Gumii Paarlaamaa Oromoo (GPO)

Oromo Parliamentarians Council (OPC)

 

Baga Nagaan Dhuftan!Welcome to Oromo parliamentarians council!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

              New Page 2 home                         

Who is Dr. Addisu Gebregziabher head of the Ethiopian Human Right Commission (EHRC)

 

by Melkamu Temesgen

Dr. Addisu Gebregziabher was born in Corrupted family, Corrupted regime, educated by Corrupted way and corrupted money and organizing corrupted groups and leading corrupted organization. When thousands of Ethiopian students where suffering without food  in former USSR Addis  Gebregzibher earned $3000.00 every month and also studying at the Russian friendship university. Dr. Addisu Gebregziabher head of the Ethiopian Human Right Commission (EHRC) is responsible for 4,000 life of Oromo who’s are Killed since 2014_2016. Ed.

"ዜጎች ስለሰባአዊ መብቶች የጠለቀ ዕውቀት ስላሌላቸው፣ሀገሪቱ ሞጋችና መብቱን ደፍሮ መጠየቅ የሚችል ዜጋ አላፈራችም።"
/ አዲሱ /እግዛብሔር የወያኔ መንግሥት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፡

ግለሰቡ ይህንን አስተያዬት የሰጠው፣ ከጥቅት ቀናት በፍት አቶ አባይ ፀሐዬ በምመራው የፖሊሲ ጥናት ውይይት ስብሰባ ላይ ነው። እሱ ስለ ሰባአዊ መብት ዕውቀቱንና አተረጓገሙን አውቆ ለዚህ ቦታ የታጨ ሳይሆን በህወሐት አባልነቱ የምርጫ ቦርድ ምክትል ኃላፊ ሆኖ፣ የህዝቦችን ድምፅ በማዘረፍና ለህዝብ መብት ተሟጋች የሆኑትን የህዝብ ልጆች ስያንገላታ የነበረ፣ህዝብ ያልመረጣቸው ወገኖች ወደ ሥልጣን እንዲወጡ፣የተሰረቀን የህዝብ ድምፅ አስተላልፎ የሰጠና ያሰጥ የነበረ፣የተቀወሚዎችን አቤቱታዎች በማፈን በምርጫ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ላይ ይደርስ የነበረውን ማስፈራራት፣ እሥራትና ከሥራ መባረር በስልት ስያስፈጽም የነበረ ወንጀለኛ ነው።በተለይም በኦሮሞ ፕሮቴስት ህደት ውስጥ በኦሮሞ ፈዴራል ኮንግሬስ አባለት ላይ ለደረሱት እሥራቶች፣ አዲሱ /እግዛብሔር በህገ ወጥ መንገድ ለደህንነትና ለመረጃ አገልግሎት ቀደም ስል ከምርጫ ቦርድ የተቃወሚ ዕጩዎችን ዝርዘር ያስተላልፍ የነበረ ስለመሆኑ በትክክል ስለ ሁኔታው የተከታተሉት በምሬት ይገልጻሉ።የመለስ ዜናዊ የጣት ቆረጣ ራዕይ ተግባራዊነት ማለትም ይኼ ነው። የበለጠ ግልጽ ለማድረግ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የተቃዋሚ ድርጅቶችን አስመልክቶ ..."ተቃዋሚዎች እንዳይኖሩ አንቃወምም፣ጣት እስክያወጡ ድረስ ጠብቀናቸው ...ጣታቸውን እንቆርጥላቸዋለን፣ከዚያም አርፈው ይቀመጣሉ" የሚለው የወያኔዎች የውስጥ መመሪያ ነው ማለት ነው።በመሆኑም ከነ አዲሱ /እግዛብሔር ስለ ሰባአዊ መብት መጠበቅ ሞኝነት ነው።
 

ይህ ሰዉ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተደረገውን ተቃውሞና አስመልክቶ ለሀገሪቱ ፖርላማ በቀረበውም ሪፖርት..."ከደረሰው ጥፋት አንጻር የተወሰደው ዕርምጃ የተመጣጠን ነው" በማለት በዚያ ሁሉ ህዝብ ህይወት ላይ የተሳለቀ ሰው ነው።በዕርግጥ ሪፖርቱ ከዚያ እንደማይሻገር ቀድሞም የታወቀ ነው። ታዲያ ለመብት ሞጋቾችና ደፍረው ሰለ ህዝብ ብሶት የሚናገሩትን እያሰሩ፣ እየገደሉና እያሳደዱ...."ጣት እየቆረጡ" ደፍሮ የሚናገር ጠፋ ሲባል ትንሽ እንኳን አያሳፍርም? የወያኔ መንግሥት የኦሮሞን የመብት ተሟጋች ድርጅቶች መጫና ቱለማን፣ የሰባአዊ መብት ሊግንና ኦራን (ORA) በውሸት በመወንጀል፣ ንረብቶቻቸውን በመዝረፍና መሪዎቻቸውን እንዲታሰሩ ወይም እንዲሰደዱ አድርጓል።የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ይቅሩና የኦሮሞ ሲቭክ ድርጅት መሪዎች ከወያኔ በዕውቀትና በሰባአዊ መብት ግንዛቤ የተሻሉና የበለጡም ነበሩ።እንደ ዛሬው የወያኔ መሪዎች የውሸት ዲግሪ ገዝተው ሳይደረድሩ ኦሮሞ ተሟጋች የተማሩ ልጆች ነበሩት፣ዛሬም አሉት።በወያኔ እሥር ቤቶች እየተሰቃየ ያለው ኦሮሞ ለህዝብ መብት ተሟግቶ እንጅ ሰርቆና አጭበርብሮ አይደለም። ሌላው የአባይ ፀሐዬ ንግግር ነው። የሚከተለዉን እንይ፤....በፖለሲ ጥናቱ ዘገበ መሠረት "...ዲሞክራሲን የገደቡት ችግሮች፣ በዜጎች ላይ የሚደርሰው ኢዴሞክ ራሲያዊ አያያዝ "ነው።ይህንኑ አባይ ፀሐዬ ስተነትን... " ችግሮችን ማስተካከል ያለበት ኢህአዴግ ነው፣ይህች ሀገር ወደ ትርምስ እንዳትገባ ከተፈለገ መንገዱ አንድ ብቻ ነው፣ አለባለዚያ ይህች ሀገር ትቀጣጠላለች፣እዚህች ሀገር ውስጥ ሊፈነዱ የተቃረቡ ችግሮች አሉ፣.." የህዝብ ጥያቄ ገፍቶ ከቢሮው ልደርስ የተቃረበ ጊዜ "ልክ ለማስገባት" ይዝት የነበረው ሰው አሁን ደግሞ ህዝቡን በምላስ መሸንገል የዘለቄታ መስሎት በየወሩ በተለመደው ዲስኩር "ኢህአዴግን ያስተካክላል።"ተቃረቡም ዘገዩም ግን ችግሮች ይፈነዳሉ።በሙስና በአድልዎ፣ባልተመጣጠነ የሀብት ክፍፍል፣በፍትህ ዕጦት፣ በመብቶች መገደብ፣ በሰባአዊ መብቶች መጣስ ነገሮች  ይፈነዳሉ።ወያኔዎች በህዝቦች ላይ የነገሱ ትናንሽ ንጉሶች ናቸው።ደርግ 120 አባለት ነበሩት፣የተወሰኑቱ ያስተዳድሩ በነበሩበት አካባቢ "ንጉሶች"ነበሩ።

 እነዚህ የወያኔ ንጉሶች ናቸው።

ወያኔዎች የፓርቲያቸውን አለባት ፣የወታደሮቻቸውን ብዛት መጠን ንጉሶች ሆኔዋል።ሁሉንም ያደርጋሉ፣"...ዴሞክራሲ ይሰጣሉ...ይነሳሉ፣ የሚዲያ ነፃነት ያውጃሉ...ጋዜጣኛን በቂሊንጦና በማዕከላዊ አስረው ይገርፋሉ፣የተቃዋሚዎችን መብትያከብራሉ... መሪዎቻቸውን አስረው ያሰቃያሉ፣የህዝብን የመናገር መብት ይጠብቃሉ...ወጣቱን ስለ Qeerroo ዘፈን ሰማህ ብለው አሥርና ሃያ አመት ይፈርዱበተል።የዜጎችን የመኖር ዋስትና ያስጠብቃሉ...መሬታችንን ተቀማን የሚሉትን ይረሽናሉ። የዜጎችን ሠርቶ የመኖር ዋስትና ይቀበላሉ...ዜጎች ማለትም የህወሐት አባላት ማለት ነው።""ሀገርን በጦር ይጠብቃሉ.. የጦር መሪዎች ሁሉ ግን ትግራዋ መሆን አለባቸው።የጦር ጄኔራሎቹ የሰለጠኑ ናቸው....የራሳቸውን ህይወት ታሪክ አስተካክለው አይናገሩም፣ሌሎችን ህዝቦች ታሪካቸውን ያስተምራሉ።በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ በጣም የሚፈራው የትግራዋ ልጅ ነው፣ምናልባት ፈጣሪ ግን ሳይፈራ ይከበር ይሆናል....ፍርሃትና ክብር ለየቅል ናቸው።የወያኔ ሰዉ አይነካም፣አይከሰስም...ለማማትም ጥግ ይዘህ መሆን አለበት..በንግርት እንዳትጠለፍ።የወያኔ ሰው ባለፀጋ ነው.. ግብርና ታክስ አይመለከተውም።የወያኔ ሰው መሬት የመንጠቅ መብት፣ባንክ የመበደር መብት፣ብድሩን ያለመመ ለስ መብት፣ቀረጥ ያለመክፈል መብት፣ከክልሉ ውጭ ቦታ ለመመራት ቅድሚያ የማግኘት መብት፣ሳያስፈቅድም እንቬስት የማድረግ መብት፣ ትግራዋ ያልሆነውን ባለንብረትና ነጋዴ በገቢዉ ላይ ተጽዕኖ የሚፈጥር ተመሳሳይ የብዝኔስ መስክ ከለው የማስወገድ መብት..ትንሽ ጠከንር ካለም በፖለቲካ የማስወንጀል መብት፣በኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በሜትክ፣ በውጭ ጉዳይ /ር፣ንግድ ባንክ፣ ብሔራዊ ባንክ፣ በመርከብ ድርጅት፣በምድር ባቡር፣ በመንግሥት ቤቶች አስተዳደር፣በደህንነትና በኤምግሬሼን፣በጉምሩክና ገቢዎች ባለሥልጣን፣ፍንፍኔ ከተማ የተለያዩ የአተስዳደር ዕርከኖች፣ ቀድሞ የመቀጠርና ዋስትናም ያለማረቅብ ትግራዋ መብት አለው።የአውሮፕላን ፖይሌት ፣ሆስቴስ፣ባቡር ነጂና የጦር ጄት አብራሪ ለመሆን አታስብ፣ ባቡሩ ወይም አይሮፕላኑ ሳይገዛ በበጀት እያለ ሥራው ተይዟል።


በአፍርካ ታሪክ 25 አመታት ውስጥ የአንድ ብሔር ህዝብ ተወላጅ ሆኖ ከሌሎቹ አብረውት ካሉት ህዝቦች በተለየ መልኩ በማይታወቅ የሀብት ምንጭ ብዙ ከበርቴዎችን ያፈራ ወነኔ ነው።በአንድ ባለ ብዙ ብሔር ሀገር ውስጥ ሌሎቹ ድርሻ ሳይኖራቸው 25 አመት ውስጥ ብዙ ኮሎኔልና ጄኔራሎች የሾመ መንግሥት የወያኔ መንግሥት ነው።በአንድ ሀገር ውስጥ የአንድ ብሔር አባል የሆኑ ቡድኖች አብሮአቸው ከሚኖረው ሌላው ህዝብ በተለየ መልኩ ከማይታወቅ የገቢ በሃያ አምስት አመታት ውስጥ የተሻሉ መኖሪያ ቤቸች ፣ዘመናዊ የቤት መኪናዎች ስኖሩአቸው ይህ የመጀመሪያ ነው።ለዚህ ሁሉ ክስተት ሙስና፣የሌሎች ህዝቦች መብት መታፈን፤የነፃ ፕሬስ መጥፋትና የመንግሥት ሰዎች ለህግ ያለመገዛት ነው።

ለምሳሌ ቀደም ስል በጋምቤላው የመሬት ዝርፈያ የእርሻ ቦታ ከተመሩት 623 ባለሀብቶች 461 ሰዎች የትግራይ ልጆች ነበሩ።ከነዚህ 461 የትግራይ ሰዎች 200 ባለሀብቸች 4.96 ቢሊዮን ብር ብድር ተሰጥቷቸዋል፤ከነዚህ ወስጥ 29 ሰዎች በፍጹም ጋምቤላ አልደረሱም፤ ግን መሬትም የገንዘብ ብድርም ወስደዋል።ለእርሻ ያለ ቀረጥ ከገቡት 565 ትራክቴሮች ጋምቤላ የደረሱት 312 ናቸው፣253 ቦሌ ላይ የተሸጡ ናቸዉ።ከ261 ፕካ አፕ መኪናቸች ጋምቤላ የደረሱት 102 ሲሆኑ 159 አቅጣጫ ለውጠዋል።ከ62 ዶዜሮች 21 የት እንደ ደረሱ አልታወቀም። ከገቡት ተሽከርካሪዎች አንድ ትግራዋ ሰው 78 መኪኖችን ያለአንዳች ወጭ ከውጪ አሰገብተው ሽጠዋል።
ስለዚህ አባይ ፀሐዬ የፈራት ትርምስ ትመጣለች፣ብዙ ችግሮችም ይመጠሉ። ችግሮቹም በወኔያ ላይ የሚመጡ ናቸው።

 

 

                                                              Copyright ©2008 GPO/OPC Allrights Reserved