ፤ አቤት ያንተ ያለህ አንቺ ኦሮሚያ ቁልቁል የሚታድጊ ሀገር ።

Dinni numarssee halkani guyyaa

Biyyatti warra kiyyaa

Egaa maal nuu wayyaa

Oromiyaa yaa biyya kiyyaa ?

ኦሮሚያ እንቁ ፤ አልማዝ ወርቅ ሞልቷት እያለ ሳታጣ አጥታ እንደ አመድ ነጥታ ፤ ነጭ ማኛ ፤ ማርና ወተት እያላት ጠኔ ጎጆ የሰራባት ለልጇ ማሽላ እንኳ ማቅመስ ተስኗት ረሃብ የነገሰባት ፤ ለሌላ እንጂ ለራሷ መሆን የተሳናት ምስኪን መሬት !!

አቤት ! አዎይ ነዶ !!

መከራው ፤ እሮሮው ፤ ግፍና በደል እልቂቱ ዛሬም አልጠገገም ።አሁንም እንኳ በዚህቺው በኢትዮጵያ ከዚያው ከደም መሬት ከድንጋይ ውስጥ የበቀሉ ፤ ከምድረ-በዳ የፈሉ ፤ከአለት የተፈለጡ ጥቁር ባልጩቶች ( ጨካኝ ውሪ እባቦች ) ባልወለደ አንጀታቸው ምስኪኑን ወገኔን በጥይትና በቦንብ እየጨረሱት ነው ። ኦሮሞው ወገኔ በግፍ እየተገደለ ነው ። ፍትህ በጎደለባት ፤እውነት በሌለባት ፤ ሃሰት ቅጥፈት በነገሰባት ፤ አመዛዛኝ ዳኛና እውነተኛ ሃቀኛ ሰው በጠፋባት ፤ የተበደለው ሰሚ ባጣበት በዚያች በጨለማዋ ዓለም በኢትዮጵያ ምድር መኖር እንዴት ይከብዳል ? ኢትዮጵያዊ ተብሎ መጠራትስ ምን ያህል ያሳፋራል ? ኢትዮጵያ መላ የሌላት ሀገር ፤ ኢትዮጵያዊም ያልታደለና ባለቤት ያጣ ፍጡር !!

ይህንን ለዘመናት የተፈራረቀብንና ዛሬም ጨምድዶ የያዘንን ጨቋኝ ሥርዓት በመቅጨት ታሪካዊ ጠላታችንን አንገቱን ቆርጠን የዘውትር ህልምና ቅዠቱን ማምከን የጊዜው ወቅታዊ እና አጣዳፊ ተግባራችን ነው ።

ለጋራ ግንዛቤ እንዲረዳን ከ150 ዓመታት በፊት ጀምሮ እስካሁኗ ደቂቃና ሰኮንድ ድረስ ዘልቆ የመጣውን ትምክህት ፤ እብሪትና ትዕቢት ብሎም አንድ ባንዲራ ፤ ሀገር ማቅናት ፤ ሃይማኖት አንድነት ፤ ስልጣኔ ፤ ልማት (ማስተር ፕላን ) ወዘተ.. እያለ ተራ በተራ እየተለዋወጠ የሚቃዠውን ቀጣፊ ሥርዓት ጨርሶ ለማጥፋት ተያያዥነት ያለውን ታሪካዊ ጠባሳና አሻራ ወደ ኋላ ተመልሶ መቃኘት አስፈላጊ ነው ። pg. 8

ከጥንት ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ የኦሮሞ ጠላት ራሱ ኦሮሞ ጭምር ነው ያሰኛል ። በእርግጥ በየጊዜያቱ የተፈራረቁበት በርካታ ጠላቶች ቢሆኑም ሁሉም ጠላቶች እሱኑ (ኦሮሞን ) ተጠቅመው አጠቁት ፤ ኦሮሞ ራሱ በየዋህነቱ ፤ በገራምነቱ ፤ በገራገርነቱ ፤በደግነቱና በቀናነቱ ተዘናግቶ ለጠላት ስለ ተመቻቸ ተጠቃ ፤ እጁን በእጁ በላ ። እሱ በከፈተው ቀዳዳ በኩል ተኩላዎች ፤ ቀበሮዎችና እባቦች በኦሮሞ መካከል ገብተው መሰሪ ዓላማቸውን በሥራ ላይ አዋሉት ።የኦሮሞ ህዝብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የወራሪዎች አባሪ ተባባሪ በሆኑት ጥቂት ከሃዲ ባንዳ ልጆቹ አማካኝነት ክፉኛ ተጎዳ ማለት ይቻላል ።

ለምሳሌ ከአጼዎች እስከ ደርግ ዘመን የነበሩት የአገዛዝ ሥርዓቶች ውስጥ የሃላፊነት ቦታና ስልጣን የነበራቸው የኦሮሞ ከፍተኛ የጦር መሪዎች እና ባለሥልጣናት በሙሉ ልክ እንደ ዛሬዎቹ የ”OPDO” አባላትና የወያኔ ካድሬዎች ( የይስሙላ ባለስልጣናት ) ለኦሮሞ ያተረፉት ጭቆናን ፤ የጅምላ ጭፍጭፋን እና ለራሰችው ደግሞ ውርደትና ባርነትን ብቻ ነው ።

የቀድሞዎቹ የሰሜን ወራሪዎች ወደ ኦሮሞና ሌሎች ክልሎች ሲመጡ ልክ እንደ ዛሬዎቹ መሰሪ ፤አታላዮችና ፈሪዎች ስለነበሩ ግልጽ የሆነ ጦርነትን በማወጅ ፊት ለፊት የመጡ አልነበሩም ። ነገር ግን የረቀቀ ዘዴና ተንኮል በተሞላበት ራሳቸውን ከሰማይ ሰማያት ዘር ከንጉስ ዳዊት ልጅ ከእስራኤል ንጉስ ከሰለሞን ከአይሁድ (ከኢየሱስ የዘር ግንድ ) በፈጣሪ ተዕዛዝና ምሪት ከህዝበ-እስራኤል (ከአይሁድ ) በቅለው እኛን እንዲመሩ ፤ ሊያስተምሩ፤ ሊመክሩ ፤ ሀገር ሊያቀኑ ፤ ትውልድን ሊያሰለጥኑ በፈጣሪ አምላክና ምሪት ለኛ የተላኩ አስመስለው ነጩን ውሸት በእውነት ጀቡነው (ደርተው ) የቅጥፈት አዋጅ ነጋሪት እየጎሰሙ በአንድ እጃቸው መስቀል ፤ በሌላኛው እጃቸው ደግሞ ጠመንጃ ይዘው የሌላውን እምነት ፤ ባህል ፤ ቋንቋና ልማድ አጥፍተው ሀገራችንን (መሬታችንን) በወረራ በመውሰድ እነሱ ባለታሪክ ሆነው ሌላውን የታሪክ አልባ ያደረጉ ጎሰኛ ፤ ጎጠኛ ፤ዘረኛ ፤ እና ራስ ወዳድ የሆኑ ገና ከጥንት ጀምሮ የጠባብነት ልክፍት ያሰከራቸው ዋሾዎች ነበሩ ።

እነዚያ ጉዶች ቀድሞም ቢሆን የሰውን ሀገር ወረው ፤እምነት ጨፍልቀው ፤ ታሪክ ደምስሰው ወደ ሰው ቄዬ ሰርገው ሲገቡ በርግጥ በነበራቸው እውቀት ፤ ንጽህና ፤ቅድስናና መንፈሳዊ መገለጥ ለህዝቦችና ለሀገር በጎ ራዕይና ቀና ዓላማ ያነገቡ በርግጥ ከፈጣሪ የተላኩ መላዕክት ወይም ጀግና ስለነበሩ በጦርነት አሽንፈው ሳይሆን እንዳውም ወደ እኛ ወደ ኦሮሞ ክልል ጥሰው ሲገቡ ባዶ ገላቸውን (እርቃናቸውን) የቆረፈደ ቁርበት (ቆዳ ) ለብሰው ፤ እንኳን ሊያሰለጥኑ ፤ ሁሉንም አንድ አድርገው ሀገር ሊያቀኑ ሳይሆን ራሳቸው በልተው ያልጠረቁ ፤ አንዳች የማያውቁ ፤ ለምንም ሃላፍነት የማይበቁ ፤ እርስበርስ የማይግባቡ ሊጠፋፉ የሚፈላለጉ ፤ እንደ ተራበ ቀበሮ የሚባሉ ፈርሃ እግዚአብሔር ያልነበራቸው ተኩላዎች እና ስግብግብ (selfish) ዋሾዎች ነበሩ ። ታዲያ ለራሱ ህብረትና ፍቅር ሳይኖረው ፤ ፈጣሪ አምላክን ሳያክብር ፤ ሳይሰለጥን ጦሙን ውሎ እያደረ ፤ ቀንና ሌሊት ቁርበት ለብሶ ውሎ እያደረ “አንድ ህዝብ አድርጌህ እየመራሁህ ላሰልጥንህ መጣሁ” ብሎ ከመዋሸት የበለጠ ስግብግብና ሰነፍ ዋሾ ኖሮ ያውቃል ዎይ ? አያ ጅቦ በማያውቁት ሀገር ለንግድነት ሄዶ “ቁርበት አንጥፉልኝ “አለ እንደተባለው ተረት መሆኑ ነው ። የሌላውን እምነት ፤ ባህል ፤ ቋንቋ፤ ልማድና ታሪክ አጥላልቶ በማንቋሸሽ የራሱን ምንነት ለምስፋፋት ሌት ተቀን ከመጣር የበለጠ ስግብግብ ፤ ጎሰኛ ፤ ጠባብ ጎጠኛና እብሪተኛ አክራሪ ብሔርተኛስ አለ ዎይ ? pg. 9

“ የአይጥ ምስክር ድንቢጥ ናጥ “ እንዲሉ የዛሬዋ ወያኔም ብትሆን የዋዛ አይደለችም ። በተቻላት መጠን እጅና እግሯን አራዝማ ( በልዩ ልዩ ጥቅማጥቅምና ድለላ እንዲሁም ማስፈራራት ) ዘዴ ተጠቅማ “ ትውልድን ከፋፍሎ በጠላትነት ፈርጆ በማጣላት “ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል “ እንዳለችው እንስሳ የስልጣን ዘመኗን ለማራዘም ሁሉን በክላ ፤ አጣልታ ደም አቃብታ ፤ “ማኖ “ አስነክታ ህዝባችንን አቃቅራ ከፋፍላ ለየብቻ ነጥላ ለመምታት የዘመናችንን መንፈሳዊ ተብዬ የቤተ-እምነት መሪዎችን ጭምር ቀጥራ አሰልጥና በካድሬነት በኛው መካከል ማሰማራቷ ፋሺኑ ያለፈበት ፤ አሳፋሪና ቅሌት የተሞላበት የተበላ እቁብ ነው ።

ከሁሉ የሚገርመውና የሚደንቀው ከጥንት እስካ አሁን የኦሮሞ ጠላቶች ብዙ መሆናቸው ነው ።ከላይ እንደ ተጠቀሰው የቀድሞዎቹ ጠላቶች ጠመንጃን ወድረው መስቀልን በደረታቸው ላይ በትልቁ አንጠልትለው (ለጥፈው) በአናታቸው ታቦትን (ጽላት ) በእጃቸው ግን ደም ጨብጠው የዚያን ዘመኑን ህዝባችንን ዋሽተው አታለው በእግዚአብሔር ስም ሳይማሩ ሊያስተምሩ ፤ እነሱ ራሳቸው ሳይነጹ ሊያንጹ ፤ ሳይቀደሱ ሌላውን ሊቀድሱ ፤ ማንም ሳይረክስ ለመቀደስ ወዘተ.. በሚል ውሃ ረጭተውና ክር በሰው አንገት ላይ አስረው በድግምትና መተት ህዝባችንን በማደናገር የራሱን ጥንታዊ እምነት አስጥለው መሬቱንም ቀምተው ፤ታሪክና ባህሉን ያጠፉበት ጠባሳ ሳይፈወስ የዛሬዎቹ አዲስ ግልብጥ መንፈሳዊ ነቢያት ተብዬ የኦሮሞ ፓስተሮችና ወንጌላዊያን ጭምር ሳይቀሩ የንጹሃንን ደም መጣጩን ፤ ሀገራችንን የበታተነውን ፤ ኢኮኖሚያችንን የመዘበረውን ፤ ሀገር ቆርሶ የሸጠውን ፤ ጠባብ ብሔርተኛ ወራዳ የሽፍታ ቡድን ን “ የፍትህ ፤ የዲሞክራሲ ፤ የእምነት ነጻነት ፤ የልማት ባለ ራዕይ መንግስት ለሆነው የኢትዮጵያ ተስፋ ( ለወያኔ ) ተገዙ “ ይሉናል ።

ይህ ብቻም አይደለም “ እምቢ ካላችሁ በኑሮ አትባረኩም ፤መንግስተ-ሰማይ ለናንተ ዝግ ስለሆነች አትጸድቁም “ በማለት ነጋ ጠባ በየእምነት ቤቶች ፑልፒትና በየእስተዲዮሙ ሀገር አቀፍ መንፈሳዊ ኮንፈረንስ ( የጀማ ስብከተ-ወንጌል 0 ፕሮግራሞችን እያዘጋጁ ወያኔ-ወለድ ባንዲራዎችን አንግበው በማውለብለብ ና የድል ፋና ችቦ እየለኮሱ ሰው ሁሉ ለወያኔ እንዲንበረከክ የሚያስደርግ የውሸት ወንጌልን ከኪሳቸው እያወጡ በመስበክ በክርስቶስ ስም ትውልድን አዘናግተው በማሸማቀቅ የወያኔ ባሪያ ያደርጉታል ።

የድፍረታቸው ድፍረት በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞተው በብርሰልስ (ቤልጄየም ) ሆስፒታል ውስጥ ከወር በላይ እሬሳቸው ቋንጣ ሆኖ በማቀዝቀዣ ውስጥ እስኪቆረፍድ ድረስ በተቀመጠበት ወቅት “ አቶ መለስ ሞተ ተብሎ ሲወራ ለምን ሰማችሁ ? ( ለምን አወራችሁ ?) ፤ እኛ ባለን መረጃ መሰረት ጠቅላይ ሚንስትራችን ድነው ጤናቸው በአሁኑ ሰዓት በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ ይገኛል ፤ እንዲያውም በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ራሳቸው በቴሌቪዥን መስኮቶች ላይ ቀርበው ሲናገሩ እናያቸዋለን እንሰማለን ፤ ሞተ ብላችሁ ያወራችሁ ያሟረታችሁ ተነሱና ተንበርክካችሁ ንሰሃ ግቡ ። “ በማለት ህዝበ-ክርስቲያኑን ባልሰራው ሃጥያት አሸማቀውና አስፈራርተው ንሰሃ ያስገቡ ባንዳ የሃሰት መምህራን ፤ የቤተእምነት መሪ ካድሬዎች ምንኛ ያሳዝናሉ ? ለመሆኑ ቀኑ ደርሶ የሞተን ሰው የመሞቱን ወሬ መስማትም ሆነ ላልሰማው ማሰማት እንደ ሃጥያት ተቆጥሮ ወቅሶና ገስጾ ትውልድን ንሰሃ ግቡ ብሎ የሚያዝ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ወይስ ቅዱስ ቁራን ?

እነዚህ ከሃዲዎች ከትናንት ታሪክ የማይማሩ ፤ እውነትን የማይናገሩ ፤ ለጥቅማቸው ሲሉ ሃሰት የሚቀባጥሩ ፤ ለወያኔ ፍርፋሪ ያደሩ ፤ በመንፈሳዊ አገልግሎት ስም ህዝበ-ክርስቲያንን የሚመዘብሩ ፤ ለሆዳቸው ብቻ pg. 10

የሚጥሩ ፤ ትውልድን ለማዘናጋት የተሰማሩ ፤ ለዝና ፤ ለእውቅና ፤ ለክብርና ጥቅማቸው ሌት ተቀን በትጋት የሚሰሩ፤ ካድሬዎች ስለነበሩ ለዕለት ሆዳቸው ምድራዊ ፊላጎትና ስሜት እርካታ ሲሉ እግዚአብሔርን እንኳ ጨርሶ የማይፈሩ ፤ በእግዚአብሔር አምሳያ ለተፈጠረው ክቡር ሰው ፈጽሞ የማይራሩ የሀሰት መልክተኞች እንጂ ከእግዚአብሔር ወገን አይደሉም ።

እነዚህ በሶስት ቢላዋ የሚበሉትን የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሁለገቦች ጌታ አምላክ ይቅር ይበላቸው ፤ ጊዜውና ሰዓቱ ሲደርስ ግን ታሪክና ህዝብ ይፋረዳቸዋል ።

እነዚህ መንፈሳዊ ቋንቋን እያወሩ ወያኔን የፍትህ ፤ የዲሞክራሲ ፤ የእምነት ነጻነት አባትነትና የልማት መሃንዲስ አድርገው ሊሰብኩን ቢቃጡም ሁላችንም የትናንቱን ገንጣይ ወንበዴ ማንነት የዘነጋን መስሏቸው የወያኔን ማንነት ለኛ ለመንገር ማሰብ “ ለቀባሪው አረዱት “ ያሰኛል ። አሁን ማን ይሙት በርግጥ የወያኔ መንጋ ፈርሃ እግዚአብሔር ያላቸው አማኞች ሃይማኖተኞች ነበሩ ? አክራሪ ኮሚንስቶች ወይም አብዮተኞች አልነበሩም ዎይ ? በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ ጻዲቅ ለእንስሣም ቢሆን ይራራል “ የሚል ቃል ማንበቤ ትዝ ይለኛል ። እነዚህ የዛሬ መንፈሳዊያን ተብዬዎች ግን የሰው ልጅ በግፍ በጭካኔ በአደባባይ ሲገደል ፤ እንደ ቅጠል ሲረግፍ ፤ በየእስር ቤቱ ሲማቅቅ እንዴት የሚራራ አንጀት አጡ ?

አዎን ! እነ አጅሬ የልማት ፤ የእድገት ፈላስፎች ፤ የሀገራችን ታሪካዊ ባለ ራዕይ ነን ባይ ፈጣጣና ጠባብ ጎጠኞች ባልሳሳት ከዛሬ 42 ዓመት በፊት ብዛታቸው 11 ያህል የሚሆኑ ጥቂት ወጣቶችና አንድ ጎልማሳ ፤ 4 ጠመንጃዎችንና 1 ሽጉጥ ብቻ ይዘው ትግሬን ከኢትዮጵያ ሊገነጥሉ ደደቢት በረሃ የገቡ የጠባብ ብሔርተኝነት ስብስብ የበረሃ አይጠ-ሞገጦች ስለመሆናቸው እሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ እኛና ታሪክ ምስክሮች ነን ።

ያኔ በ11 ወጣቶች የተጀመረው ሀገርን ገነጣጥሎ ህዝቦችን የመለያየት የትጥቅ ትግል ለ17 ዓመታት ያህል ቀጥሎ በብዙ ቢሊዮን የሚገመት የሀገር ህብትን አውድሞ ፤ የብዙ ሺህዎችን ውድ ህይዎት እንደ ቅጠል አርግፎና ብዙ ሺህዎችንም አካለ ጎዶሎ ካደረገ በኋላ ከሌሎች በርካታ ዓለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታዎች ጋር ተደማምሮ ፤ አምባ-ገነኑ የደርግ ሥርዓት አርጅቶ ሲወድቅ የውስጥና የውጪ ኋይሎች እርዳታ ታክሎበት እነ ወያኔን በለስ ቀናቸውና ከትግራይ የብሔር ጠባብነትና ገንጣይነት አልፈው ተርፈው የእድገት ሁሉ መሐንዲስና የልማት ፈር ቀዳጅ ባለራዕይ መስለው ኢትዮጵያን የሚትጋጥ ፤ የሚትመጠጥ ፤ የሚትሸጥ የሚትለወጥ ፤ ኦሮሚያ ደግሞ ማንም የማይተኛላት ፤የማይወዳት ሁሉ የሚፈልጋት ፤የማትነጥፍ ጥገት ፤ ቢኖሩባት የማትቆረቁር የማትጎረብጥ የሚትመች ፤ ሁሉም የሚመኛት ፤ቢሸጧት ትልቅ ዋጋ የሚታወጣ ፤ ቢዘሩባት ብዙ ፍሬ የሚትሰጥ ፤ እንደ ዳቦ የሚትገመጥ ድንግል መሬት ፤ አየር ንብረቷ ምቹ ፤ ጣፋጭ ሸንኮራ አገዳና የሚትመጠጥ የማር ወለላ የግል አንጡራ ሃብታቸውና ትርፋቸው አድርጓት እርፍ አሉ ።

ከዚያን ወዲያማ ምኑ ይነገራል? የቱ ተነግሮ የቱ ይቀራል ? ስንቱስ ተወርቶ ያልቃል ? በአጭሩ ይሀው እስከ ዛሬ ድረስ መላው የሀገርቱ ዜጎች ዕለት በዕለት ያለአንዳች ጥፋትና ወንጀል ይታሰራሉ ፤ ይደበደባሉ ፤ ከሥራ ፤ ከሀገር ይባረራሉ ፤ ከይዞታቸው ይፈናቀላሉ ፤ ንብረታቸውን ይነጠቃሉ ፤ ከትምህርት ገበታቸው ይስተጓጎላሉ ፤ ይደሃያሉ ፤ በጭካኔ ይገደላሉ ። በሌላ በኩል ዘመነኞቹ ጠባብ ባለጊዜዎች ግን ዕለት በእለት ይፋፋሉ ፤በሥልጣን ይቆናጠጣሉ ፤ የሀገሪቷን ሁለንተና ይቆጣጠራሉ ፤ ይበለጽጋሉ ፤ pg. 11

ያልታደለው ቀን የጎደለበት ያገራችን ህዝብ ግን ከድህነት ደረጃም እጅግ የወረደ መራራ ችግርና ፈተናን እየተጋቱ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮን ለመኖር ይንደፋደፋሉ።

ይባስ ተብሎም የኦሮሞ ማህበረሰብ ከትናንቱ ( ከቀድሞው ) በባሰ ሁኔታ ማንነቱና ታሪኩ ተፍቆ ፤ ውለታው ተረስቶ ፤ እጅግ ተንቆ ፤ከምድሩ ፤ ከሀገሩ ከመንደሩ ፤ ከሰፈሩ አንዳች ድርሻ እንዳይኖረው እጅ እግሩን ጠፍረው በገዛ ቄዬው ላይ ሳይቀር የበይ ተመልካች ባይተዋር ከማድረጋቸውም በላይ አልፈው ተርፈው መሬትህን ( ርስትህን ፤ ቄዬህን ) ጥለህ ፤ ያረስከውን መሬት ሳትዘራ ፤ የዘራሀውን አዝመራ ሳታጭድ ፤ ያጨድከውን ሳትወቃ በጠራራ ጸሀይ በውድቅት ሌሊት ጣሪያና ግድግዳህን ብቻ ነቅለህ ፤ይዞታህን ለቀህ ጥፋ ተባለ ።

አቤት ድፍረት ፤ ከልክ ያለፈ ንቀት !!

እነዚህ የበረሃ ተኩላዎች የሰውን ልክና ግምት አለማወቃቸው ፤ የራሳቸውንም አቅም የማይገነዘቡ ከዚያ ከደም መሬት በደም ተዘርተው በደም የበቀሉ ከድንጋይ የተፈለፈሉ ተባይ ፈልፈላዎች ፤ ድንጋይ እራስ መርዛም ጥቁር እባቦች ።ዛሬ በኛ በኦሮሞዎች ላይ እየተፈጸመ ካለው ጭቆና ፤ ግፍ ፤ ንቀትና ጥቃቱ ከልክ ያለፈ ፤ ድንበር የዘለለ እና ሚዛኑን የሳተ ያለፈ በመሆኑ ተንቀናል ፤ተዋርደናል ፤ አንዴ ብቻ ሳይሆን ብዙ ሞቶችን ደጋግመን በቁም ሞተናል ።

እኛ የትናንቶቹ እንኳን እንደሚናውቀው ፤ የቆዬ ታሪክም እንደሚመሰክረው የኦሮሞ ህዝብ በርካታ ዘመናትን በተደጋጋሚ ተታሎ መብቱን ለሌሎች አሳልፎ ሰጥቷል ። አሁን ዘንድሮ ግን በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ የእሮሞን ህዝብ ገጥሞት የማያውቅ ፈተናና ጥቃት ገጥሞታል ፤ ብርቱ መከራና ስቃይ ከፊታችን ተጋርጧል ፤ ዘርንማንዘራችን ፤ አያት ቅድመ አያቶቻችን እጅግ ውድ የህይወት ዋጋን ከፍለው ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ለዘመናት ጠብቀው ያቆዩልን ሀገር ፤ የወላጆቻችንና የኛም እትብት የተቀበረባት ቄያችን እዚህ ግባ በማይባሉ ምናምንቴ ቅጫሞች እየተነጠቅን ነን ።

እንዲሁም ሆኖ “ ገና ምኑ ታይቶ ? ገና በበረት ውስጥ ጭምር እናጉራቸዋለን እንጂ ወደደኡም ጠሉ እኛው ያልናት ትዕዛዝ ትፈጸማለች ፤ አለበለዚያ እንቢ ቢሉ ግን በጠመንጃ አፈሙዝ ልክ እናስገባቸዋለን “ በማለት እቅጯን እየነገሩን ዝተውብናል ፤አስፈራርተውናል።

የመብት ፤ የነጻነትና የፍትህ ጥያቄን በሰለማዊ መንገድ ሲቀርብላቸው “ እናንተ አሸባሪዎች ፤ አጋንንቶች ፤ ሳይጣኖች .. “ ወዘተ እያሉ እንደ ወንጀለኛ በመቁጠር በዛቸ በማሸመቀቅ አስደንግጠው በመከፋፈል በጦር መሳሪያ ከምድር ገጽ ሊያጠፉን ተነስተውብናል ። አሁን በዚህ ደቂቃና ሰዓት የትውልድ ህይወት እየተቀጠፈ ነው ፤ ቁጥራቸው በብዙ ሽህዎች የሚገመተው ህዝባችን አዋቂና ህጻን ሳይባል በየእስር ቤቱ እየታጎረ ከሞት እጅግ የከበደ ስቃይና መከራ እየተጋተ ነው ፤ በየመንደሩ ሁሉ ንጹሃን ወገናችን የውሻ ያህል እንኳ ክብር አጥቶ ሰብአዊ መብቱ ተገፎ ፤ ፍጡር ሰው መሆኑ ጨርሶ ተረስቶ እንደ እባብ በየአደባባዩና ጎዳናው ላይ “ አናቱ (ጭንቅላቱ) በአረመኔዎች ተበጣጥሶ እንደ አይጥ በየጥሻው የትም እየተጣለ ነው። ከእንግዲህ ደግሞ ስንቶቹን የመታሰርና የመገደል ዕጣ እንደሚደርሳቸው ከወዲሁ መገመት አይቻልም ።

ላለፉት 24 ዓመታት መጠነ ሰፊ የሆነ በደል ፤ ጭቆናና ግፍ እንዲሁም የህይወት ህልፈት ሲያፈራርቅብን የሰነበተው ሰው በላው አምባ ገነን ሥርዓት ስምና ቅርጹን ለወጥ አድርጎ ብቅ ያለ ቢሆንም የከዚህ pg. 12

ቀደሞቹ ሌሎች ጨቋኝ ሥርዓቶች ቅጥያ መሆኑን ባንስተውም የአሁኑ ግን እጅግ ከእሬት ይበልጥ መራራ ሆኖብናል ።

ከዚህ ከገጠመን ብርቱ ፈተና ፤ ችግር ፤ መከራና ከባድ አደጋ ለመወጣት የጋራ ክንዳችንን አስተባብረን እየፈጀን ያለውን ወራሪ ጠላት መግጠም ግንባር ቀደም የሆነ የሁሉም ኦሮሞ ልጅ ሃላፊነት ነው ።ነገር ግን ይህንን ህዝብ አስተባብሮ ፤ አቀናጅቶና አደራጅቶ የሚመራ ወሳኝ የሆነ አካል ( ድርጅት ወይም የፖለቲካ ተቋም ) መኖር ነበረበት ፤ ሌላው ቀርቶ መቼ ፤ እንዴትና ምን መደረግ ስላለብን በግንባር ተገናኝቶ ለመምከር ፤ በስልክም ይሁን በአካል ተፈላልጎና ተቀራርቦ በመገናኘት ሃሳብ ለመስጠት ፤ ጥያቄ ላማቅረብ ፤ለመመካከር ፤ እና ጠቃሚ የሆነ የጋራ አፋጣኝ መፍትሄ ለማስገኘት የሚቻልበት ጭላንጭል እና ይህ ነው የሚባል ጠቋሚ ተስፋ ጎልቶ ባለመታየቱ ይህችን ደብዳቤ ለመጻፍ ተነሳሳሁ ።

ይህ ሁሉ ዘግናኝ የሆነው አሳፋሪ ውርደትና ጥቃት ሁላችንም በህይወት እያለን በኛ ላይ ስለ መፈራረቁ ተጠያቂነትና ሃላፊነቱ በሁሉም የኦሮሞ ልጅ ትከሻ ላይ የወደቀ በመሆኑም እኔም እንደ ኦሮሞ ተዋላጅነቴ ከንፈር ከመምጠጥ ባለፈ በጣም ከመናደድ አልፎ እንቅልፍና እረፍት የሚነሳ መቆርቆር ፤ መቃጠል መንጨርጨር እየተፈራረቀብኝ ብቻዬን የሚፈይደው ነገር ስለማይኖር የጉዳዩ ባለቤት ለሆናችሁ ለወገኖቼ ለኦሮሞ ልጆች ጭንቀቴንና ንዴት ቁጭቴን በማካፈል በያለንበት ቁጭ ብለን በወሬ ብቻ ከሚንዋከብ ፤ ከንፈር ከሚንመጥ ፤የህይወት ዋጋ ጭምር ከፍለን በመተጋገዝና በመረዳዳት ለሀገራችን ፤ ለህዝባችን አፋጣኝ መፍትሄ እንፈልግ ለማለት ወደድኩ ።

ይህ እብሪተኛና ትዕቢተኛው ጠላታችን ወያኔ ጥጋቡ በዝቶ ፤ የግፍ ጽዋው ሞልቶ ለመደፋት በመቃረቡ በራሱ ጊዜ መውደቂያውን አፋጥኖ መቀበሪያ ጉድጓዱን ለራሱ እየቆፈረ ይገኛል ። ወያኔዎች እጃቸው በንጹሃን ደም በመጨማላለቁ የሚሰሩትንና የሚያወሩት ጨርሶ ጠፍቷቸው በትውልድ ላይ አፈና ፤ ግፍና ጭቆና ፤ በጅምላ ግዲያ ዘርን የማጥፋት (genocide) ዘመቻ ፤ ኢሰባኣዊ በሆነ መንገድ እየፈጸሙ ፤ ንብረት እየቀሙ ፤ ዜጎችን ከመኖሪያቸው እያፈናቀሉ ፤ ህጻናትንና ወጣቶችን ከትምህርት ገበታ እያስተጓጎሉ ፤ ሰራኞችን ከስራ እያባረሩ ፤ ያለአንዳች ጥፋትና ወንጀል ያለፍርድ አስሮ በማሰቃየት “አሸባሪ ፤ ሳይጠንና አጋንንት ናችሁ “ እያስባለ እናትና ልጅን በአንድ ላይ ገድለው የጥይት ዋጋ ገንዘብ ያልከፈሉትን እሬሳቸውን እንዳይቀበሩ በመከልከል ክብሩን የሰው በድን የዝንብ እራትና መጫወቻ እያደረጉ የኦሮሞን ደም ውሻ ያስላሰ ግፈኛ ፤ ሞገደኛ ፤ወንጀለኛና ወሮበላ ቡድን ነው።

ይህንን አስከፊ አረመኔ የህዝብና የሀገር ጠላት የሆነውን የወያኔ መንጋ መንግስት ተብዬ ታግሎ ለመጣል በህዝብ ራሳቸውን ያደራጁ ተቋዋሚ የፖለቲካ ሃይሎች (ፓርቲዎች ) በሀገር ቤትና በውጪ ያሉ በርካታ ቢሆኑም ቅሉ ፤ የቱንም ያህል ለህዝብና ለሀገር ነጻነት ፤ የፍትህ ሥርዓትን ለዜጎች ለማምጣት በየበኩላቸው ደፋ ቀና እያሉ ብርቱ ጥረት በማድረግ ቢሆኑም አንድ ብቻ የጋራ ጠላት ያላቸው መሆኑ በግልጽ እየታወቀ ሃይላቸውን አቀናጅተው ራዕይና ቪዢናቸውን አዋህደው ፤ በመካከላቸው ያለውን አመለካከትና አቋም ለማቻቻል ጥረት ሲያደርጉ አይታዩም ። ሁሉም በራሱ ዋሻ በያለበት እንዳለ አለ እንጂ ከራሱ ኮሮጆ ወጣ ብሎ ሌላውን ሲያስተባብር ወይም ወደ ሌላው ቀርቦ ራሱን ከመሰል የዓላማ ተጋሪዎቹ ጋር ተግባብቶ ለመስራትና ዋጋ ለመግፈል ዝግትና ፊላጎታቸው አናሳ ነው ።

እርስበርስ በትግስት ለመነጋገርና ለመመካከር ከመፈላለግ ይልቅ ፤ አብሮ ከመስራት ይልቅ ፤ የህዝብን ጥቅምና የሀገር ልዕልናን ከማስቀደም ይልቅ ፤ ለታቀደ የጋራ ዓላማ ህዝቡን ገርተውና መርተው ትውልድን pg. 13

ከአደጋ ከማዳን ይልቅ ፤ የጋራ ጠላታቸው ላይ የተባበረ ክንዳቸውን በጋራ ከማሳረፍ ይልቅ እርስበርስ በጎሪጥ የሚተያዩ ፤ የማይደራረሱ ፤ አንዳንዶቹ በደረቅ ፕሮፓጋንዳ የሚካሰሱ ፤ በራሱ በስሎና ገንፍሎ የውጣውን የህዝብ ብሶትና አመጽ ከግቡ የማያደርሱ ፤ ጠላትን በሩቁ መክሰስ እንጂ ወደ ህዝቡ ውስጥ ( ትግል ሜዳ ) ገብተው ታግለው የሚያታግሉ ፤ ጠላትን የማያቆስሉ ፤የማያደሙ ፤ ሳይጠሙና ሳይራቡ ፤ ሳይቆስሉና ሳይደሙ ሥልጣንን በአቋራጭ የሚፈልጉ የመቶ ሜትር ሯጮች ፤ መሞትንና መቁሰልን የማይሹ ፤ምናልባትም በወሬና በመፈክር ብቻ ብሎም በፈረንጆች በጎ ፈቃድና መልካም ቸርነት እንዲሁም እገዛ ብቻ ከወያኔ ወደ እነሱ የሥልጣን ሽግግር እንዲደረግ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ቁጭ ብለው የስልጣን ተራ የሚጠብቁ ይመስላሉ ።

ሌላው ቀርቶ ያለ አንዳች የፖለቲካ ፓርቲ አመራር ላለፉት 24 ዓመታት በህዝባችን ላይ ተጭኖት ከከረመው የአምባ ገነኖች ከልክ ያለፈ ጭቆና ፤ ግፍ ፤ ብሶትና እሮሮ የህዝባችን ቁጣ ሞልቶ ቢገነፍልም የማናቸውም የፖለቲካ ሃይሎች ቁርጠኝነት እና ከያሉበት ተፈላልጎና ተጠራርቶ ወደ ትግሉ (ህዝቡ ) ተቀላቅሎ ታግሎ የማታገል ዝግጅት ፤ የህዝቡን አመጽ የመምራት ተነሳሽነት ቅን ፍላጎት ፤ ተግባብቶ ወደ ፊት የመሄድ ተስፋ ጭላንጭል አለመኖሩ ቀሪ ትግላችንን መራራ ፤ ውስብስብና ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ረጅም ጊዜን ሊጠይቀን ቢችልም አሁንም ቢሆን አንዳንድ ቅን ፤ ቁርጠኛ የሀገራችን የፖለቲካ ሊህቃንና በርካታ ቆራጥ ምሁራን ስላሉን ተስፋ አንቆርጥም ።

በኔ አመለካከት እስከ ዛሬ የተፈራረቁብን ችግሮች መከራ ፤ ግፍ ፤ ጥቃት ፤ ውርደት ፡ እስራት ፤ እንግልት ፤ ስደትና ሞት ፤እያንዳንዳችንን አብስሎናልና ለኦሮሞ ህዝብ ከእንግዲህ ስለ ማንነቱ ፤ መብቱ ፤ ታሪክ ፤ትግልና ነጻነት አስፈላጊነት በማንም ሊነገረው አይገባም ።

በዘመናት ያልተቋረጠ ግፍ ፤ አድልዎ ና ብሶት እንዲሁም ከልክ ያለፈ እሮሮ ራሱ ከሚገባው በላይ አድጎና በስሎ “ እምቢ ለነጻነቴ “ በማለት ኦሮሞ በከባድ ቁጣ ገንፍሎ ወቷልና ከእንግዲህ ወደ ኋላ የሚመልሰው አንዳች ኋይል ከቶ አይኖርም ። ይልቁንም ይህ ህዝብ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይሄድ ፤ መሰሪዎች በዘዴና በስውር ጣልቃ ገብተው በልዩ ልዩ ተንኮል ጥቅማጥቅምና የማደናገሪያ ሃሳብ ህዝቡን ከፋፍለው በማጣላት ጉልበትና ኋይል እንዳያሳጡ ፤ አንዳን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ በፖለቲካኝነት በህዝብ ስም ራሳቸውን ተቋዋሚ ነን ብለው ከሚጠሩቱ አንዳንድ ከወያኔ የማይሻሉ ብልጣ-ብልጥ የሥልጣን ጥመኞች ይህንን ዕድልና ክፍተት ተጠቅመው በአቋራጭ በህዝብ አናት ለመቆናጠጥ ሲሉ የበለጠ ነገር እንዳይበላሽ ከሁሉ አስቀድመን አንድዳንድ ሁኔታዎችን ( ነገሮችን ) ፈጠን ብለን እንዲናስተካክል ለማሳሰብ እውዳለሁ ። እነሱም ፡

1ኛ. አንድነት :- እኛ የኦሮሞ ተወላጆች መሰረታችን ፤ምንጫችን ዘራችን ፤ ግንዳችችን ሁሉ ተዘርቶ የበቀለው ከአንድ ፍሬ ነው። ሁላችንም ከአንድ ቤተሰብ (ከኦሮሞ ) የተገኘን ፤ አንዱ ኦሮሞ የሌላው ኦሮሞ የደሙ ቅጂ ፤የአጥንቱ ስባሪ ፤ የስጋው ክፋይ ነው ።

እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ሁሉ ፈጠረ ፤ ሰው ግን በልምምድ ብዛትና ጊዜ ህደት የተለያዩ ቋንቋዎችን ፈጥሮ የራሱ መግባቢያው አደረገ ።በዚህ ሁሉ ህደት ውስጥ ኦሮሞም ባህሉ እምነቱ ልማዱ እና ታሪኩ ጭምር አንድ ነው ። የዛሬ ችግር ፤ መከራ ፤ ፈተና ፤ እንግልት እንዲሁም የወደፊት ዓላማውና ቀንደኛ ጠላቱም አንድ ነው። ጠላታችን ወያኔ ነው ። pg. 14

ጠላትን በልጦ ድል በመንሳት በአሸናፊነት ለመውጣት የሃይማኖትና የአካባቢ ልጅነት ልዩነቶችን በማስወገድ ቀዳዳ መድፈን ከእንግዲህ ይጠበቅብናል ። ከዚህ ቀደም በኦሮሞ የፖለቲካ የትግል ታሪክ ውስጥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በግልም ሆነ በቡድን የተሰራውን ስህተት ማስተካከልና ዳግም እንዳይደገም መከላከል እንጂ እገሌና እነ እገሌ በድለውናል (ጥፋት ፈጽመዋል ) በሚል መወቃቀስ ፤ መወነጃጀል ፤ መካሰስና ስም መጠፋፋት ይቁም።

ኦሮሞ ሆኖ በኦሮም ስም ለኦሮሞ ታግሎ ለማታገል በየቦታው በተለያየ መንገድ በግልም ሆነ በቡድን የሚንቀሳቀስ ሁሉ ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሞ ከያለበት ተፈላልጎ በፉጨት በመጠራራት ተነጋግሮና በጥልቀት ተመካክሮ ለአንድ ዓላማና የጋራ ጥቅም በአንድነት ታግሎ የጋራ ጠላቱን ለመጣል ከዚህ ቀደም ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ የተሳሰረ አንድነትና ጠንካራ ህብረት መፍጠር አለበት።

2ኛ. ማዕከላዊ አሰራርን የጠበቀ አመራር ( አካል ) መፍጠር ፦በሚፈጠረው አካል ሥር ከላይ እስከ ታች (ከታች እስከ ላይ ) በተዋረድ የህዝብን ዓላማና ጥቅም ለመጠበቅ ፤ በሚያስችል መልክ በድስፕሊን የታነጸና በቃል ኪዳን የታሰረ የግንኙነት መስመር እና የዕዝ ሰንሰለት (chain of command) ዘርግቶ ለአንድ የጋራ ግብና ስኬት የሚንመራበትን ሃላፊነትና ተጠያቂነት ያለው ሥርዓት ( ተቋም ) ማበጀት።

3ኛ . የትጥቅ ትግል ፦ ወያኔን ታግሎ በመጣል ግፍ ጭቆናንና የጅምላ ግድያን ለማስቆም ሰላማዊ ትግል በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ከእንግዲህ ፈጽሞ ሊሰራ አይችልም ። ሁለት እጅን አጣምሮ አናት ላይ በማድረግ የትግል መዝሙር እየዘመሩ ወይም እየጨፈሩ ጎዳና ለጎዳና በመዘዋወር በራስ ላይ ድብደባን ፤ እስራትንና ሞትን ማብዛት ነው ። እንዲሁም ወያኔን በማውገዝና እሮሮን ለዓለም መንግስታት በማሰማት ፤ትዕይንተ ህዝቡን ለመበተን ወያኔ በወሰደው የጅምላ ጭፍጭፋ እርምጃ የታሰረውን ፤ የተሰወረውን የተደበደበውን ፤ የተሰደደውንና የተገደለውን ማንነትና ህዝብ ብዛት በየሶሻል ሚዲያ ዘግቦ መለጠፍ ወይም ማሰራጨት ብቻውን ችግራችንን ቀርፎ ወያኔን አንገዳግዶ ካለንበት ወደ ፊት አንዲት እርምጃ እንኳ ፈቀቅ ሊያደርገን አይችልም ።

ምክንያቱም ላለፉት 24 ዓመታት ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን መላው የእትዮጵያ ህዝብ በቡድንም ይሁን በተናጠል እየታሰረ ፤ እየተደበደበ ፤ እየተገደለ ምናልባት ያለጦርነት በሰላማዊ መንገዶች፦

1ኛ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ ይሳካ እንደሆነ ተስፋ በማድረግ ህዝቡ ይሰሩልኛል ፤ ይወክሉኛል ፤ ለሀገርና ለህዝብ ይጠቅማሉ ብሎ ያመነባቸውን ተወካዮቹን ቢመርጥም በተለያየ ጊዚያት ውድቅ ተደርጎበታል ፤ መራጩ ህዝብም ሆነ ተመራጩ የህዝብ ተወካዮች የውያኔ የቅጣት በትር ( የጥይት ) ሰለባ ሆነዋል ፤ 2ኛ.የመናገር ፤ የመጻፍ ፤ የመጠየቅና ህሳብን በነጻነት የመግለጽ ሰባአዊ መብቶች ሁሉ በቀላሉ የሚታሰቡ አልሆኑም ፤ እስከ ዛሬ ድረስ የተከተልነው የትግል ስልት ሰላማዊ ቢሆንም ሰውንና ጊዜን ከመጨረስ በስተቀር አንዳች ፋይዳ አላስገኘም ።

3ኝ፣ህዝባችን ቅሬታውን ፤ቁጭቱን ፤ እሮሮውን ፤ ብሶቱን ስሜቱንና ሃሳቡን ብሎም የፍትህና የመብት ጥያቄዎችን ህገ-መንግስታዊ የዜግነት መብቱን ተጥቅሞ በሰላማዊ መንገድ ለመንግስት በሰልፍም ሆነ በሚድያ ተጥቅሞ ለማቅረብ ቢሞክር የጥይት እራት ከመሆንና ለእስራትና ለእንግልት ብሎም ለስደት ከመዳረግ በስተቀር የፈየደው ነገር እስከ ዛሬ የለም ። pg. 15

እስከ ዛሬ ድረስ ያልተከደበት የትግል ስልት የትጥቅ ትግል ብቻ ነው ፤ካሁን በኋላ ግን ምንም ምርጫ ስለሌለን እሱኑ ማፋፋም ብቻ ነው ።ይልቁንም ጠላትን ፊት ለፊት እየተናነቁ በቅድሚያ የህዋሀትን ( የወያኔን )ቁልፍ የኢኮኖሚ ተቋማትንና ወሳኝ ባለስልጣኖቻቸውን ማውደም ( መደምሰስ)።

ከወሬ ፤ ከኡኡታና የድረሱልን ጥሪ ይልቅ ራሳችንን ለትግሉ ማዘጋጀት እስካሁን በተሞከረው አኳኋን በሰላማዊ ትግል ከወያኔ ግድያና አፈና አምልጦ በመውጣት ፍትህ እኩልነት ያለበትን ሥርዓት ተክቶ የራስን መብት በማስከበር ሀገርንና ትውልድን ከነዚህ ወራሪዎች ለዘለቄታ ማስጣል ስለማይቻል ለትጥቅ ትግሉ ተሳታፊ እንዲሆን ትውልድን በዚያ ዙሪያ መቀስቀስ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው ።

ምክንያቱም ስቃይ እየተፈራረቀበት ፤ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ፤ ከባድ ውርደትና ጥቃት እየደረሰበት ፤ ብሎም ንብረቱ እየወደመ ፤ ቄዬው እየፈረሰ ፤ ከይዞታው እየተፈናቀለ ፤መቆሚያ መቀመጫ ( ለዕለት መኖሪያ አጥቶ ) ከቦታ ወደ ቦታ እየተሰደደ በረንዳና ዱር አዳር ሆኖ ፤ አሽከርና ገረድ ሆኖ ፤ እየሞተ በሰላማዊ ትግል መፈክር ብቻ እያሰማ ፤ “ ሆ “ ብሎ እየጨፈረ ፤ ወይም ደግሞ እስክሪብቶና ወረቀት ብቻ ይዞ እየተጻጻፉ በመካሰስና አቤቱታ በማሰማት የእልቂቱንና የጭፍጭፋውን ትዕይንት ቀርጾ በዜና መልክ እየዘገቡ በሶሻል ሚዲያ በመለጣጠፍ ብቻ መብቱን ያስከበረ ፤ ከባሪነትና ከጭቆና ነጻ የወጣ የሀገሩን ሉዓላዊነት ያስጠበቀ ( ከጠላት ያስጣለ ) ሀገርም ሆነ ህዝብ እስከ ዛሬ ድረስ በዓለም ታሪክ ኖሮ አያውቅምና ነው ።

በመሆኑም ጠላታችንን በትጥቅ ትግል ለመጣል በምንም ተጽዕኖ ሊበጠስ ( ሊከፋፈል ) በማይችል አንድነት በጋራ ተሰልፎ አንድ ወጥ በሆነ ማዕከላዊ አመራር ሥር ተዋቅሮ ፤ ተላላነትን ትቶ ፤ ገራገርነቱን ትቶ ፤ የዋህነትንና ደግነትን አቁሞ በጠላት ላይ ጨካኝ በመሆን ያለ አንዳች መዘናጋት መሰሪ ወያኔዎቹን እንደ ተርብ ነድፎ መጨረስ መቻል ይኖርብናል ።

ምናልባት አንዳንዶቻችን በአዕምሮችን እንደሚናሰላስለው ለትጥቅ ትግሉ መሳካት ወታደር መመልመል ፤ ጫካ ገብቶ መሰልጠን ፤ስንቅ ማሰናዳት ፤ የጦር ሰፈር ማዘጋጀትት (ምሽግ ቆፍሮ ደፈጣ መያዝ ) ወይም የተለያዩ ሁኔታዎችን በቅድሚያ ማሟላት ፈጽሞ አያስፈልገንም ።ከነዚህ ይልቅ በአሁኑ ሰዓት ኦሮሞ ስለ ማንነቱ እና ክብሩ ታሪኩ መብቱ ነጻነቱ ብሎም መሬቱ ( ሀገሩ ) ህይወቱን ሰውቶ ማስጠበቅ አለበት ፤ ኦሮሞ ከእንግዲህ ስለ ራሱ እንጂ ስለ ሌላው መኖርን ማቆም አለበት ።

እስከ ዛሬ የነበሩብንን ክፍተቶች ደፍነን ፤ ልዩነቶቻችንን በማቻቻል ስህተቶችችንን አርመን አንድ ወጥ በሆነው የጋራ ጥቅምና ዓላማ በአንድ ማዕከላዊ አመራር ሥር በትዕዛዝ ሰንሰለት (chain of command ) ተዋቅረን በመደራጀት ከልብ ለመሰዋት ቁርጥ ውሳኔ አድርጌን ለራሳችን ፤ ለህዝባችንና ለሀገራችን በፈጣሪ አምላክ ፊት ቃል ኪዳን ከገባን በሚፈጠረው አንድነትና ህብረት አማካይነት በየፊናችን የየድርሻችንን ሃላፊነትና ግዴታ ለመወጣት ከተሰለፍን አንዲቷ ቀጭን ትዕዛዝ ( መመሪያና ውሳኔ ) በታቀደለት ሰዓት ፤ በተመደበለት ቦታና ቀን በአንድ ጊዜ በተመሳሳይ ደቂቃና ሰኮንድ ሁሉም የኦሮሞ ዘር ባለበት ሥፍራ (አካባቢ ) ፤ ክልል ፤ከተማና ገጠር ሁሉ ላይ እንዲተገበር ማድረግ ብቻ ከበቂ በላይ ውጤትን ያስገኛል ።

ትጥቅን ( የጦር መሳሪያን ) እና ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስፍራን (ጫካን ) በሚመለከት

1ኛ . ሁሉም የኦሮሞ ልጅ በአንድ የዕዝ ሰንሰለት ( ማዕከላዊ አመራር ) ሥር ተጠልሎ ( ተሰባስቦ ተደራጅቶ ) ጠላቱን ለመምታት ( ለመደምሰስ) በአንድ ላይ ወደ ትግል ( ሰልፍ አደባባይ ) pg. 16

በየአቅጣጫው “ሆ “ ብሎ ከወጣ ራሱ ህዝቡ አንዱ ለሌላው እርስ-በርሱ መጠለያ ፤ መከታ ፤ ፤ ጫካና ማንም ጥሶት ወደ ውስጥ የማይገባበት ምሽግና ወታደራዊ ካምፑ ስለሆነ በአንዲት ጀንበር ጠላቱን ይውጣል ።

2ኛ. ሁሉም ኦሮሞ ቁርጥ ውሳኔ አድርጎ በአንድ ላይ ከወጣ ዱላውና ስለታም ብረቶች ፤ እንዲሁም የግል ነፍስ-ዎከፍ ጠመንጃና ሽጉጥ ብሎም በእጁ እሳት ጭምር ይዞ ከተጠቀመ አስቀድሞ ተጠንተውና ተለይተው የተመረጡ የህወሀት (የወያኔ) ዒላማዎችንና ቁልፍ ባለሥልጣናትን በማውደምና በማስወገድ የጠላትን መሳሪያ ነጥቆ ሊታጠቅ ይችላል ።

3ኛ. ነጥቆ በታጠቀው መሳሪያ ቀሪውን ጠላት ፊት ለፊት በመግጠም የሃይል ሚዛኑን በፍጥነት በመቀየር በጠላት ሰፈር ሽብርን ፤ ድንጋጤንና ፍርሃትን ፈጥሮ የውጪ ሃያላን ተብዬ መንግስታትን ትኩረትና ከበሬታን እንዲሁም የሚዲያ ሽፋን ስለሚያገኝ በጥንካሬው ባስመዘገበው ጊዜያዊ ድል የዓለምን ትኩረት የሚስብ የሚዲያ ሽፋን ጭምር በማግኘት ጠላቱን ያርበደብዳል ፤ከዚያ ቀደም ሲል ምናልባት ያመነታ ( የፈራ ) ጎሬቤትና ጎረቤቶቻቸው ባካባቢው ካሉ አደፋፍሮ ራሱም ተበራቶ ተጨማሪ ወገን ሊያፈራና ሃይለኛ ጉልበታም መሆን ያስችለዋል ።

ከዚህ በላይ የተጠቀሰው ጊዜያዊ ድል ከተደረሰ ጠላት ወደደም ጠላ የሃይል ሚዛን አሰላለፉን መቀየሩ የግድ ነውና በተለምዶ እንደ ታየው ለውሸትም ይሁን ለእውነት ገለልተኛ አካላትና መንግስታት የድርድርና የእርቅ ሃሳብ ከየአቅጣጫው ይዘው መቅረባቸው አይቀሬ ነው ።

ያ ድርድርና የሽምግልና ውይይት ከቀረበ ደግሞ ቅድሚያ ሁኔታዎችን (pre-conditions)ለማስቀመጥ ዕድል ስለሚናገኝ ያንን ጠቃሚ የቅድሚያ ሁኔታ በትክክል በማስቀመጥ ያለአንዳች መዘናጋት እና መታለል ረቀረው የትጥቅ ትግል ይበልጥ ተጥናክሮ በመቀጠል ሙሉ ለሙሉ ነጻነት እስኪገኝ ድረስ ትግሉን ማፋፋም ይቻላል።

ስለ ትጥቅ ትግል ( የጦር መሳሪያ ጉዳይ ) ሲናስብ በተለይ ጠላታችን ከታጠቀው ዘመናዊ መሳሪያና ከሰለጠነው የሰራዊት ብዛት አኳያ ሲመዛዘን የኔ ሃሳብ ምናልባት ቅዠትና እብደት የሚመስላቸው የወሬ ፈላስፎች ( ፈሪዎች) በኛው መካከል ሊኖሩ እንደሚችሉ አልጠራጠርም ።

ይሁን እንጂ የኛ የኦሮሞ ልጆች ዱላ (በትር) ቅጫሟና ሙጀሌያሟ ጠላታችን ወያኔ ከታጠቀችው ከዘመኑ ሮኬት ከቶ አይተናነስም ፤ አዎን ዱላችን ጨፍጫፊው ግፈኛ ሠራዊት ካነገበው መትረየስ እጅግ የሚበልጥ የሰማይ ቁጣና ከባድ ናዳ ነው ።

ስለዚህ እሱኑ ( ዱላችንን) ይዘን ፤ ሌላም የየግል የጦር መሳሪያና ስለታም ብረቶችን እንድሁም እሳት ጭምር ተጠቅመን በተባበረ ክንዳችን በቆራጥ ወኔ በጠላቶቻችን አናት ላይ ሲናሳርፍ ፤በአንጀቱ ላይ ስንሰካ ፤ በመንደሩና በኢኮኖሚ ይዞታው ላይ ስንለኩስ እስከ ዛሬ የፈሰሰው የወገኖቻችን ንጹህ ደም ከተንዠቅዠቀበት ይታፈሳል ፤ በየአቅጣጫው መንታ መንታ የዘነበው የእህቶቻችንና እናቶቻችን እንባ ይታበሳል ፤ በአረመኔዎች ጭካኔ የተሰውት የብዙዎች ህይወት ዋጋ በእጥፍ ይመለሳል ፤ ታሪካቸው ና ገድላቸው ይወሳል ፤ ይነገራል፤ ሰማዕታት ይዘከራሉ ፤ የመስዋዕትነታቸው ዋጋ ፍሬ ይታጨዳል ፤ የእስከ ዛሬው ሃዘን ያጎበጠው ግለሰብም ሆነ ቤተሰብ ካቀረቀረበት ቀና ይላል ፤ እልህ ያቆሰለው ይፈወሳል ፤ pg. 17

በብስጭት ያረረው አንጀት ይርሳል ፤ በቁጭት የበገነው ቆሽት ይድናል ፤የተወጋ ልብ ይጠገናል ፤ ተስፋ የቆረጡና ወኔ ያጡ ሁሉ ሞራል ፤ ድፍረትና ጉልበት አግኝተው ይበረታሉ ።

በአጠቃላይ እኛነትንና መብታችንን አስከብረን ፤ ነጻ ወጥተን ፤ ጠላታችንን በአፍ ጢሙ የሚንቀብርበት ጊዜ እጅግ በጣም ቅርብ ነው ።

መዘንጋት (መርሳት ) የሌለብን አጣዳፊ ነገር

ከላይ የተጠቀሱትን እንዲሁም በተጨማሪ ለወደፊት የሚንነድፋቸውን እቅድና ዓላማዎች በሥራ ከመተርጎማቸው በፊት አጣዳፊ ቅድመ-ሁኔታዎችን በአስቸኳይ መፈጸም ይኖርብናል ። እነሱም ፦

1ኛ. በታሪክ እንደሚታወቀው ዛሬ ከገጠሙን የታሪክ አተላ ወያኔዎች በስተቀር ኦሮሞ ማንንም ጠላቱ አድርጎ አያውቅም ፤ በቀደመው የርስበርስ ጦርነቶች ዘመን በጦር ሜዳ የማረካቸውን ጠላቶቹን እንኳ “ጉድፈቻና ሞጋፈቻ “ በሚባል የኦሮሞ ባህል መሰረት የቤተሰቡ አካልና ዘመድ አድርጎ በመቀበል ከራሱ ጋር ቀላቅሎ ልጆቹን እየዳረ ፤ መሬትና የቀንድ ከብት በነጻ ሰጥቶ ከሁሉ ጋር ተግባባቶና ተከባብሮ ተዛምዶ ኖረ እንጂ ምርኮኛንም እንኳ ገድሎ ወይም አስሮ አጎሳቁሎ የማያውቅ ሰው ወዳድና እንግዳ ተቀባይ ቅንና ደግ ሩህ ሩህ ህዝብ ነው ።

ሌላው ቀርቶ ከወያኔ አመራሮች በስተቀር ከተቀረው የትግሬና ሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጋር የወዳኝነት እንጂ የጠላትነት ታሪክ እንዳልነበረው ተገልጾ የዛሬው ትጥቅ ትግልም ሆነ የወደ ፊት የኦሮሞ ዋና ዓላማ ነፍሰ ገዳይ አረመኔ የትግሬ አመራርንና የነሱ ግብረ-አበር ባንዳዎችን ብቻ ማስወገድ እንደሆነ ተደጋግሞ በሁሉም ሚዲያዎች ያለማቋረጥ መነገር ፤ መወራትና መገለጽ መታወጅ አለበት ።

2ኛ. በአካባቢያችን( በኦሮሞ ) እና አጎራባች ክልሎች የሚኖሩትን ሌሎች ግለሰቦች ፤ ቡድኖችና ብሔሮችን መብትና ጥቅም የሚጻረር ፤ እምነትና ሃይማኖታቸውን የሚያጎድፍ ፤ ንብረታቸውን የሚነካ ፤ አንዳች የአፍ ወለምታ ( የድርጊት እርምጃ) በኛ ስም እንዳይፈጸምባቸው በሁሉም አቅጣጫና አካባቢ ወዳጅነትን እንጂ ጠላትነትን እንዳናተርፍ ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ።

5ኛ. ለታቀደው የትግላችን ማጠናከሪያና ለየትኛውም ቀጣይነት ላለው የኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ፤ መብትና ጥቅም ማስከበሪያ ( ማስጠበቂያ ) የሚሆን ከወዲሁ መሰረት መጣያ ተጠያቂነትና ሙሉ ሃላፊነት ያለው ግልጽነት በተሞላበት (Check & balance or Controlling mechanism ) የአሰራር ዘዴን የተከተለ በቋሚነት ገንዘብ የማሰባሰቡ (Fund rasing ) እንቅስቃሴ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲጀመር ጠንካራ ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ማቋቋም።

4ኛ. በአሁኑ ሰዓት በየክልሉ ያሉ የ”OPDO” ካድሬዎችና አንዳንድ የወያኔ አመራሮች በቡድን ዘመቻ መልክ እየተንቀሳቀሱ ላለፉት 7 ሳምንታት በኦሮሞዎች ሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ ትዕይንት የተሳተፉትን ወጣቶች አድነው ለማጥፋት አንዳንድ መምህራንን ፤ የተማሪዎች ወላጆችን እና መላውን ገበሬንና ብሎም በየከተማው ያሉትን ነዋሪዎችን እየተጠቀሙ በሽምግልና ሰበብ ህዝቡን አዘናግተው በማታለል ህይወታቸውን ለማትረፍ በየስፍራው ተደብቀው ያሉትን ወጣቶችና ጠንካራ ገበሬዎችን በማባበል አድነው ከያዟቸው በኋላ እያሰቃዩና እየገደሏቸው ነው።እግረ-መንገዳቸውን አንዱ ሌላውን እንዲያጋልጥ ፤ pg. 18

እንዲጠቁም በማድረግ በልዩ ልዩ ጥቅማጥቅሞች ደልለው ህዝቡን በመከፋፈል አጋጭተው ነገ እንዳይተባበር ፤ በቅራኔና በጥላቸ ወጣጥረው ትውልድን እርስበርሱ ደም እያቃቡ ናቸው ።

ይህንን በማድረግ ከአሁን በኋላ ህዝቡ ለመብትና ነጻነቱ እርስበርሱ ተማምኖ ተባብሮ በጋራ ቆርጦ እንዳይታገል በልዩ ልዩ የማጭበርበሪያ ጥቅሞች ሰውን ሁሉ ደልለው ትውልድን እያስፈራሩ እና ደም እያቃቡ ስለሆነ የዚህን ዓይነቱን የወራዶች መሰሪ ተንኮል የሽምግልና ግብዣ (ጥሪ) አንድነትን ለመበታተን ህብረትን ለማፍረስ የታቀደ ሴራና ደባ መሆኑን ህዝቡና ወጣቱ ተገንዝበው ማንኛውንም የዚህ ዓይነቱን የድለላ እርቅ ሃሳብ ከየትኛውም አቅጣጫ እንዳይቀበሉ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ያለማቋረጥ መስጠት

5ኛ. ከኢትዮጵያ ውጪ በመላው ዓለም በተለይም በአውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ተላላቅ ከተሞችና ክፍለ ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ ቦታዎች ሁሉ ቢያንስ ለ3 ቀናት ዘልቆ የሚቆይ የመንግስታትና የሀገራት መስሪያ ቤቶች (ተቋማት) ፊት ለፊት ወይም ዙሪያ የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቶ ከሁሉም ከተሞች ተጠራርቶ ወደ አደባባይ በመውጣት እዛው ውሎ ማደርና አድሮ መዋል።

ይህንንን ሰላማዊ ትግልና የመብት ጥያቄ ትዕይንት ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ዓለም በሞላ እንዲታዘብ ፤ እንዲያውቅ ፤ እንዲዘግብ ፤እንዲናገርና እንዲያስተጋባ በሰላማዊ ቁጣና ጩሀት በጾምና ጸሎት ጭምር ጫና በመፍጠር ለዓለም ማሳወቅ ።

7ኛ. ጠላታችን ወያኔ በሀገርና በህዝብ ላይ እስከ ዛሬ እየፈጸመ ያለውን ግፍ ፤ በደል ፤ድብደባ ፤ እስራት ፤ ግድያ ፤ የሀገር ሃብት ዝርፊያ ፤ የጅምላ ጭፍጨፋ ሁሉ የሚገልጽ በሰዕል ፤ በቪዲዮ ፤ በጽሁፍ አቀነባብሮ በማዘጋጀት በያቅጣጫው ለመንግስታት ፤ ለሀገራት ፤ ለሚዲያዎች ፤ ለሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ለእምነት ( መንፈሳዊ ) ተቋማት እና በየጎዳናው ሁሉ ላይ ለሚራማመድ አላፊ አግዳሚ ህዝብ ጭምር ማደል።

8ኛ. እነዚህ በውጪ ህርገራት በሚገኙ ተላላቅ ከተሞችና አደባባዮች የሚደረጉት ሰላማዊ ሰልፎች የሚያስገኙልንን እንድምታ መሰረት በማድረግ በተሻለ ሁኔታ በሀገር ቤትም አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የኦሮሞ ክልሎች በውጭ በተደረገው ምሳሌ (model ) መሰረት በተመሳሳይ ሁኔታ ለ3 ቀናት የሚቆይ ሰላማዊ ሰልፍ በጥንቃቄና በሚስጢር ተቀነባብሮ የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የተቃውሞ ትዕይንት መጥራት ።

በነዚህ በ3ቱ ቀናት የተቃውሞ ትዕይንት ወቅት በሀግሪቱ ውስጥ በአጠቃላይ ለውጥ ጠቋሚ (የህዝቡን ጥያቄ በተገቢና አጥጋቢ መልክ ለመመለስ የሚያስችል ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ የያዘ አቋም ወይም ውሳኔ ) መንግስት ካልወሰደ ወይም ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደተለመደው “ ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ አትችሉም “ በሚል እንደገና ሰልፉን በጠመንጃ ለመበተን ፤ለመከልከል ( ከቶውንም ህዝቡ ከቤታቸው ወደ አደባባይ አንዳይወጣ ) በህዝቡ ላይ የሃይል እርምጃ መውሰድ ከጀመረ (ከቃጣ ) ከዚህ በፊት ላለፉት 24 ዓመታት እስከ ዛሬ የቀጠለው የሰላማዊ ትግል ምዕራፍ ከመቅጽበት ይዘጋና ህዝቡ ወደቤቱ ሳይመለስ ወዲያውኑ በያዘው ዱላ ፤ስለት ፤የግል መሳሪያና ተቀጣጣይ እሳት ጭምር ራሱን ከመከላከል አልፎ ጠላቱን እየተናነቀ ተረባርቦ በመግደል የጠላትን መሳሪያ ቀምቶ ቀጣይና ያልተቁረጠ ጦርነት ውስጥ በመግባት ከላይ አስቀድሞ እንደተጠቆመው የወያኔን ዋና ዋና የግል ንብረትና ቁልፍ የሆኑ ወሳኝ ባለሥልጣናቱን ቀደም ሲል በጥንቃቄና በምስጢር ተጠንቶ በተዘጋጀው ስልት ( እቅድ ) መሰረት pg. 19

ያወድማል ፤ ያስወግዳል ፤ መግቢያና መውጪያ መንገዶችንም በመዝጋት የኢኮኖሚና የወታደራዊ እንቅስቃሴን በማምከን መንግስትን አቅም ሽባ ማድረግ ይቻላል ።

ማሳሰቢያ ፦

እንዲህ ዓይነቱን የጥቃት እርምጃ መውሰድ በተናጠል ፤ በተለያየ ቀን ፤ በተለያዩ ቦታዎችና ሰዓታት ለማድረግ ማቀድ አለስፈላጊ መስዋዕትነትን ስለሚያስከፍለን ጨርሶ መታሰብ የለበትም ፤ ይልቁንም በሁሉም አቅጣጫ ወያኔን አደናግጦ ግራ በማጋባት ሃይል በመበታተን አቅም ለማሳጣት እንዲረዳን በተመሳሳይ ቀን ፤ ሰዓት ፤ በህሉም ክልልና ስፍራ ሁሉ እኩል ጥቃት መሰንዘር ከጀመርን ያልታሰበ ዱብ-ዕዳ እና ናዳ ከሰማይ ቁጣ የማይተናነስ የህዝብ ክንድ ስለሆነ የኋይል አሰላለፉ ከመቅጽበት ይቀየራል ፤ በርካታ ድሎችንም ማስመዝገብ (ማግኘት) ይቻላል ።

ምክንያቱም ፦

1ኛ. የወያኔ ሃይሎች የቱንም ያህል መሳሪያና የሰራዊት ብዛት ቢኖራቸውም ከየማዛናቱ ገንፍሎ የሚወጣውን የህዝብ ቁጣና የጥቃት እርምጃ ጨርሶ መቆጣጠር ቀርቶ መመከት አይችሉም ፤

2ኛ. የእስከ ዛሬው የወያኔ መሳሪያና ቀኝ እጅ ( ባንዳ ) የነበረው የ “OPDO”አባላት ፤ የአካባቢ ታጣቂ ሚሊሻዎች ፤ ፖሊስና የፈደራል ጦር አባላት የነበሩ የኦሮሞ ተወላጆች መካከል ከፍተኛ የሆነ አዲስ የአሰላለፍ ና የአቋም ለውጥ ወዲያው ስለሚፈጠር ከህዝቡ ጋር በመሆን ጠመንጃቸውን ወደ ወያኔ የሚያዞሩ ፤ የህዝቡንም የትጥቅ ትግል አመጽ በመቀላቀል (ምናልባትም በአስገራሚ ፍጥነት የህዝብ አመጹን በመምራት ) የላቀ ታሪካዊ ሚና ሊጫወቱ የሚችሉ ኋይሎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ጥርጥር የለኝም ፤

3ኛ. በሚፈጠረው አዲስ የሃይል አሰላለፍ ሳቢያ ወያኔ ክፉኛ ተደናግጦ መያዣ መጨበጫ ያጣና በሽብርና በፍርሃት ከመዋጡ የተነሳ ሥልጣን ጥሎ በየአቅጣጫው ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ልፈረጥጥ ይችላል ወይም ለጊዜው ለመገመት የሚያዳግት ሌላ ጥፋት ሊፈጽምም ይሞክር ይሆናል ፤

4ኛ. ያንን ትዕይንትና አዲስ አሰላለፍን በትዝብት ( በጥርጣሬ ) የሚመለከቱ የውጪ ዲፕሎማቶች ፤ የዓለም ሀገራትና ታላላቅ መንግስታት ፤ ሚዲያዎች እንዲሁም የሰባአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሁሉ ለትግሉ ክብደት ፤ ልዩ ትኩረት እና አክብሮት በመስጠት አዲስ የመፍትሄ ሃሳብ ይዘው ለዳኝነት ( ለሸምጋይነት ) ብቅ ይላሉ ፤

5ኛ. ከዚህ ሁሉ የውስጥና የውጪ ጫና በኋላ ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ራሱን ለድርድር ያቀርባል ፤

6ኛ. ያኔ ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ በጨበጠው ጊዜያዊ ድል ሳይኩራራ ድርድሩን አሜን ብሎ በመቀበል ፤ነገር ግን ለራሱ በሚያመች ሁኔታ ለመሰረታዊ ችግሩና የትግሉ ዓላማ አኳኋን ዘላቂ መፍትሄን የሚያስገኝ የተጠናን ቅድመ ሁኔታን አስቀድሞ አዘጋጅቶ ወቅቱ ሲደርስ ይዞ ለመቅረብ ካሁን ጀምሮ ራሱን ያዘጋጃል

ለምሳሌ ፦

1ኛ. ለጠፋው ህይወት የደም ዋጋን መክፈል ፤ pg. 20

2ኛ. በድብደባና በጥይት ለቆሰሉና አካለ ጎደሎ ለሁኑ የአካል ጉዳት ካሳ ክፊያ ፤

3ኛ. ከሥራ የተባረሩና ከትምህርት ገበታ የተፈናቀሉትን ወደ ነበሩበት መመለስ፤

4ኛ. በየእስር ቤቱ የታጎሩትን በአስቸኳይ መፍታት፤

5ኛ. የንጹሃንን ህይወት ያጠፉትን ነፍሰ-ገዳዮችንና በድብደባ ህዝቡን ያሰቃዩትን ወንጀለኞች ለፍርድ ማቅረብ ፤

6ኛ. በሰላማዊ መንገድ የፍትህና የመብት ጥያቄ ያቀረበውን የኦሮሞ ህዝብ በንቀት ተመልክተው “ አጋንንት ፤ ሳይጣን ፤ አሸባሪ “ ወዘተ..ብለው የተሳደቡ ፤ “ቢወዱም ባይወዱም ማስተር ፕላኑን በግድ ሥራ ላይ እናውላለን ፤ እምቢ ካሉ ግን ልክ እናስገባቸዋለን “ በማለት የዛቱና ያስፈራሩ ግለሰቦችን ለፍርድ ማቅረብ ፤

7ኛ. OPDO እና ወያኔ ህዝብን የሚመሩበትና ሀገርን የሚያስተዳድሩበት ስብዕና ፤ ሞራል ፤ አቅምና ችሎታ የሌላቸው ፤ ሃላፊነት የጎደላቸው አረመኔና ዘራፊ ወሮበላ ሽፍቶች ስለሆኑ ከሥልጣን ወርደው ሥልጣኑን ለህዝብ ተወካዮች እንዲያስረክቡ ፤

8ኛ. ዘመነኞቹ ባለጊዜ የህወሀት ከበርቴዎችና የነሱ ተላላኪና አሽከር የሆኑት ባንዳዎች በሙሉ ከሀገር የመዘበሩትንና ከህዝብ የዘረፉትን ሃብትና ንብረት ለህዝብ እንዲመልሱ፤

9ኛ. የወያኔ መንግስት ህዝቡን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤

10ኛ. ለብዙዎች ከቄያቸውና መሬታቸው መፈናቀልና መነቀል ፤ የበርካታ ሰዎች ህይወት ህልፈት ፤ የአካል ጉዳት ፤ መታሰር ና የመሰደድ ሰበብ የነበረው የአዲስ አባባና አካባቢው ማስተር ፕላን እቅድና ዓላማ ስለመሻሩ ማረጋገጫና ከእንግዲህ ህዝቡ የመረጠው የመፍትሄ ሃሳብ ትልቅ ግምት ተሰጥቶት ሥራ ላይ እንዲውል አስተማማኝ ዋስትና መስጠት ፤

በተረፈ ወደዱም ጠሉ ፤ ማስተር ፕላን ተብየው ቢቀርም ቢመጣ የኦሮሞ ህዝብ ከ”OPDO” እና ከወያኔ ጋር ደም ተቃብቷል ፤ የደም ዋጋ ደግሞ ያው ደም ነው፤ ይዋል ይደር እንጂ ፤ ጊዜ ይፍጅ እንጂ ቀኑና ሰዓቱ ሲደርስ የዘሮቻችን ፤ የልጆቻችን ደምና መተኪያ የሌላት ህይወት ዋጋን በእጥፍ እንበቀላለን ።

ይህ ሁሉ ሲሆን በወገን በኩል ከፍተኛ የንብረት ውድመት ፤ የአካል ጉድለትና የህይወት መስዋዕትነት እንደሚጠይቀን ከወዲሁ መገመት ብቻ ሳይሆን የማይቀርልን ከባድ ፈተናና ዋጋን የሚያስከፍል አይቀሬ መሆኑን ተገንዝበን እያንዳንዱ ኦሮሞ አሁን ካጋጠመው እልቂት ፤ ባሪነትና ሊመጣበት እያንዣበበ ካለው የዘላለም ጥቃትና ውርደት ከወዲሁ ለማምለጥ ከፈለገ በቁርጠኝነት ለመሰዋት ራሱን ለትግሉ ማዘጋጀት ይጠበቅበታል ። አለበለዚያ ክከዚህ ቀደሙ እጅግ የከፋ በምንም መንገድ ሊወጣው የማይችል ጥቃት ፤ ሀገርና የራሴ ነው የሚለው ቅርስና መኖርያ የሌለው ባርነት ፤ ድህነት ፤ ስቅይና ቅሌት መጪውን ትውልድ እንደሚጠብቀው መታወቅ አለበት።

ምክንያቱም የሚንታገለው ለነጻነት ፤ ለኩልነት ብሎም አጠቃላይ ጭቆናንና አድልዎን በመቃወም መብትን አስከብሮ ፍትህና ሰላምን ለማስፈን ነው ። pg. 21

ነጻነት ደግሞ ዋጋው ብዙ ፤ እጅግም ውድና ታላቅ ነው ። “Freedom is not free “ ይላሉ ፈረንጆች ። ነጻነት ርካሽ ስላልሆነ ያለዋጋ በነጻ አይገኝም ማለታቸው ነው ። በርግጥም ያለአንዳች ድክምና ልፋት ብሎም ዋጋ የሚገኝ ሁሉ አይጣፍጥም ፤ ርካሽ የሆነ ሁሉ ዋጋና ክብር የለውም ፤ ደግሞም አይጥምም ፤ማንም አይፈልገውም ፤ ለዚህም ነው የኛም ነጻነት በብዙ መከራና ፈተና የተከበበ ፤ በልዩ ልዩ ውስብስብ ችግሮች የተተበተበ ፤ አጣብቂኝ ውስጥ ያለ የከበሩ ማዕድናት ( ወርቅ ፤ አልማዝ ፤ እንቁ )ወዘተ ... የመሳሰሉት ያህል ውድና እሩቅ የሆነብን ።

ይሁን እንጂ የቱንም ያህል ጊዜ ቢፈጅ የተፈለገውን የንብረት ውድመት ፤ የአካል ጉዳትና የህይወት ህልፈት ዋጋ ቢያስከፍለንም ፤ ነገር ግን በጊዜውና በቀኑ ከብዙ ድካምና መስዋዕትነት በኋላ በእርግጠኝነት የራሳችን የግላችን የሚናደርገው ነጻነት በእጃችን ሲገባ እጅግ በጣም በጣም ደስ ይላል ፤ ይጣፍጣል ፤ የአዕምሮ እረፍት ፤ የመንፈስ እርካታን ፤ የልብ እፎይታን በማስገኘት እኛንና መጪውን ትውልድ የሚያኮራ ገድልና ታሪክ ይሆናል ።

በነገራችን ላይ ነጻነት የዜጎች መብት ነውና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ነጻነታችንን ማረጋገጥ ከፈጣሪ አምላክ የተሰጠን ተፈጥሮያዊ መብት ነው ፤ ከዘርንማንዘራችን ሲወርድ ሲዋረድ የተሰጠችን ቄያችን መሬታችን ፤ ርስታችንና ሀገራችን ኦሮሚያ የተፈጠርንባት ፤ እትብታችን የተቀበረባት ፤ የኛው መንደርና የዜግነት መብታችንም ገና ስንወለድ አብሮን የተሰራ ለኛው እንዲውል የተፈጠረ እንጂ ማንም መንገደኛ ዟሪ መጤ በችሮታው የኛኑ መልሶ ለኛ ሰፍሮና ለክቶ የሚቆርስልን ፤ ትንሽ ቆንጥሮ የሚበትንልን ፤ ወይም መጥኖ የሚያጎርሰን የእንጀራ እናት ቅምሻና ጉርሻ ወይም የግለሰብ ጉልቤዎች ችሮታና ገጸበረከት አይደለም ።

እኛ የኦሮሞ ልጆች ዛሬ የሚንፈልገው አንድ ነገር ነው ፤ ነጻንታችንን ። ሁላችንም ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ ታሪካዊ ተጽዕኖች ለዘመናት ከኛ ርቆ የቆዩትን በኢኮኖሚ ፤ በሥልጣን ፤ በባህል ፤ በቋንቋ ፤ በእምነታችን የማንም ተለጣፊ መሆንን አንሻም ። በሀገራችን ፤ በመሬታችን ፤ በቄያችን ተከብረን የመኖር ፤ የመናገር ፤ የመጻፍ ፤ የመጠየቅ ፤ የመደራጀት ፤ የመምረጥ ፤ የመመረጥ ፤ ራስን የማስተዳደር ፤ ( የመምራት ) ፤አካባቢያችንን ለኛ በሚጠቅም ና በሚመች መልኩ እየተንከባከብን የማልማት መብትና ሃላፊነቱ የኛ የባለቤቶቹ ፤ የባለ ታሪኮቹ ድርሻና ሃላፊነት እንጂ የማንም የውጪ ባዕድ ጣልቃ ገብነት ቦታ የለውም ።

ምክንያቱም ሀገር ማለት ህዝብ ነው ፤ሰው የሌለው መሬት ደግሞ ብቻውን ሀገር ሊባል ከቶ አይችልም፤ ነጻ ሀገር የሌለው ህዝብም ሁሌ የሌላ ጥገኛ ና በማንም የሚደፈር ለጥቃት የተጋለጠ ስለሆነ ሰባዊ ፍጡርነቱ የተገፈፈ ፤ የዜግነት ክብሩና መብቱ የተረገጠ ፤ የተናቀ ምስኪን ጥገኛ ( ስደተኛ ) ፍጡር ስለሆነ ከምርኮኛ ፈጽሞ የማይሻል የግለሰቦች ባሪያ አሽከር ( ገረድ) ነው ።

የኦሮሞ ማህበረሰብ ለዛሬው ቄያችን ፤ መሬታችን ኦሮሚያና ብሎም ኢትዮጵያ በዓለም ካርታ ላይ መኖር የዘርንማንዘሮቻችን የዘመናት መስዋዕትነት ሁሉ ድምር ውጤት ነው ፤ ከዚህ ቀደም ለብዙ ሺህ ዓመታት በቅድመ አያቶቻችንና ከዚያም በፊት በነበሩት ዘሮቻችን ተጠብቆ የኖረው መሬታችን (ሀገራችን) ዛሬ እኛ በህይወት እያለን እፍኝ በማይሞሉ ተራና ወራዳ ሽፍቶች ከማስወሰድ የበለጠ ጥቃት ፤ በቁም መደፈርና ቅሌት፤ ሞትና የታሪክ ኪሳራ የለም ።

የዛሬን ሳይጨምር ከጨቋኞቹ የአጼዎች ሥርዓትና ከአምባ ገነኑ የደርግ መንግስት የጥይት ሰለባነት የተረፉትን ህዝባችንን ትግሬ መራሹ የወያኔ ጎጠኛ ቡድን በያንዳንዷ ቀንና ሌሊት ላለፉት 24 ዓመታት pg. 22

ደማችንን እያፈሰሰ ዘሮቻችንን ፈጅቷል ። የዚህ የሰሞኑ መግደል ፤ ማሰር እና መደብደብ ብቻ ሳይሆን የኦሮሞና የዛሬዋ ኢትዮጵያ ዋና እንብርት የሆነውን የብርቅዬ ጀግኖች እትብት የተቀበረበትን የሽዋን ክፍለ ሀገር ወርሶ የትግራይ ሪፓብልክ አካል ሊያደርጋት ፈልጎ የዜግነት መብታችንን ጭምር ገፎ አሳዶ እያበረረ በአውሮፕላን በቦንብና በጥይት የጅምላ ጭፍጭፋ እያካሄደብን ይገኛል ።

ይህኛው ጥቃት ከከዚህ ቀደሞቹ ጭቆናዎችና የመብት ረገጣዎች እጅግ በተለየ ሁኔታ ንቀትና እብሪት የተሞላበት ወደር ያልተገኘለት በአዋጅ ዘርን የማጥፋት (genocide) ዘመቻና አዋጅ ነው ። አሁንም እንካ ይህቺን ሃሳቤን ለናነተ ለኦሮሞ ወገኖቼ ለማካፈል ሲነሳ በሁሉም የኦሮሞ ክልሎች ወገኖቻችንን ወያኔ በጥይት ሲቆላ ፤ ዛፍ ላይ ሲያንጠለጥል ፤አሰቃይቶ ገድሎ እሬሳቸው እንኳ በአግባቡ እንዳይቀበር ማንነታቸው እንዳይታወቅ ፊታቸውን አበላሽቶ ሰውነታቸውን እንደ አውሬ ቆራርጦ ለአውሬ ሲሳይ እንዲሆኑ በየጥሻው ስወረውር መላው ዓለም እያየ ፤ እየሰማ ፤እየታዘበ ቢሆንም ፍትህ ግን የሚሰጠን ፤ከደም መጣጩ አውሬ የሚያስጥለን አልተገኘም ።

ለመሆኑ እኛ ማን ነን ?

ምክንያቱም እኛም ደክመን ፤ ፈርተን በተለያዩ ውስጣዊ ችግሮችና በጠላት መሰሪ ተንኮል እርስበርስ ተጠላልፈን ፤ አንድ ለመሆን መቁረጥ አቅቶን ዳኛ ጠፍቶ ፍትህ ጎድሎ በተቃራኒው ግን እየሞትን እየጠፋን ደማችን እየፈሰሰ ወንጀለኛ ፤ አሸባሪ ፤ ጸረ-ልማት ወዘተ ተባልን ።

ይህም ሁሉ ተፈጽሞብን መሬታችንን አልተከላከልንም ፤ ቄያችንን የራሳችን ማድረግ አልቻልንም ፤ የዜግነት መብታችንን አላስጠበቅንም ፤ ነጻነት አጥተናል መብታችን ተገፏል ፤ በሰው ሀገር የሚኖር ስደተኛ እና ምርኮኛ ያህል እንኳ ክብር አጥተናል ፤ ባሪያዎች ተደርገናል ፤ የፈሰሰው ደማችንን አልተበቀልንም ፤ተንቀናል ፤ ካሉትም ከሞቱትም በታች ሆነናል ።

አረ ለመሆኑ እኛ ማን ነን ? እንዴት ቅጫም ወሮበላ ወያኔ ( ጥቂት የትግሬ መንጋ ) ከምድረ- በዳ እስከ ደጃችን ድረስ መጥቶ ቄያችንን እንዴት ሊያስለቅቀን ቻለ ? ለምን እንገደላለን ? ምን ነካን ? በዚህች ምድር ላይ ስንቴ ነው መኖር የሚንችለው ? ከፈጣሪ የተሰጠንን ዕጣ ፋንታና ዕድል በሌሎች ከስወሰድን ሌላ ተለዋጭ ቀሪ ዘመንና ዕድል ለኛ ብቻ ከእንግዲህ አለ ዎይ ? ስንት ነፍስ አለን ? ስንቴ ነው የሚንሞተው ? ገዳያችንን ለምን አንገድልም ? ተራ በተራ ሞትን ከምንጠብቅ ሞት የማይቀርልን ከሆነ በነጻ ከምንሞት ገለንስ ለምን አልሞትንም ?

ቢገባንም ባይገባንም የማንረባ ፤ ለራሳችን የማንበቃ ሆነን በመታያታችን ዓለምና ጎረቤቶቻችን ፤እንዲሁም ጠላቶቻችን ጭምር ቆመው በንቀት እየታዘቡን ናቸው ። እንዴት ማሰብ አቃተን ? የደም ዋጋ እኮ ደም ነው ፤ እስከ አሁን እየፈሰሰ ያለው የወገኖቻችን ፤ የጨቅላ ህጻናት ወጣቶችና ጎልማሳ አረጋዊያን ንጹህ ደም ለኛ ለቀሪዎቹ የሲቃ ድምጽ እየቃተተ ከትቢያ እየጮሀ ነው ።

ውድ የኦሮሞ ልጆች ፤ ወገኖቼ ዘመዶቼ ዘሮቼ ሆይ !

መተኪያ የሌላቸው ብርቅዬ ወገኖቻችን ደምና ህይወት ከንቱ ሆኖ መቅረት የለበትም ፤ በብዙ እጥፍ በመበቀል ማንነታችንን አስመስክሬን ፤ የተወሰደብንን መብትና መሬታችንን አስምልሰን ፤ በሀገርና pg. 23

በህዝባችን ላይ የተቃጣውን አደጋና ጥቃት በመመከት የተጋረጡብንን ፈተናዎች በኛው በእሮሞ ልጆች የተባበረ ክንድ ፤ በእግዚአብሔር ፈቃድና እገዛ ፤ እንዲሁም በሌሎች ሰላም ወዳድ እና ፍትህ ናፋቂ ህዝቦች እና ብሔር ብሔረሰቦች የጋራ ትብብርና ርብርብ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የወረረንን ጨፍጫፊ ባንዳ ሰራዊት ከታወጀብን ዘርን በማጥፋት ፤ ህዝብን በማሸማቀቅ ባሪያ አድርጎን ሊገዛን ፤ ቄያችንን ሊቀማ የመጣብንን የሽፍታ መንጋ መበተን ብቻም ሳይሆን ጨርሶ መደምሰስ ይቻላል ።

ስለዚህ በቃ !! ኦሮሞ የሆንክ ንቃ ፤ ወገንህን አንቃ ፤ ለኦሮሞ ጥቅም በእርግጥ በሀቀኝነት ሊቆም የሚችል የጋራ የሆነ ወሳኝ ማዕከላዊ አመራርን ለመፍጠር በቅንነት እና በታማኝነት ሌት ተቀን ትጋ ፤ በየደቂቃና ሰኮንድ የወገኖቻችን ህይወት እየረገፈ ባለፈው ስህተትና ጥፋት ስትከራከርና ስትዋቀስ ስትካሰስ ወርቃማ ጊዜህን አታጥፋ፤ ጠላትህን ፈጥነህ አጥቃ ፤ ለዛሬም ሆነ ለወደ ፊት በሚያዋጣን ጉዳይ ላይ ብቻ በትግስት ተነጋገር ፤ ተመካከር ፤ ተወያይ ፤ ሚስጥርህን ከኦሮሞ ውጪ ለማንም አትናገር ፤ገርነትና የዋህነት ከእንግዲህ ይብቃ ።

በሌላ በኩል የህዝብና የሀገር መሪ ለመሆን የሚመኝ የኦሮሞ ፖለቲከኛ ካለ ተራርቆ ፤ ተኮራርፎ ፤ ከህዝቡ ተለይቶ ፤ ከትግሉ ሜዳ ርቆ ፤ምንም ዋጋ ሳይከፍል በእስክርፕቶና ወረቀት ፤ በወሬና በምኞት ብቻ ፍሬ ያለው ሥራ መስራት እንደማይቻል ተረድቶ ለህዝብ የሚጠቅም ራዕይና ቪዢን አለን የሚሉ ሁሉ ከያሉበት ተፈላልገው እና ተጠራርተው በመከባበርና በመቻቻል እየተነጋገሩ ፤ በጋራ እንዲመካከሩ ፤ ድርሻ ድርሻቸውን ተከፋፍለው ከቦታ ቦታ ሌት ተቀን ተዘዋውረው ወደ ህዝብ ቀርበው አጀንዳ አዘጋጅተው ከህዝብ ጋር ለመገናኘትና በቅርበት ትግሉን ለመምራት መድረክ እንዲፈጥሩ ፤ እቅድና ስትራቴጂ ነድፈው ለአንድ ዓላማ ወጥ በሆነ ማዕከላዊ አሰራርና አመራር ሥር ህዝብን አዋቅረው እንዲያንቀሳቅሱን አደራ እላለሁ ።

በተረፈ “ ግርግር ለሌባ ያመቻል “ እንዲሉ ይህንን አጋጣሚ ተጥቅመው መላው የኦሮሞ ተሳትፎ እና ምክክር የሌለበት ፤ ፈቃድ ፤ ሃሳብ ፤ ፊላጎትና ውሳኔ ያልታከለበት አካሄድ እንደ ከዚህ ቀደሙ ለብዙኋኑ ኪሳራና የዘመናት እንግልት ፤ ለጥቂቶች ደግሞ ለጊዜውም ቢሆን ለትናንሽ የሥልጣን ቦታዎች መንጠላጠያ እንጂ ለማናችንም ዘላቂ ጥቅምና መፍትሄ አስገኝቶልን አያውቅም ።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም በተለያዩ አጋጣሚዎች የኦሮሞን ምንነት ፤ መብት ፤ እና ነጻነት ስክዱና ባህል ቋንቋውን ብሎም እምነትና ታሪኩን ሲያንቋሽሹ ከነበሩት የጭቃ ውስጥ ጠላቶቻችን ጋር አንዳንድ የኦሮሞ ፖለትከኞች ከኦሮሞ ህዝብ ጀርባ በእሮሞ ህዝብ ስም እርቅ ፤ ድርድር ፤ አንድነት ፤ ወዘተ ‘’ በሚል የጀመሩት ድብቅ አጀንዳ ካለ ከትናንት የከፋ መጃጃልና ትርፍ የሌለው አካሄድ ስለሆነ በእንዲህ ዓይነት መንገድ የሚጓዙ ካሉ ለኪሳራና ውድቀት የሚዳርገን የፖለቲካ ንግድ ነውና እንዲህ ዓይነቱን መቀበል ከባድ አደጋ ስላለው ማናችንም ቢንሆን ያንን ማድረግ እንደሌለብን ዳግመን ደጋግመን በጥንቃቄ ማሰብ ይኖርብናል እላለሁ ።

የኦሮሞ ሚዲያዎችም እንዲሁ በዚህ ጉዳይ ላይ ይበልጥ የህዝቡን የጋራ ግንዛቤ ለመጨመር ፤ የተሳሰረ አንድነትን ለመፍጠር ፤ ደጋግመው እንዲናገሩ እንዲመክሩ ፤ እንዲያስተምሩ ፤ እንዲያወሩ ፤ የኦሮሞ ህዝብ ለመብቱና ለነጻነቱ እየከፈለ ያለውን መስዋዕትነት እያስተጋቡ ፤ ቁጣውንና ጩሀቱን እያሰራጩ ፤ ለፖለቲካ መሪዎችም እርማት ፤ ጥቆማንና ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችን እያመነጩ የተቀናጀ ውጤት የሚያስገኝ pg. 24

ሥራ እንዲሰራ ፤ከዋናው ግባችን ላይ እንዲንደርስ የኦሮሞን ህዝብ የሚያስተባብር ጥሪ ሁሌ ያለመታከት እንዲያስተላልፉ በአክብሮት ለማሳሰብ እወዳለሁ ።

የራሳችን ቄዬና መሬት ባለቤት መሆናችንን በማረጋገጥ ፍትህ ፤ ነጻነት የሰፈነበት ፤ የሰው ልጆች መብት እኩል ተጠብቆ ፤ ባህል እምነት ፤ ቋንቋ ልማድና ታሪክ እኩል ተከብሮ ፤ የህግ የበላይነት በተግባር ሥራ ላይ የሚውልበት ዲሞክራሲያዊ ት የሆነች ሀገር ለመገንባት እንብቃ ፤ አድልዎና ጭቆና ፤ ዘረኝነት ፤ ጎጠኝነት ፤ ጠባብነት ፤ የብሔርተኞች እብሪት ፤ ትምክህት ፤ ትዕቢት ንቀት የሌለበት ፤ ከሙስና የጸዳች ፤ ለዜጎቿ ሁሉ የሚትመች ሰላማዊ ምድር ለመፍጠር በቆራጥነት እንውጣ እያልኩ የአክብሮት ጥሪዬን ለናንተ ለወገኖቼ ለኦሮሞ ልጆች ትህትናና አክብሮት የተሞላበትን ወገናዊ የኡኡታ ጥሪ ከአደራ ጭምር አሰማለሁ ።

የታሪክ አተላ ሆኖ እየተዋቀስን ፤ እየተሳቀቅን ተዋርደን በድህነትና በባርነት ከሚንማቅቅ ዛሬውኑ ጠላታችንን ለመደምሰስ ወኔን እንታጠቅ ፤ በክፎዎች መሰሪ ሴራና ረቂቅ ተንኮል ላለመጠላለፍ አበክሬን እንጠቀቅ ።

የኦሮሞ ደም ፈሶ በከንቱ አይቀርም !

እግዚአብሔር ከኛ ጋር ነው !!

ድል ለኦሮም ህዝብ !!!

ሞት ለወያኔ !!!!!!

ዋቁማ ጮቢ ( Ijoollee Jalduu) , Sanyyii Warra Salaallee ,Makaa warraa Gindoo

Email ; ijoolleejeldu.16@gmail.com

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved